ترجمهٔ معانی قرآن کریم - الترجمة الأمهرية - زين * - لیست ترجمه ها


ترجمهٔ معانی سوره: سوره فتح   آیه:

ሱረቱ አል ፈትህ

إِنَّا فَتَحۡنَا لَكَ فَتۡحٗا مُّبِينٗا
1. (መልዕክተኛችን ሙሐመድ ሆይ!) እኛ ላንተ (መካን) በመክፈት ግልጽ የሆነን ድል ለገስንህ።
تفسیرهای عربی:
لِّيَغۡفِرَ لَكَ ٱللَّهُ مَا تَقَدَّمَ مِن ذَنۢبِكَ وَمَا تَأَخَّرَ وَيُتِمَّ نِعۡمَتَهُۥ عَلَيۡكَ وَيَهۡدِيَكَ صِرَٰطٗا مُّسۡتَقِيمٗا
2. አላህ ያለፈውንና የሚመጣውን ኃጢአትክን ሊምርህ፤ ፀጋውንም ባንተ ላይ ሊሞላና ቀጥተኛዉን መንገድ ሊመራህ፤
تفسیرهای عربی:
وَيَنصُرَكَ ٱللَّهُ نَصۡرًا عَزِيزًا
3. አላህም ብርቱን እርዳታ ሊረዳህ መካን ከፈተልህ::
تفسیرهای عربی:
هُوَ ٱلَّذِيٓ أَنزَلَ ٱلسَّكِينَةَ فِي قُلُوبِ ٱلۡمُؤۡمِنِينَ لِيَزۡدَادُوٓاْ إِيمَٰنٗا مَّعَ إِيمَٰنِهِمۡۗ وَلِلَّهِ جُنُودُ ٱلسَّمَٰوَٰتِ وَٱلۡأَرۡضِۚ وَكَانَ ٱللَّهُ عَلِيمًا حَكِيمٗا
4. አላህ ያ በአማኞች ልቦች ውስጥ ከእምነታቸው ጋር እምነትን ይጨምሩ ዘንድ እርጋታን ያወረደ ነው:: አላህ የሰማይና የምድር ስራዊት ሁሉ የሱ ብቻ ነው:: አላህ ሁሉን አዋቂና ጥበበኛ ነው::
تفسیرهای عربی:
لِّيُدۡخِلَ ٱلۡمُؤۡمِنِينَ وَٱلۡمُؤۡمِنَٰتِ جَنَّٰتٖ تَجۡرِي مِن تَحۡتِهَا ٱلۡأَنۡهَٰرُ خَٰلِدِينَ فِيهَا وَيُكَفِّرَ عَنۡهُمۡ سَيِّـَٔاتِهِمۡۚ وَكَانَ ذَٰلِكَ عِندَ ٱللَّهِ فَوۡزًا عَظِيمٗا
5. ወንድ አማኞችና ሴት ምዕመናትን በስሮቻቸው ወንዞች የሚፈሱባቸውን ገነቶች በውስጣቸው ዘወታሪዎች ሲሆኑ ሊያስገባቸው፤ ከነርሱም ሐጢያቶቻቸዉን ሊያብስላቸው (መካን ከፈተልህ):: ይህም ከአላህ ዘንድ የሆነ ታላቅ መታደል ነው::
تفسیرهای عربی:
وَيُعَذِّبَ ٱلۡمُنَٰفِقِينَ وَٱلۡمُنَٰفِقَٰتِ وَٱلۡمُشۡرِكِينَ وَٱلۡمُشۡرِكَٰتِ ٱلظَّآنِّينَ بِٱللَّهِ ظَنَّ ٱلسَّوۡءِۚ عَلَيۡهِمۡ دَآئِرَةُ ٱلسَّوۡءِۖ وَغَضِبَ ٱللَّهُ عَلَيۡهِمۡ وَلَعَنَهُمۡ وَأَعَدَّ لَهُمۡ جَهَنَّمَۖ وَسَآءَتۡ مَصِيرٗا
