Check out the new design

Traducción de los significados del Sagrado Corán - Traducción al amárico - Academia de África * - Índice de traducciones


Traducción de significados Capítulo: Al-‘Imrán   Versículo:
وَكَيۡفَ تَكۡفُرُونَ وَأَنتُمۡ تُتۡلَىٰ عَلَيۡكُمۡ ءَايَٰتُ ٱللَّهِ وَفِيكُمۡ رَسُولُهُۥۗ وَمَن يَعۡتَصِم بِٱللَّهِ فَقَدۡ هُدِيَ إِلَىٰ صِرَٰطٖ مُّسۡتَقِيمٖ
101. የአላህ አናቅጽ በእናንተ ላይ እየተነበቡና መልዕክተኛዉም በመካከላችሁ እያለ እንዴት ትክዳላችሁ? በአላህ የሚጠበቅ ሰው ሁሉ ወደ ቀጥተኛው መንገድ በእርግጥ ተመራ::
Las Exégesis Árabes:
يَٰٓأَيُّهَا ٱلَّذِينَ ءَامَنُواْ ٱتَّقُواْ ٱللَّهَ حَقَّ تُقَاتِهِۦ وَلَا تَمُوتُنَّ إِلَّا وَأَنتُم مُّسۡلِمُونَ
102. እናንተ ያመናችሁ ሆይ! አላህን ትክክለኛውን ፍራቻ ፍሩት። እናንተም ሙስሊሞች ሆናችሁ እንጂ አትሙቱ።
Las Exégesis Árabes:
وَٱعۡتَصِمُواْ بِحَبۡلِ ٱللَّهِ جَمِيعٗا وَلَا تَفَرَّقُواْۚ وَٱذۡكُرُواْ نِعۡمَتَ ٱللَّهِ عَلَيۡكُمۡ إِذۡ كُنتُمۡ أَعۡدَآءٗ فَأَلَّفَ بَيۡنَ قُلُوبِكُمۡ فَأَصۡبَحۡتُم بِنِعۡمَتِهِۦٓ إِخۡوَٰنٗا وَكُنتُمۡ عَلَىٰ شَفَا حُفۡرَةٖ مِّنَ ٱلنَّارِ فَأَنقَذَكُم مِّنۡهَاۗ كَذَٰلِكَ يُبَيِّنُ ٱللَّهُ لَكُمۡ ءَايَٰتِهِۦ لَعَلَّكُمۡ تَهۡتَدُونَ
103. (እናንተ ያመናችሁ ሆይ!) የአላህን ጠንካራ የእምነት ገመድም ሁላችሁም ያዙ:: አትለያዩም። ጠበኞች በነበራችሁ ጊዜ በእናንተ ላይ የዋለውን የአላህን ጸጋም አስታውሱ:: ይሀውም በልቦቻችሁ መካከል አስማማ በጸጋዉም ወንድማማቾች ሆናችሁ:: በእሳት ጉድጓድ አፋፍ ላይ የነበራችሁ ስትሆኑ ከእርሷም አዳናችሁ:: ወደ ቀጥተኛው መንገድ ትመሩ ዘንድ አላህ ለእናንተ አናቅጽን እንደዚሁ ያብራራል::
Las Exégesis Árabes:
وَلۡتَكُن مِّنكُمۡ أُمَّةٞ يَدۡعُونَ إِلَى ٱلۡخَيۡرِ وَيَأۡمُرُونَ بِٱلۡمَعۡرُوفِ وَيَنۡهَوۡنَ عَنِ ٱلۡمُنكَرِۚ وَأُوْلَٰٓئِكَ هُمُ ٱلۡمُفۡلِحُونَ
104. (እናንተ ያመናችሁ ሆይ!) ከናንተ መካከል ወደ በጎ ነገር የሚጠሩና በመልካም ስራ የሚያዙ፤ ከክፉ ነገርም የሚከለክሉ ቡድኖች ይኑሩ:: እነዚያ ከእሳት የሚድኑ እነርሱው ናቸው።
Las Exégesis Árabes:
وَلَا تَكُونُواْ كَٱلَّذِينَ تَفَرَّقُواْ وَٱخۡتَلَفُواْ مِنۢ بَعۡدِ مَا جَآءَهُمُ ٱلۡبَيِّنَٰتُۚ وَأُوْلَٰٓئِكَ لَهُمۡ عَذَابٌ عَظِيمٞ
105. (እናንተ ያመናችሁ ሆይ!) እንደነዚያ ግልጽ ተዐምራት ከመጣላቸው በኋላ እንደተለያዩትና እንደተጨቃጨቁት የመጽሐፉ ባለቤት ሰዎች አትሁኑ:: እነዚያም ለነርሱ ታላቅ ቅጣት አለባቸው::
Las Exégesis Árabes:
يَوۡمَ تَبۡيَضُّ وُجُوهٞ وَتَسۡوَدُّ وُجُوهٞۚ فَأَمَّا ٱلَّذِينَ ٱسۡوَدَّتۡ وُجُوهُهُمۡ أَكَفَرۡتُم بَعۡدَ إِيمَٰنِكُمۡ فَذُوقُواْ ٱلۡعَذَابَ بِمَا كُنتُمۡ تَكۡفُرُونَ
106.ያን ፊቶች የሚያበሩበትና ፊቶች የሚጠቁሩበትን የትንሳኤን ቀን አስታውሱ። እነዚያ ፊቶቻቸው የጠቆሩት ወገኖች «ከእምነታችሁ በኋላ ካዳችሁን? እግዲያዉስ ትክዱ የነበራችሁትን ነገር ቅጣቱን ቅመሱ።» ይባላሉ።
Las Exégesis Árabes:
وَأَمَّا ٱلَّذِينَ ٱبۡيَضَّتۡ وُجُوهُهُمۡ فَفِي رَحۡمَةِ ٱللَّهِۖ هُمۡ فِيهَا خَٰلِدُونَ
107. እነዚያ ፊቶቻቸው ያበሩት ወገኖች ደግሞ በአላህ ችሮታ ገነት ውስጥ ናቸው:: እነርሱ በውስጧ ዘወታሪዎች ናቸው::
Las Exégesis Árabes:
تِلۡكَ ءَايَٰتُ ٱللَّهِ نَتۡلُوهَا عَلَيۡكَ بِٱلۡحَقِّۗ وَمَا ٱللَّهُ يُرِيدُ ظُلۡمٗا لِّلۡعَٰلَمِينَ
108. እነኚህ ባንተ ላይ በእውነት የምናነባቸው የአላህ አናቅጽ ናቸው:: አላህም ለዓለማት በደልን የሚሻ አይደለም::
Las Exégesis Árabes:
 
Traducción de significados Capítulo: Al-‘Imrán
Índice de Capítulos Número de página
 
Traducción de los significados del Sagrado Corán - Traducción al amárico - Academia de África - Índice de traducciones

Traducida por Muhammad Zain Zuhar Al-Din. Publicada por la Academia de África.

Cerrar