Check out the new design

ترجمهٔ معانی قرآن کریم - ترجمه‌ى امهری ـ آکادمی آفریقا * - لیست ترجمه ها


ترجمهٔ معانی سوره: غافر   آیه:
قَالُوٓاْ أَوَلَمۡ تَكُ تَأۡتِيكُمۡ رُسُلُكُم بِٱلۡبَيِّنَٰتِۖ قَالُواْ بَلَىٰۚ قَالُواْ فَٱدۡعُواْۗ وَمَا دُعَٰٓؤُاْ ٱلۡكَٰفِرِينَ إِلَّا فِي ضَلَٰلٍ
50. ዘበኞቹም «መልዕክተኞቻችሁ በታዐምራቶች ይመጡላችሁ አልነበሩምን?» ይላሉ ከሓዲያንም «እንዴታ መጥተውልናል እንጅ፤ ግን አሰተባበልናቸው።» ይላሉ። «እንግዲያውስ ጸልዩ የከሓዲያንም ጸሎት በከንቱ እንጂ አይደለም።» ይሏቸዋል፡:
تفسیرهای عربی:
إِنَّا لَنَنصُرُ رُسُلَنَا وَٱلَّذِينَ ءَامَنُواْ فِي ٱلۡحَيَوٰةِ ٱلدُّنۡيَا وَيَوۡمَ يَقُومُ ٱلۡأَشۡهَٰدُ
51. እኛ መልክተኞቻችንን እነዚያንም ያመኑትን በቅርቢቱ ሕይወትም ምስክሮች በሚቆሙበት ቀንም በእርግጥ እንረዳለን።
تفسیرهای عربی:
يَوۡمَ لَا يَنفَعُ ٱلظَّٰلِمِينَ مَعۡذِرَتُهُمۡۖ وَلَهُمُ ٱللَّعۡنَةُ وَلَهُمۡ سُوٓءُ ٱلدَّارِ
52. በደለኞችን ምክንያታቸው በማይጠቅማቸው ቀን እንረዳለን። ለነርሱም ርግማን አላቸው:: ለነርሱም መጥፎ አገር አላቸው::
تفسیرهای عربی:
وَلَقَدۡ ءَاتَيۡنَا مُوسَى ٱلۡهُدَىٰ وَأَوۡرَثۡنَا بَنِيٓ إِسۡرَٰٓءِيلَ ٱلۡكِتَٰبَ
53. ሙሳንም መምሪያ በእርግጥ ሰጠነው:: የኢስራኢልንም ልጆች መጽሐፍን አወረስናቸው::
تفسیرهای عربی:
هُدٗى وَذِكۡرَىٰ لِأُوْلِي ٱلۡأَلۡبَٰبِ
54. ለባለ አእምሮዎች መሪና ገሳጭ ሲሆን፤
تفسیرهای عربی:
فَٱصۡبِرۡ إِنَّ وَعۡدَ ٱللَّهِ حَقّٞ وَٱسۡتَغۡفِرۡ لِذَنۢبِكَ وَسَبِّحۡ بِحَمۡدِ رَبِّكَ بِٱلۡعَشِيِّ وَٱلۡإِبۡكَٰرِ
55. (መልዕክተኛችን ሙሐመድ ሆይ!) ታገስም የአላህ ተስፋ እውነት ነውና፤ ለስህተትህም ምህረትን ለምን፤ ከቀትር በኋላም በማለዳም ጌታህን ከማመስገን ጋር አጥራው::
تفسیرهای عربی:
إِنَّ ٱلَّذِينَ يُجَٰدِلُونَ فِيٓ ءَايَٰتِ ٱللَّهِ بِغَيۡرِ سُلۡطَٰنٍ أَتَىٰهُمۡ إِن فِي صُدُورِهِمۡ إِلَّا كِبۡرٞ مَّا هُم بِبَٰلِغِيهِۚ فَٱسۡتَعِذۡ بِٱللَّهِۖ إِنَّهُۥ هُوَ ٱلسَّمِيعُ ٱلۡبَصِيرُ
56. እነዚያ የመጣላቸው አስረጅ ሳይኖር በአላህ አናቅጽ የሚከራከሩ በልቦቻቸው ውስጥ እነርሱ ደራሾች ያልሆኑት ኩራት ብቻ እንጂ ምንም የለም:: በአላህም ብቻ ተጠበቅ፤ እነሆ እርሱ ሁሉን ሰሚና ሁሉን ተመልካች ነውና::
تفسیرهای عربی:
لَخَلۡقُ ٱلسَّمَٰوَٰتِ وَٱلۡأَرۡضِ أَكۡبَرُ مِنۡ خَلۡقِ ٱلنَّاسِ وَلَٰكِنَّ أَكۡثَرَ ٱلنَّاسِ لَا يَعۡلَمُونَ
57. ሰማያትንና ምድርን መፍጠር ሰዎችን ከመፍጠር ይልቅ ታላቅ ነው:: ግን አብዛሀኞቹ ሰዎች አያውቁም::
تفسیرهای عربی:
وَمَا يَسۡتَوِي ٱلۡأَعۡمَىٰ وَٱلۡبَصِيرُ وَٱلَّذِينَ ءَامَنُواْ وَعَمِلُواْ ٱلصَّٰلِحَٰتِ وَلَا ٱلۡمُسِيٓءُۚ قَلِيلٗا مَّا تَتَذَكَّرُونَ
58. ዐይነ ስዉርና የሚያይ እነዚያም አምነው መልካሞችን የሰሩትና መጥፎ ሰሪው አይስተካከሉም። በጣም ጥቂትን ብቻ ትገስፃላችሁ::
تفسیرهای عربی:
 
ترجمهٔ معانی سوره: غافر
فهرست سوره ها شماره صفحه
 
ترجمهٔ معانی قرآن کریم - ترجمه‌ى امهری ـ آکادمی آفریقا - لیست ترجمه ها

مترجم: محمد زین زهرالدین. آکادمی آفریقا آن را منتشر كرده است.

بستن