6. በአላህም ክፉ ጥርጣሬን ወንድ ተጣራጣሪ አስመሳዮችንና ሴት አስመሳዮችን ወንድ አጋሪዎችና ሴት አጋሪዎችን ያሰቃይም ዘንድ (በትግል አዘዘ):: በእነርሱ ላይ ክፉ ከባቢ አለባቸው:: በእነርሱ ላይ አላህ ተቆጣባቸው ረገማቸዉም:: ለእነርሱ ገሀነምን አዘጋጀላቸው:: ገሀነም መመለሻነቷም ከፋች::
تفسیرهای عربی:
وَلِلَّهِ جُنُودُ ٱلسَّمَٰوَٰتِ وَٱلۡأَرۡضِۚ وَكَانَ ٱللَّهُ عَزِيزًا حَكِيمًا
7. ለአላህ የሰማያትና የምድር ሰራዊቶች አሉት:: አላህ ሁሉን አሸናፊና ጥበበኛ ነው::
تفسیرهای عربی:
إِنَّآ أَرۡسَلۡنَٰكَ شَٰهِدٗا وَمُبَشِّرٗا وَنَذِيرٗا
8. (መልዕክተኛችን ሙሐመድ ሆይ!) እኛ መስካሪ፤ አብሳሪና አስፈራሪ አድርገን በእርግጥ ላክንህ::
تفسیرهای عربی:
لِّتُؤۡمِنُواْ بِٱللَّهِ وَرَسُولِهِۦ وَتُعَزِّرُوهُ وَتُوَقِّرُوهُۚ وَتُسَبِّحُوهُ بُكۡرَةٗ وَأَصِيلًا
9. በአላህ ልታምኑ። በመልዕክተኛዉም ልታምኑ፤ ልትረዱትና ልታከብሩት፤ አላህንም በጠዋትና ከቀትር በኋላ ልታወድሱት (ላክንህ)።
تفسیرهای عربی:
إِنَّ ٱلَّذِينَ يُبَايِعُونَكَ إِنَّمَا يُبَايِعُونَ ٱللَّهَ يَدُ ٱللَّهِ فَوۡقَ أَيۡدِيهِمۡۚ فَمَن نَّكَثَ فَإِنَّمَا يَنكُثُ عَلَىٰ نَفۡسِهِۦۖ وَمَنۡ أَوۡفَىٰ بِمَا عَٰهَدَ عَلَيۡهُ ٱللَّهَ فَسَيُؤۡتِيهِ أَجۡرًا عَظِيمٗا
10. (መልዕክተኛችን ሙሐመድ ሆይ!) እነዚያ ቃል ኪዳን የሚጋቡህ ቃል ኪዳን የሚጋቡት አላህን ብቻ ነው:: የአላህ እጅ ከእጆቻቸው በላይ ነው:: ያፈረሰም ሰው የሚያፈርሰው በነፍሱ ላይ ብቻ ነው:: በእርሱ ላይ አላህን ቃል ኪዳን የተጋባበትን የሞላ ሰው ታላቅ ምንዳ በእርግጥ ይሰጠዋል::
تفسیرهای عربی:
سَيَقُولُ لَكَ ٱلۡمُخَلَّفُونَ مِنَ ٱلۡأَعۡرَابِ شَغَلَتۡنَآ أَمۡوَٰلُنَا وَأَهۡلُونَا فَٱسۡتَغۡفِرۡ لَنَاۚ يَقُولُونَ بِأَلۡسِنَتِهِم مَّا لَيۡسَ فِي قُلُوبِهِمۡۚ قُلۡ فَمَن يَمۡلِكُ لَكُم مِّنَ ٱللَّهِ شَيۡـًٔا إِنۡ أَرَادَ بِكُمۡ ضَرًّا أَوۡ أَرَادَ بِكُمۡ نَفۡعَۢاۚ بَلۡ كَانَ ٱللَّهُ بِمَا تَعۡمَلُونَ خَبِيرَۢا
