Check out the new design

ترجمهٔ معانی قرآن کریم - ترجمه‌ى امهری ـ آکادمی آفریقا * - لیست ترجمه ها


ترجمهٔ معانی سوره: یونس   آیه:
وَلَوۡ أَنَّ لِكُلِّ نَفۡسٖ ظَلَمَتۡ مَا فِي ٱلۡأَرۡضِ لَٱفۡتَدَتۡ بِهِۦۗ وَأَسَرُّواْ ٱلنَّدَامَةَ لَمَّا رَأَوُاْ ٱلۡعَذَابَۖ وَقُضِيَ بَيۡنَهُم بِٱلۡقِسۡطِ وَهُمۡ لَا يُظۡلَمُونَ
54. ለበደለች ነፍስ ሁሉ በምድር ላይ ያለው ሀብት ሁሉ የእርሷ ቢሆንላት በእርግጥ ቤዛ ባደረገችው ነበር:: ቅጣቱንም ባዩ ጊዜ ጸጸትን ይደብቃሉ (ይገልጻሉ):: በመካከላቸዉም በትክክል ይፈረዳል:: እነርሱም ቅንጣት ያህል አይበደሉም::
تفسیرهای عربی:
أَلَآ إِنَّ لِلَّهِ مَا فِي ٱلسَّمَٰوَٰتِ وَٱلۡأَرۡضِۗ أَلَآ إِنَّ وَعۡدَ ٱللَّهِ حَقّٞ وَلَٰكِنَّ أَكۡثَرَهُمۡ لَا يَعۡلَمُونَ
55. አስተውሉ! በሰማያትና በምድር ያለው ሁሉ የአላህ ብቻ ነው:: አስተዉሉ! የአላህ የተስፋ ቃል እርግጥ ነው:: ግን አብዛኞቻቸው አያውቁም::
تفسیرهای عربی:
هُوَ يُحۡيِۦ وَيُمِيتُ وَإِلَيۡهِ تُرۡجَعُونَ
56. እርሱ ሕያው ያደርጋል:: ይገድላልም:: ወደ እርሱም ትመለሳላችሁ::
تفسیرهای عربی:
يَٰٓأَيُّهَا ٱلنَّاسُ قَدۡ جَآءَتۡكُم مَّوۡعِظَةٞ مِّن رَّبِّكُمۡ وَشِفَآءٞ لِّمَا فِي ٱلصُّدُورِ وَهُدٗى وَرَحۡمَةٞ لِّلۡمُؤۡمِنِينَ
57. ሰዎች ሆይ! ከጌታችሁ ዘንድ ግሳጼ በደረቶች ውስጥ ላለው በሽታም ፍቱን መድሀኒት፤ ለአማኞችም ብርሃንና እዝነት የሆነ መልዕክት በእርግጥ መጣላችሁ።
تفسیرهای عربی:
قُلۡ بِفَضۡلِ ٱللَّهِ وَبِرَحۡمَتِهِۦ فَبِذَٰلِكَ فَلۡيَفۡرَحُواْ هُوَ خَيۡرٞ مِّمَّا يَجۡمَعُونَ
58. (መልዕክተኛችን ሙሐመድ ሆይ!) «በአላህ ችሮታና በእዝነቱ ተደሰቱ:: በዚህም ምክንያት ይደሰቱ:: እርሱ ከሚሰበስቡት ሀብት ሁሉ በላጭ ነው።» በላቸው::
تفسیرهای عربی:
قُلۡ أَرَءَيۡتُم مَّآ أَنزَلَ ٱللَّهُ لَكُم مِّن رِّزۡقٖ فَجَعَلۡتُم مِّنۡهُ حَرَامٗا وَحَلَٰلٗا قُلۡ ءَآللَّهُ أَذِنَ لَكُمۡۖ أَمۡ عَلَى ٱللَّهِ تَفۡتَرُونَ
59. (መልዕክተኛችን ሙሐመድ ሆይ!) «አላህ ከሲሳይ ለእናንተ ያወረደው ከእርሱም ከፊሉን እርም ከፊሉን የተፈቀደ ያደረጋችሁትን አያችሁን?» በላቸው:: «አላህ ይህንን ለእናንተ ፈቀደላችሁን? ወይስ በአላህ ላይ ትቀጣጥፋላችሁ?» በላቸው::
تفسیرهای عربی:
وَمَا ظَنُّ ٱلَّذِينَ يَفۡتَرُونَ عَلَى ٱللَّهِ ٱلۡكَذِبَ يَوۡمَ ٱلۡقِيَٰمَةِۗ إِنَّ ٱللَّهَ لَذُو فَضۡلٍ عَلَى ٱلنَّاسِ وَلَٰكِنَّ أَكۡثَرَهُمۡ لَا يَشۡكُرُونَ
60. እነዚያ በአላህ ላይ ውሸትን የሚቀጣጥፉ ሰዎች በትንሳኤ ቀን በአላህ ጥርጣሬያቸው ምንድን ነው? አይቀጡም ይመስላቸዋልን? አላህ በሰዎች ላይ ቅጣትን ባለማቻኮል የልግስና ባለቤት ነው:: ግን አብዛኛዎቹ አያመሰግኑትም::
تفسیرهای عربی:
وَمَا تَكُونُ فِي شَأۡنٖ وَمَا تَتۡلُواْ مِنۡهُ مِن قُرۡءَانٖ وَلَا تَعۡمَلُونَ مِنۡ عَمَلٍ إِلَّا كُنَّا عَلَيۡكُمۡ شُهُودًا إِذۡ تُفِيضُونَ فِيهِۚ وَمَا يَعۡزُبُ عَن رَّبِّكَ مِن مِّثۡقَالِ ذَرَّةٖ فِي ٱلۡأَرۡضِ وَلَا فِي ٱلسَّمَآءِ وَلَآ أَصۡغَرَ مِن ذَٰلِكَ وَلَآ أَكۡبَرَ إِلَّا فِي كِتَٰبٖ مُّبِينٍ
61. (መልዕክተኛችን ሙሐመድ ሆይ!) በማንኛዉም ነገር ላይ አትሆንም፤ ከእርሱም ከቁርኣን ትንሽም አታነብም፤ ማንኛውንም ሥራ አንተም ሆንክ ሰዎቹ አትሠሩም፤ በገባችሁበት ጊዜ በናንተ ተግባር ላይ ተጠባባቂዎች ብንሆን እንጂ :: በምድርም ሆነ በሰማይ የብናኝ ክብደት ያክል እንኳን ከጌታህ እውቀት አይርቅም:: ከዚያም ያነሰም ሆነ የተለቀ ነገር በግልጹ መጽሐፍ ውስጥ የተጻፈ ቢሆን እንጂ የለም::
تفسیرهای عربی:
 
ترجمهٔ معانی سوره: یونس
فهرست سوره ها شماره صفحه
 
ترجمهٔ معانی قرآن کریم - ترجمه‌ى امهری ـ آکادمی آفریقا - لیست ترجمه ها

مترجم: محمد زین زهرالدین. آکادمی آفریقا آن را منتشر كرده است.

بستن