Check out the new design

Traducción de los significados del Sagrado Corán - Traducción al amárico - Academia de África * - Índice de traducciones


Traducción de significados Capítulo: Al-Israa   Versículo:
وَإِن كَادُواْ لَيَسۡتَفِزُّونَكَ مِنَ ٱلۡأَرۡضِ لِيُخۡرِجُوكَ مِنۡهَاۖ وَإِذٗا لَّا يَلۡبَثُونَ خِلَٰفَكَ إِلَّا قَلِيلٗا
76. ከምድሪቱ (ከዓረብ) ምድር ከእርሷ ያወጡህ ዘንድ ሊያሸብሩህ በእርግጥ ተቃረቡ:: ያን ጊዜም ካንተ በኋላ ጥቂትን ጊዜ እንጂ አይቆዩም ነበር::
Las Exégesis Árabes:
سُنَّةَ مَن قَدۡ أَرۡسَلۡنَا قَبۡلَكَ مِن رُّسُلِنَاۖ وَلَا تَجِدُ لِسُنَّتِنَا تَحۡوِيلًا
77. (መልዕክተኛችን ሙሐመድ ሆይ!) ከመልዕክተኞቻችን ካንተ በፊት በእርግጥ እንደ ላክናቸው ሰዎች ልማድ ብጤ ይጠፋ ነበር፤ ለልማዳችንም መለወጥን አታገኝም (አይለወጥም)።
Las Exégesis Árabes:
أَقِمِ ٱلصَّلَوٰةَ لِدُلُوكِ ٱلشَّمۡسِ إِلَىٰ غَسَقِ ٱلَّيۡلِ وَقُرۡءَانَ ٱلۡفَجۡرِۖ إِنَّ قُرۡءَانَ ٱلۡفَجۡرِ كَانَ مَشۡهُودٗا
78. ሶላትን ከጸሐይ መዘንበል እስከ ሌሊት ጨለማ ድረስ ስገድ:: የጎህንም ሶላት ስገድ:: የጎህ ሶላት መላዕክት የሚገኙበት ነውና::
Las Exégesis Árabes:
وَمِنَ ٱلَّيۡلِ فَتَهَجَّدۡ بِهِۦ نَافِلَةٗ لَّكَ عَسَىٰٓ أَن يَبۡعَثَكَ رَبُّكَ مَقَامٗا مَّحۡمُودٗا
79. (መልዕክተኛችን ሙሐመድ ሆይ!) ከሌሊት ላንተ ተጨማሪ የሆነችን ሶላት በቁርኣን ስገድ:: ጌታህ ምስጉን በሆነ ስፍራ በእርግጥ ያቆምሃልና::
Las Exégesis Árabes:
وَقُل رَّبِّ أَدۡخِلۡنِي مُدۡخَلَ صِدۡقٖ وَأَخۡرِجۡنِي مُخۡرَجَ صِدۡقٖ وَٱجۡعَل لِّي مِن لَّدُنكَ سُلۡطَٰنٗا نَّصِيرٗا
80. (መልዕክተኛችን ሙሐመድ ሆይ!) በልም: «ጌታዬ ሆይ! የተወደደን መግባት አስገባኝ፤ የተወደደንም መውጣት አስወጣኝ:: ለእኔም ካንተ ዘንድ የተረዳን ስልጣን አድርግልኝ።»
Las Exégesis Árabes:
وَقُلۡ جَآءَ ٱلۡحَقُّ وَزَهَقَ ٱلۡبَٰطِلُۚ إِنَّ ٱلۡبَٰطِلَ كَانَ زَهُوقٗا
81. (መልዕክተኛችን ሙሐመድ ሆይ!) «እውነት መጣ ውሸትም ተወገደ፤ እነሆ ውሸት ተወጋጅ ነውና።» በል።
Las Exégesis Árabes:
وَنُنَزِّلُ مِنَ ٱلۡقُرۡءَانِ مَا هُوَ شِفَآءٞ وَرَحۡمَةٞ لِّلۡمُؤۡمِنِينَ وَلَا يَزِيدُ ٱلظَّٰلِمِينَ إِلَّا خَسَارٗا
82. ከቁርኣን ለአማኞች መድሓኒትና እዝነት የሆነን እናወርዳለን በዳዮችንም ኪሳራን እንጂ ሌላ አይጨምርላቸዉም::
Las Exégesis Árabes:
وَإِذَآ أَنۡعَمۡنَا عَلَى ٱلۡإِنسَٰنِ أَعۡرَضَ وَنَـَٔا بِجَانِبِهِۦ وَإِذَا مَسَّهُ ٱلشَّرُّ كَانَ يَـُٔوسٗا
83. በሰዉም ላይ ጸጋችንን በለገስን ጊዜ ከምስጋና ይዞራል ጎኑንም ከእውነት ያርቃል:: ችግርም በነካው ጊዜ ተስፋ ቆራጭ ይሆናል::
Las Exégesis Árabes:
قُلۡ كُلّٞ يَعۡمَلُ عَلَىٰ شَاكِلَتِهِۦ فَرَبُّكُمۡ أَعۡلَمُ بِمَنۡ هُوَ أَهۡدَىٰ سَبِيلٗا
84. (መልዕክተኛችን ሙሐመድ ሆይ!) «ሁሉም በሚመስለው መንገድ ላይ ይሠራል:: ጌታችሁም እርሱ መንገዱ ቀጥተኛ የሆነውን አዋቂ ነው።» በላቸው።
Las Exégesis Árabes:
وَيَسۡـَٔلُونَكَ عَنِ ٱلرُّوحِۖ قُلِ ٱلرُّوحُ مِنۡ أَمۡرِ رَبِّي وَمَآ أُوتِيتُم مِّنَ ٱلۡعِلۡمِ إِلَّا قَلِيلٗا
85. (መልዕክተኛችን ሙሐመድ ሆይ!) ከሓዲያን ከሩህ ይጠይቁሃል። «ሩህ ከጌታዬ ነገር ነው:: ከእውቀትም ጥቂትን እንጂ አልተሰጣችሁም።» በላቸው::
Las Exégesis Árabes:
وَلَئِن شِئۡنَا لَنَذۡهَبَنَّ بِٱلَّذِيٓ أَوۡحَيۡنَآ إِلَيۡكَ ثُمَّ لَا تَجِدُ لَكَ بِهِۦ عَلَيۡنَا وَكِيلًا
86. (መልዕክተኛችን ሙሐመድ ሆይ!) ብንሻ ያንን ወደ አንተ ያወረድነውን በእርግጥ እንወስድብሃለን:: ከዚያም ላንተ በእኛ ላይ በእርሱ ለማስመለስ ተያዢን አታገኝም::
Las Exégesis Árabes:
 
Traducción de significados Capítulo: Al-Israa
Índice de Capítulos Número de página
 
Traducción de los significados del Sagrado Corán - Traducción al amárico - Academia de África - Índice de traducciones

Traducida por Muhammad Zain Zuhar Al-Din. Publicada por la Academia de África.

Cerrar