11. (መልዕክተኛችን ሙሐመድ ሆይ!) ከዐረብ ዘላኖች መካከል እነዚያ ከዘመቻ ወደ ኋላ የቀሩት «ገንዘቦቻችንና ቤተሰቦቻችን አስቸግረዉን ስለነበር ነውና (የቀረነው) ምህረትን ለምንልን» ይሉሃል:: በልቦቻቸው ውስጥ የሌለውን ነገር በምላሶቻቸው ይናገራሉ:: «አላህ እናንተን መጉዳትም ሆነ መጥቀም ቢፈልግ ከአላህ ለእናተ አንዳችን ለመከላከል የሚችል ማን ነው? በእውነቱ አላህ ለምትሰሩት ነገር ሁሉ ውስጠ አዋቂ ነው።» በላቸው።
تفسیرهای عربی:
بَلۡ ظَنَنتُمۡ أَن لَّن يَنقَلِبَ ٱلرَّسُولُ وَٱلۡمُؤۡمِنُونَ إِلَىٰٓ أَهۡلِيهِمۡ أَبَدٗا وَزُيِّنَ ذَٰلِكَ فِي قُلُوبِكُمۡ وَظَنَنتُمۡ ظَنَّ ٱلسَّوۡءِ وَكُنتُمۡ قَوۡمَۢا بُورٗا
12. ይልቁንም መልዕክተኛውና ምዕመናኖቹ ወደየቤተሰቦቻቸው ፈጽሞ አለመመለሳቸውን እርግጠኞች (ተጠራጣሪዎች) ስለነበራችሁ ነው። ይህም በልቦቻችሁ ውስጥ ተሸለመላችሁ:: መጥፎንም መጠርጠር ጠረጠራችሁ ጠፊዎች ህዝቦችም ሆናችሁ::
تفسیرهای عربی:
وَمَن لَّمۡ يُؤۡمِنۢ بِٱللَّهِ وَرَسُولِهِۦ فَإِنَّآ أَعۡتَدۡنَا لِلۡكَٰفِرِينَ سَعِيرٗا
13. በአላህና በመልዕክተኛው ላለመነ ሰው እኛ ለከሓዲያን እሳትን አዘጋጅተናል::
تفسیرهای عربی:
وَلِلَّهِ مُلۡكُ ٱلسَّمَٰوَٰتِ وَٱلۡأَرۡضِۚ يَغۡفِرُ لِمَن يَشَآءُ وَيُعَذِّبُ مَن يَشَآءُۚ وَكَانَ ٱللَّهُ غَفُورٗا رَّحِيمٗا
14. የሰማያትና የምድር ንግስና የአላህ ብቻ ነው:: የሚፈልገውን ወደ ቀናው ይመራል:: የሚፈልገውንም ሰው ይቀጣል:: አላህ መሀሪና አዛኝ ነውና::
تفسیرهای عربی:
سَيَقُولُ ٱلۡمُخَلَّفُونَ إِذَا ٱنطَلَقۡتُمۡ إِلَىٰ مَغَانِمَ لِتَأۡخُذُوهَا ذَرُونَا نَتَّبِعۡكُمۡۖ يُرِيدُونَ أَن يُبَدِّلُواْ كَلَٰمَ ٱللَّهِۚ قُل لَّن تَتَّبِعُونَا كَذَٰلِكُمۡ قَالَ ٱللَّهُ مِن قَبۡلُۖ فَسَيَقُولُونَ بَلۡ تَحۡسُدُونَنَاۚ بَلۡ كَانُواْ لَا يَفۡقَهُونَ إِلَّا قَلِيلٗا
