Check out the new design

ترجمهٔ معانی قرآن کریم - ترجمه‌ى امهری ـ آکادمی آفریقا * - لیست ترجمه ها


ترجمهٔ معانی سوره: یوسف   آیه:
قَالَ هَلۡ ءَامَنُكُمۡ عَلَيۡهِ إِلَّا كَمَآ أَمِنتُكُمۡ عَلَىٰٓ أَخِيهِ مِن قَبۡلُ فَٱللَّهُ خَيۡرٌ حَٰفِظٗاۖ وَهُوَ أَرۡحَمُ ٱلرَّٰحِمِينَ
64. «ከአሁን በፊት በወንድሙ ላይ እንዳመንኳችሁ እንጂ በእርሱ ላይ አምናችኋለሁን? አላህም በጠባቂነት ከሁሉ የበለጠ ነው:: እርሱም ከአዛኞች ሁሉ ይበልጥ አዛኝ ነው።» አላቸው።
تفسیرهای عربی:
وَلَمَّا فَتَحُواْ مَتَٰعَهُمۡ وَجَدُواْ بِضَٰعَتَهُمۡ رُدَّتۡ إِلَيۡهِمۡۖ قَالُواْ يَٰٓأَبَانَا مَا نَبۡغِيۖ هَٰذِهِۦ بِضَٰعَتُنَا رُدَّتۡ إِلَيۡنَاۖ وَنَمِيرُ أَهۡلَنَا وَنَحۡفَظُ أَخَانَا وَنَزۡدَادُ كَيۡلَ بَعِيرٖۖ ذَٰلِكَ كَيۡلٞ يَسِيرٞ
65. እቃቸውንም በከፈቱ ጊዜ ሸቀጣቸውን ወደ እነርሱ ተመልሶ አገኙት። «አባታችን ሆይ! ምን እንፈልጋለን? ይህች ሸቀጣችን ናት ወደ እኛ ተመልሳልናለች እንረዳባታለን:: ለቤተሰቦቻችንም እንሸምታለን። ወንድማችንንም እንጠብቃለን:: የአንድ ግመልን ጭነትም እንጨምራለን:: ይህ በንጉሱ ላይ ቀላል ስፍር ነው።» አሉ።
تفسیرهای عربی:
قَالَ لَنۡ أُرۡسِلَهُۥ مَعَكُمۡ حَتَّىٰ تُؤۡتُونِ مَوۡثِقٗا مِّنَ ٱللَّهِ لَتَأۡتُنَّنِي بِهِۦٓ إِلَّآ أَن يُحَاطَ بِكُمۡۖ فَلَمَّآ ءَاتَوۡهُ مَوۡثِقَهُمۡ قَالَ ٱللَّهُ عَلَىٰ مَا نَقُولُ وَكِيلٞ
66. «ካልተከበባችሁ በስተቀር እርሱን በእርግጥ የምታመጡልኝ ለመሆናችሁ ከአላህ የሆነን ቃልኪዳን (መተማመኛ) እስከምትሰጡኝ ድረስ ከናንተ ጋር ፈጽሞ አልከዉም።» አላቸው። መተማመኛቸውንም በሰጡ ጊዜ «አላህ በምንለው ሁሉ ላይ ዋስ ነው።» አላቸው።
تفسیرهای عربی:
وَقَالَ يَٰبَنِيَّ لَا تَدۡخُلُواْ مِنۢ بَابٖ وَٰحِدٖ وَٱدۡخُلُواْ مِنۡ أَبۡوَٰبٖ مُّتَفَرِّقَةٖۖ وَمَآ أُغۡنِي عَنكُم مِّنَ ٱللَّهِ مِن شَيۡءٍۖ إِنِ ٱلۡحُكۡمُ إِلَّا لِلَّهِۖ عَلَيۡهِ تَوَكَّلۡتُۖ وَعَلَيۡهِ فَلۡيَتَوَكَّلِ ٱلۡمُتَوَكِّلُونَ
67. አለም፡- «ልጆቼ ሆይ! በአንድ በር አትግቡ:: ግን በተለያዩ በሮች ግቡ:: ከአላህም ፍርድ በምንም አልጠቅማችሁም (አልመልስላችሁም)። ፍርዱ የአላህ እንጂ የሌላ አይደለም:: በእርሱ ላይ ብቻ ተመካሁ:: ተመኪዎችም ሁሉ በእርሱ ላይ ብቻ ይመኩ።»
تفسیرهای عربی:
وَلَمَّا دَخَلُواْ مِنۡ حَيۡثُ أَمَرَهُمۡ أَبُوهُم مَّا كَانَ يُغۡنِي عَنۡهُم مِّنَ ٱللَّهِ مِن شَيۡءٍ إِلَّا حَاجَةٗ فِي نَفۡسِ يَعۡقُوبَ قَضَىٰهَاۚ وَإِنَّهُۥ لَذُو عِلۡمٖ لِّمَا عَلَّمۡنَٰهُ وَلَٰكِنَّ أَكۡثَرَ ٱلنَّاسِ لَا يَعۡلَمُونَ
68. አባታቸው ካዘዛቸው ስፍራ በገቡ ጊዜ ከአላህ ፍርድ ምንም ነገር ከእነርሱ የሚከለክልላቸው አልነበረም:: ግን በየዕቁብ ነፍስ ውስጥ የነበረች ጉዳይ ናት:: ፈጸማት። እርሱም ስላሳወቅነው የእውቀት ባለቤት ነው። ግን አብዛኞቹ ሰዎች አያውቁም::
تفسیرهای عربی:
وَلَمَّا دَخَلُواْ عَلَىٰ يُوسُفَ ءَاوَىٰٓ إِلَيۡهِ أَخَاهُۖ قَالَ إِنِّيٓ أَنَا۠ أَخُوكَ فَلَا تَبۡتَئِسۡ بِمَا كَانُواْ يَعۡمَلُونَ
69. በዩሱፍ ላይ በገቡ ጊዜም ወንድሙን ወደ እርሱ አስጠጋውና «እነሆ እኔ ወንድምህ ነኝ:: ይሰሩት በነበሩትም ሁሉ አትበሳጭ።» አለው።
تفسیرهای عربی:
 
ترجمهٔ معانی سوره: یوسف
فهرست سوره ها شماره صفحه
 
ترجمهٔ معانی قرآن کریم - ترجمه‌ى امهری ـ آکادمی آفریقا - لیست ترجمه ها

مترجم: محمد زین زهرالدین. آکادمی آفریقا آن را منتشر كرده است.

بستن