Check out the new design

Traducción de los significados del Sagrado Corán - Traducción al amárico - Academia de África * - Índice de traducciones

PDF XML CSV Excel API
Please review the Terms and Policies

Traducción de significados Capítulo: Al-Anbiyaa   Versículo:
وَإِذَا رَءَاكَ ٱلَّذِينَ كَفَرُوٓاْ إِن يَتَّخِذُونَكَ إِلَّا هُزُوًا أَهَٰذَا ٱلَّذِي يَذۡكُرُ ءَالِهَتَكُمۡ وَهُم بِذِكۡرِ ٱلرَّحۡمَٰنِ هُمۡ كَٰفِرُونَ
36. (መልዕክተኛችን ሙሐመድ ሆይ!) እነዚያም በአላህ የካዱት ሰዎች ባዩህ ጊዜ መሳለቂያ አድርገው እንጂ አይዙህም። እነርሱ በአር-ረህማን መወሳት እነርሱ ከሓዲያን ሲሆኑ: «ያ አማልክቶቻችሁን በክፉ የሚያነሳቸው ይህ ነውን?» ይላሉ።
Las Exégesis Árabes:
خُلِقَ ٱلۡإِنسَٰنُ مِنۡ عَجَلٖۚ سَأُوْرِيكُمۡ ءَايَٰتِي فَلَا تَسۡتَعۡجِلُونِ
37. ሰው ቸኳይ ሆኖ ተፈጠረ:: ታዓምራቶቼን በእርግጥ አሳያችኋለሁና አታቻኩሉኝ::
Las Exégesis Árabes:
وَيَقُولُونَ مَتَىٰ هَٰذَا ٱلۡوَعۡدُ إِن كُنتُمۡ صَٰدِقِينَ
38. «እውነተኞች ከሆናቸሁ ይህ ቀጠሮም መቼ ነው?» ይላሉ።
Las Exégesis Árabes:
لَوۡ يَعۡلَمُ ٱلَّذِينَ كَفَرُواْ حِينَ لَا يَكُفُّونَ عَن وُجُوهِهِمُ ٱلنَّارَ وَلَا عَن ظُهُورِهِمۡ وَلَا هُمۡ يُنصَرُونَ
39.እነዚያ በአላህ የካዱ ሰዎች ከፊቶቻቸውና ከጀርቦቻቸው ላይ እሳትን የማይከለክሉበትን እነርሱም የማይረዳዱበትን ጊዜ ቢያውቁ ኖሮ ይህንን አይሉም ነበር::
Las Exégesis Árabes:
بَلۡ تَأۡتِيهِم بَغۡتَةٗ فَتَبۡهَتُهُمۡ فَلَا يَسۡتَطِيعُونَ رَدَّهَا وَلَا هُمۡ يُنظَرُونَ
40. ይልቁንም ሰዓቲቱ በድንገት ትመጣቸዋለች:: ታስደነግጣቸዋለችም:: መመለሷንም አይችሉም:: እነርሱም የሚቆይላቸው አይደሉም።
Las Exégesis Árabes:
وَلَقَدِ ٱسۡتُهۡزِئَ بِرُسُلٖ مِّن قَبۡلِكَ فَحَاقَ بِٱلَّذِينَ سَخِرُواْ مِنۡهُم مَّا كَانُواْ بِهِۦ يَسۡتَهۡزِءُونَ
41. (መልዕክተኛችን ሙሐመድ ሆይ!) ካንተ በፊትም የነበሩት መልዕክተኞች በእርግጥ ተቀለደባቸው፤ በእነዚያ ከእነርሱ ይቀልዱ በነበሩት ይሳለቁበት የነበሩት ቅጣት ሰፈረባቸው።
Las Exégesis Árabes:
قُلۡ مَن يَكۡلَؤُكُم بِٱلَّيۡلِ وَٱلنَّهَارِ مِنَ ٱلرَّحۡمَٰنِۚ بَلۡ هُمۡ عَن ذِكۡرِ رَبِّهِم مُّعۡرِضُونَ
42. (መልዕክተኛችን ሙሐመድ ሆይ!) «ከአር-ረህማን ቅጣት በሌሊትና በቀን የሚጠብቃችሁ ማነው?» በላቸው:: በእውነቱ እነርሱ ከጌታቸው ግሠጼ ከቁርኣን ዘንጊዎች ናቸው::
Las Exégesis Árabes:
أَمۡ لَهُمۡ ءَالِهَةٞ تَمۡنَعُهُم مِّن دُونِنَاۚ لَا يَسۡتَطِيعُونَ نَصۡرَ أَنفُسِهِمۡ وَلَا هُم مِّنَّا يُصۡحَبُونَ
43.ለእነርሱ ከእኛ ሌላ የምትከላከልላቸው አማልዕክት አለቻቸውን? ነፍሶቻቸውን መርዳትን አይችሉም:: እነርሱም (ከሓዲያኑ) ከእኛ አይጠብቁም።
Las Exégesis Árabes:
بَلۡ مَتَّعۡنَا هَٰٓؤُلَآءِ وَءَابَآءَهُمۡ حَتَّىٰ طَالَ عَلَيۡهِمُ ٱلۡعُمُرُۗ أَفَلَا يَرَوۡنَ أَنَّا نَأۡتِي ٱلۡأَرۡضَ نَنقُصُهَا مِنۡ أَطۡرَافِهَآۚ أَفَهُمُ ٱلۡغَٰلِبُونَ
44.በእውነትም እነዚህንና አባቶቻቸውን በእነርሱ ላይ ዕድሜ እስከ ረዘመባቸው ድረስ አጣቀምናቸው:: ተታለሉም። እኛ ምድርን ከጫፎቿ የምናጎድላት ሆነን ስንመጣባት አያዩምን? እነርሱ አሸናፊዎች ናቸውን?
Las Exégesis Árabes:
 
Traducción de significados Capítulo: Al-Anbiyaa
Índice de Capítulos Número de página
 
Traducción de los significados del Sagrado Corán - Traducción al amárico - Academia de África - Índice de traducciones

Traducida por Muhammad Zain Zahr Ad-Din. Publicada por la Academia de África.

Cerrar