15. ከጠላት የተማረኩትን ገንዘቦች ልትይዙ በሄዳችሁ ጊዜ እነዚያ ወደ ኋላ የቀሩት ሰዎች «ተውን እንከተላችሁ» ይሏችኋል:: በዚህም የአላህን ቃል ሊለውጡ ይፈልጋሉ:: «ፈጽሞ አትከተሉንም:: ልክ እንደዚሃችሁ ቃል የመሰለ ከዚህ በፊት አላህም ብሏል» በሏቸው:: «ይልቁንም ትመቀኙናላችሁ» ይላሉም:: በእውነት እነርሱም ጥቂትን እንጂ የማያውቁ ነበሩ::
تفسیرهای عربی:
قُل لِّلۡمُخَلَّفِينَ مِنَ ٱلۡأَعۡرَابِ سَتُدۡعَوۡنَ إِلَىٰ قَوۡمٍ أُوْلِي بَأۡسٖ شَدِيدٖ تُقَٰتِلُونَهُمۡ أَوۡ يُسۡلِمُونَۖ فَإِن تُطِيعُواْ يُؤۡتِكُمُ ٱللَّهُ أَجۡرًا حَسَنٗاۖ وَإِن تَتَوَلَّوۡاْ كَمَا تَوَلَّيۡتُم مِّن قَبۡلُ يُعَذِّبۡكُمۡ عَذَابًا أَلِيمٗا
16. ዘላኖች (ከአዕራቦች) ወደ ኋላ ለቀሩት (እንዲህ) በላቸው: «የብርቱ ጭካኔ ባለቤት ወደ ሆኑ ህዝቦች ውጊያ ወደ ፊት ትጠራላችሁ፤ ትጋደሏቸዋላችሁ:: ወይም ይሰልማሉ ብትታዘዙም አላህ መልካም ምንዳን ይሰጣችኋል:: ከአሁን በፊት እንደ ሸሻችሁ ብትሸሹ ደግሞ አሳማሚ ቅጣት ይቀጣችኋል::»
تفسیرهای عربی:
لَّيۡسَ عَلَى ٱلۡأَعۡمَىٰ حَرَجٞ وَلَا عَلَى ٱلۡأَعۡرَجِ حَرَجٞ وَلَا عَلَى ٱلۡمَرِيضِ حَرَجٞۗ وَمَن يُطِعِ ٱللَّهَ وَرَسُولَهُۥ يُدۡخِلۡهُ جَنَّٰتٖ تَجۡرِي مِن تَحۡتِهَا ٱلۡأَنۡهَٰرُۖ وَمَن يَتَوَلَّ يُعَذِّبۡهُ عَذَابًا أَلِيمٗا
17. (ሰዎች ሆይ!) በአይነስውር ላይ (ከዘመቻ በመቅረቱ) ኃጢአት የለበትም:: በአንካሳ ላይም ኃጢአት የለበትም:: በበሽተኛም ላይ ኃጢአት የለበትም:: አላህንና መልዕክተኛውን የሚታዘዝ ሁሉ ከስሮቻቸው ወንዞች የሚፈሱባቸውን ገነቶች ያስገባዋል:: የሚያፈገፍገዉንም ሁሉ አሳማሚ ቅጣት ይቀጣዋል::
تفسیرهای عربی:
۞ لَّقَدۡ رَضِيَ ٱللَّهُ عَنِ ٱلۡمُؤۡمِنِينَ إِذۡ يُبَايِعُونَكَ تَحۡتَ ٱلشَّجَرَةِ فَعَلِمَ مَا فِي قُلُوبِهِمۡ فَأَنزَلَ ٱلسَّكِينَةَ عَلَيۡهِمۡ وَأَثَٰبَهُمۡ فَتۡحٗا قَرِيبٗا
18. (መልዕክተኛችን ሙሐመድ ሆይ!) ከምዕመናኖቹ በዛፊቱ ስር ቃል ኪዳን በሚጋቡህ ጊዜ አላህ በእርግጥ ስራቸዉን ወደደላቸው:: በልቦቻቸዉም ውስጥ ያለውን ዐወቀ:: በነሱም ላይ እርጋታን አወረደ:: ቅርብ የሆነንም መክፈት መነዳቸው::
