Check out the new design

Translation of the Meanings of the Noble Qur'an - Amharic translation - Africa Academy * - Translations’ Index


Translation of the meanings Surah: An-Nisā’   Ayah:
۞ وَٱلۡمُحۡصَنَٰتُ مِنَ ٱلنِّسَآءِ إِلَّا مَا مَلَكَتۡ أَيۡمَٰنُكُمۡۖ كِتَٰبَ ٱللَّهِ عَلَيۡكُمۡۚ وَأُحِلَّ لَكُم مَّا وَرَآءَ ذَٰلِكُمۡ أَن تَبۡتَغُواْ بِأَمۡوَٰلِكُم مُّحۡصِنِينَ غَيۡرَ مُسَٰفِحِينَۚ فَمَا ٱسۡتَمۡتَعۡتُم بِهِۦ مِنۡهُنَّ فَـَٔاتُوهُنَّ أُجُورَهُنَّ فَرِيضَةٗۚ وَلَا جُنَاحَ عَلَيۡكُمۡ فِيمَا تَرَٰضَيۡتُم بِهِۦ مِنۢ بَعۡدِ ٱلۡفَرِيضَةِۚ إِنَّ ٱللَّهَ كَانَ عَلِيمًا حَكِيمٗا
24. ባል ያገቡ ሴቶችም በጦርነት እጆቻችሁ በምርኮ የያዟቸው ሲቀሩ (በእናንተ ላይ እርም ናቸው):: ይህን ህግ አላህ በእናንተ ላይ ደነገገ:: ከነዚህ ከተከለከሉት ሌላ ጥብቆች ሆናችሁና ዝሙተኞች ሳትሆኑ በገንዘባችሁ ጋብቻን ልትፈለጉ ለእናንተ ተፈቀደ:: እናም ከእነርሱም መገናኘት የተጠቀማችሁባቸውን ሴቶች መህሮቻቸውን ልትሰጧቸው ግዴታ ነው:: ከመወሰን በኋላ በተዋደዳችሁበት ነገር በእናንተ ላይ ኃጢአት የለም:: አላህ ሁሉን አዋቂና ጥበበኛ ነውና::
Arabic explanations of the Qur’an:
وَمَن لَّمۡ يَسۡتَطِعۡ مِنكُمۡ طَوۡلًا أَن يَنكِحَ ٱلۡمُحۡصَنَٰتِ ٱلۡمُؤۡمِنَٰتِ فَمِن مَّا مَلَكَتۡ أَيۡمَٰنُكُم مِّن فَتَيَٰتِكُمُ ٱلۡمُؤۡمِنَٰتِۚ وَٱللَّهُ أَعۡلَمُ بِإِيمَٰنِكُمۚ بَعۡضُكُم مِّنۢ بَعۡضٖۚ فَٱنكِحُوهُنَّ بِإِذۡنِ أَهۡلِهِنَّ وَءَاتُوهُنَّ أُجُورَهُنَّ بِٱلۡمَعۡرُوفِ مُحۡصَنَٰتٍ غَيۡرَ مُسَٰفِحَٰتٖ وَلَا مُتَّخِذَٰتِ أَخۡدَانٖۚ فَإِذَآ أُحۡصِنَّ فَإِنۡ أَتَيۡنَ بِفَٰحِشَةٖ فَعَلَيۡهِنَّ نِصۡفُ مَا عَلَى ٱلۡمُحۡصَنَٰتِ مِنَ ٱلۡعَذَابِۚ ذَٰلِكَ لِمَنۡ خَشِيَ ٱلۡعَنَتَ مِنكُمۡۚ وَأَن تَصۡبِرُواْ خَيۡرٞ لَّكُمۡۗ وَٱللَّهُ غَفُورٞ رَّحِيمٞ
25. (ወንዶች ሆይ!) ከናንተ መካከል ጥብቆች ምዕመናትን ለማግባት ሀብትን ያልቻለ ሰው እጆቻችሁ ንብረት ካደረጓቸው ከምዕመናት መካከል ወጣቶቻችሁን አገልጋዬች የመረጠውን ያግባ:: አላህ የውስጥ እምነታችሁን ምንነት አዋቂ ነውና:: ከፊላችሁ ከከፊሉ የተራባ ነው:: ባሮችንም ቢሆን እንደዚሁ በአሳዳሪዎቻቸው ፈቃድ ብቻ አግቧቸው:: መህሮቻቸውንም በመልካም መንገድ ስጧቸው:: ጥብቆች ሆነው ዝሙተኛ ያልሆኑ የስርቆሽ ወዳጅንም ያልያዙ እንደሆኑ አግቧቸው:: በማግባት በተጠበቁም ጊዜ መጥፎን ስራ ቢሰሩ በእነርሱ ላይ የተደነገገው ቅጣት በነፃዎቹ ላይ ከተደነገገው ቅጣት ግማሹ ቅጣት አለባቸው:: ያ ከናንተ መካከል ዝሙትን ለፈራ ብቻ ነው:: መታገሳችሁ የተሻለ ነው:: አላህ መሀሪና አዛኝ ነውና።
Arabic explanations of the Qur’an:
يُرِيدُ ٱللَّهُ لِيُبَيِّنَ لَكُمۡ وَيَهۡدِيَكُمۡ سُنَنَ ٱلَّذِينَ مِن قَبۡلِكُمۡ وَيَتُوبَ عَلَيۡكُمۡۗ وَٱللَّهُ عَلِيمٌ حَكِيمٞ
26. (አማኞች ሆይ!) አላህ የሃይማኖታችሁን ህግጋት ሊያብራራላችሁ፤ ከናንተ በፊትም የነበሩትን ነብያት ፈለጎች ሊመራችሁ፤ በእናንተም ላይ ጸጸትን ሊቀበል ይሻል:: አላህ ሁሉን አዋቂና ጥበበኛ ነው::
Arabic explanations of the Qur’an:
 
Translation of the meanings Surah: An-Nisā’
Surahs’ Index Page Number
 
Translation of the Meanings of the Noble Qur'an - Amharic translation - Africa Academy - Translations’ Index

Translated by Muhammad Zain Zahruddin. Published by Africa Academy

close