Check out the new design

ترجمهٔ معانی قرآن کریم - ترجمه‌ى امهری ـ آکادمی آفریقا * - لیست ترجمه ها

PDF XML CSV Excel API
Please review the Terms and Policies

ترجمهٔ معانی سوره: آل عمران   آیه:
وَإِنَّ مِنۡهُمۡ لَفَرِيقٗا يَلۡوُۥنَ أَلۡسِنَتَهُم بِٱلۡكِتَٰبِ لِتَحۡسَبُوهُ مِنَ ٱلۡكِتَٰبِ وَمَا هُوَ مِنَ ٱلۡكِتَٰبِ وَيَقُولُونَ هُوَ مِنۡ عِندِ ٱللَّهِ وَمَا هُوَ مِنۡ عِندِ ٱللَّهِۖ وَيَقُولُونَ عَلَى ٱللَّهِ ٱلۡكَذِبَ وَهُمۡ يَعۡلَمُونَ
78. ከእነርሱም መካከል ከመጽሐፉ ያልሆነን ነገር ከመጽሐፉ አካል መሆኑን እንድታስቡ በመጽሐፉ ምላሶቻቸውን የሚያጣምሙም አሉ:: እርሱ ከአላህ ዘንድ ያልመጣ (ያልወረደ) ሲሆን «ከአላህ ዘንድ የመጣ (የወረደ) ነው።» ይላሉ። የሚያውቁ ሲሆኑ በአላህ ላይ ውሸትን ይናገራሉ።
تفسیرهای عربی:
مَا كَانَ لِبَشَرٍ أَن يُؤۡتِيَهُ ٱللَّهُ ٱلۡكِتَٰبَ وَٱلۡحُكۡمَ وَٱلنُّبُوَّةَ ثُمَّ يَقُولَ لِلنَّاسِ كُونُواْ عِبَادٗا لِّي مِن دُونِ ٱللَّهِ وَلَٰكِن كُونُواْ رَبَّٰنِيِّـۧنَ بِمَا كُنتُمۡ تُعَلِّمُونَ ٱلۡكِتَٰبَ وَبِمَا كُنتُمۡ تَدۡرُسُونَ
79. ለማንም ሰው አላህ መጽሐፍን፣ ጥበብንና ነብይነትን ሰጥቶት ከዚያ ለሰዎች «ከአላህ ሌላ ለእኔ ባሮች ሁኑ።» ሊል አይገባዉም:: ይልቁንም «መጽሐፉን የምታስተምሩና የምታጠኑ በነበራችሁበት በእውቀታችሁ ለራሳችሁ ተግባሪዎች ሁኑ።» ይላቸዋል።
تفسیرهای عربی:
وَلَا يَأۡمُرَكُمۡ أَن تَتَّخِذُواْ ٱلۡمَلَٰٓئِكَةَ وَٱلنَّبِيِّـۧنَ أَرۡبَابًاۚ أَيَأۡمُرُكُم بِٱلۡكُفۡرِ بَعۡدَ إِذۡ أَنتُم مُّسۡلِمُونَ
80. መላዕክትንና ነብያትንም አማልክት አድርጋችሁ እንድትይዙ ሊያዛችሁ አይገባም:: (እናንተ) ሙስሊሞች ከሆናችሁ በኋላ በክህደት ያዛችኋልን?
تفسیرهای عربی:
وَإِذۡ أَخَذَ ٱللَّهُ مِيثَٰقَ ٱلنَّبِيِّـۧنَ لَمَآ ءَاتَيۡتُكُم مِّن كِتَٰبٖ وَحِكۡمَةٖ ثُمَّ جَآءَكُمۡ رَسُولٞ مُّصَدِّقٞ لِّمَا مَعَكُمۡ لَتُؤۡمِنُنَّ بِهِۦ وَلَتَنصُرُنَّهُۥۚ قَالَ ءَأَقۡرَرۡتُمۡ وَأَخَذۡتُمۡ عَلَىٰ ذَٰلِكُمۡ إِصۡرِيۖ قَالُوٓاْ أَقۡرَرۡنَاۚ قَالَ فَٱشۡهَدُواْ وَأَنَا۠ مَعَكُم مِّنَ ٱلشَّٰهِدِينَ
81. (መልዕክተኛችን ሙሐመድ ሆይ!) «መጽሐፍንና ጥበብን ሰጥቻችሁ ከዚያ ከናንተ ጋር ላለው መጽሀፍ የሚያረጋግጥ መልዕክተኛ ቢመጣላችሁ በእርሱ እንድታምኑበት እንድትረዱትም።» ሲል አላህ የነቢያትን ቃል ኪዳን በያዘ ጊዜ (የነበረውን ክስተት ለህዝቦችህ አስታውስ)። «አረጋገጣችሁን? በዚህስ ላይ ቃል ኪዳኔን ያዛችሁን?» አላቸው። እነርሱም «አዎ አረጋገጥን» አሉ። «እንግዲያውስ መስክሩ:: እኔም ከናንተ ጋር ከመስካሪዎቹ ነኝ።» አላቸው።
تفسیرهای عربی:
فَمَن تَوَلَّىٰ بَعۡدَ ذَٰلِكَ فَأُوْلَٰٓئِكَ هُمُ ٱلۡفَٰسِقُونَ
82. እናም ከዚህ በኋላ የሸሹ አመጸኞቹ እነርሱ ብቻ ናቸው።
تفسیرهای عربی:
أَفَغَيۡرَ دِينِ ٱللَّهِ يَبۡغُونَ وَلَهُۥٓ أَسۡلَمَ مَن فِي ٱلسَّمَٰوَٰتِ وَٱلۡأَرۡضِ طَوۡعٗا وَكَرۡهٗا وَإِلَيۡهِ يُرۡجَعُونَ
83. በሰማያትና በምድር ያሉ ሁሉ በውድም ሆነ በግድ ለእርሱ የታዘዙና ወደ እርሱ የሚመለሱ ሲሆኑ (ከሓዲያን) ከአላህ ሃይማኖት ሌላን ይፈልጋሉን?
تفسیرهای عربی:
 
ترجمهٔ معانی سوره: آل عمران
فهرست سوره ها شماره صفحه
 
ترجمهٔ معانی قرآن کریم - ترجمه‌ى امهری ـ آکادمی آفریقا - لیست ترجمه ها

مترجم: محمد زین زهرالدین. آکادمی آفریقا آن را منتشر كرده است.

بستن