تفسیرهای عربی:
وَمَغَانِمَ كَثِيرَةٗ يَأۡخُذُونَهَاۗ وَكَانَ ٱللَّهُ عَزِيزًا حَكِيمٗا
19. ብዙዎች የተማረኩትን ገንዘቦች የሚወስዷቸው የሆኑን መነዳቸው:: አላህም ሁሉን አሸናፊና ጥበበኛ ነው::
تفسیرهای عربی:
وَعَدَكُمُ ٱللَّهُ مَغَانِمَ كَثِيرَةٗ تَأۡخُذُونَهَا فَعَجَّلَ لَكُمۡ هَٰذِهِۦ وَكَفَّ أَيۡدِيَ ٱلنَّاسِ عَنكُمۡ وَلِتَكُونَ ءَايَةٗ لِّلۡمُؤۡمِنِينَ وَيَهۡدِيَكُمۡ صِرَٰطٗا مُّسۡتَقِيمٗا
20. (አማኞች ሆይ!) አላህ ብዙዎቹን ምርኮዎች የምትወስዷቸው የሆኑን አላህ ቃል ገባላችሁ። ይህንንም ለእናንተ አስቸኮለላቻችሁ:: ከናንተም የሰዎችን እጆች ሠበሰበላችሁ። ብታመሰግኑና ለአማኞችም መልዕክት እንድትሆን ቀጥተኛውን መንገድ ይመራችሁም ዘንድ ይህን አደረግንላችሁ::
تفسیرهای عربی:
وَأُخۡرَىٰ لَمۡ تَقۡدِرُواْ عَلَيۡهَا قَدۡ أَحَاطَ ٱللَّهُ بِهَاۚ وَكَانَ ٱللَّهُ عَلَىٰ كُلِّ شَيۡءٖ قَدِيرٗا
21. ሌላይቱንም በእርሷ ላይ ገና ያልቻላችኋትን አላህ ያወቃትን ለእናንተ አዘጋጅቷል:: አላህ በነገሩ ሁሉ ላይ ቻይ ነውና::
تفسیرهای عربی:
وَلَوۡ قَٰتَلَكُمُ ٱلَّذِينَ كَفَرُواْ لَوَلَّوُاْ ٱلۡأَدۡبَٰرَ ثُمَّ لَا يَجِدُونَ وَلِيّٗا وَلَا نَصِيرٗا
22. እነዚያም የካዱት (የመካ ሰዎች) በተዋጓችሁ ኖሮ ለሽሽት ጀርባዎችን ባዞሩ ነበር:: ከዚያ ዘመድም ረዳትም አያገኙም::
تفسیرهای عربی:
سُنَّةَ ٱللَّهِ ٱلَّتِي قَدۡ خَلَتۡ مِن قَبۡلُۖ وَلَن تَجِدَ لِسُنَّةِ ٱللَّهِ تَبۡدِيلٗا
23. (መልዕክተኛችን ሙሐመድ ሆይ!) አላህ ያችን ከዚህ በፊት በእርግጥ ያለችፈውን ልማድ ደነገገ:: ለአላህ ልማድ መቸም ለውጥን አታገኝም::
تفسیرهای عربی:
وَهُوَ ٱلَّذِي كَفَّ أَيۡدِيَهُمۡ عَنكُمۡ وَأَيۡدِيَكُمۡ عَنۡهُم بِبَطۡنِ مَكَّةَ مِنۢ بَعۡدِ أَنۡ أَظۡفَرَكُمۡ عَلَيۡهِمۡۚ وَكَانَ ٱللَّهُ بِمَا تَعۡمَلُونَ بَصِيرًا
24. እርሱ(አላህ) ያ በመካ ውስጥ በእነርሱ ላይ ካስቻላችሁ በኋላ እጆቻቸዉን ከእናንተ ላይ እጆቻችሁንም ከእነርሱ ላይ የከለከለ ነው:: አላህም የምትሰሩትን ነገር ሁሉ ተመልካች ነው::
تفسیرهای عربی:
هُمُ ٱلَّذِينَ كَفَرُواْ وَصَدُّوكُمۡ عَنِ ٱلۡمَسۡجِدِ ٱلۡحَرَامِ وَٱلۡهَدۡيَ مَعۡكُوفًا أَن يَبۡلُغَ مَحِلَّهُۥۚ وَلَوۡلَا رِجَالٞ مُّؤۡمِنُونَ وَنِسَآءٞ مُّؤۡمِنَٰتٞ لَّمۡ تَعۡلَمُوهُمۡ أَن تَطَـُٔوهُمۡ فَتُصِيبَكُم مِّنۡهُم مَّعَرَّةُۢ بِغَيۡرِ عِلۡمٖۖ لِّيُدۡخِلَ ٱللَّهُ فِي رَحۡمَتِهِۦ مَن يَشَآءُۚ لَوۡ تَزَيَّلُواْ لَعَذَّبۡنَا ٱلَّذِينَ كَفَرُواْ مِنۡهُمۡ عَذَابًا أَلِيمًا
25. እነርሱ ማለት እነዚያ በአላህ የካዱ፤ ከተከበረው መስጊድም የከለከሏችሁ መስዋዕትንም የታሰረ ሲሆን ወደ ስፍራው እንዳይደርስ የከለከሉ ናቸው:: የማታውቋቸው ወንድ አማኞችና ሴት ምዕመናት ከከሓዲያኑ ጋር ባልነበሩ ኖሮና እናንተም ያለ እውቀት እነርሱን ረግጣችሁ ከእነርሱ (በኩል) መከፋት የሚነካችሁ ባይሆን ኖሮ እጆቻችሁን ባላገድን ነበር:: አላህም የሚፈልገውን ሰው በእዝነቱ ውስጥ ያስገባ ዘንድ (እጆቻችሁን አገደ):: በተለዩ ኖሮ እነዚያን ከእርሱ ውስጥ በአላህ የካዱትን አሳማሚን ቅጣት በቀጣናቸው ነበር::
تفسیرهای عربی:
إِذۡ جَعَلَ ٱلَّذِينَ كَفَرُواْ فِي قُلُوبِهِمُ ٱلۡحَمِيَّةَ حَمِيَّةَ ٱلۡجَٰهِلِيَّةِ فَأَنزَلَ ٱللَّهُ سَكِينَتَهُۥ عَلَىٰ رَسُولِهِۦ وَعَلَى ٱلۡمُؤۡمِنِينَ وَأَلۡزَمَهُمۡ كَلِمَةَ ٱلتَّقۡوَىٰ وَكَانُوٓاْ أَحَقَّ بِهَا وَأَهۡلَهَاۚ وَكَانَ ٱللَّهُ بِكُلِّ شَيۡءٍ عَلِيمٗا
26. እነዚያን በአላህ የካዱት ደራይቱን (እልህን) የመሀይምነቲቱን ደራ (እልህ) በልቦቻቸው ውስጥ ባደረጉ ጊዜ በቀጣናቸው ነበር:: አላህም በመልዕክተኛው ላይ እና በምዕመናኖቹ ላይ እርጋታውን አወረደ:: መጠበቂያይቱንም ቃል አስያዛቸው:: በእርሷም ተገቢዎች ባለቤቶቿም ነበሩ:: አላህም በነገሩ ሁሉ አዋቂ ነው።
تفسیرهای عربی:
لَّقَدۡ صَدَقَ ٱللَّهُ رَسُولَهُ ٱلرُّءۡيَا بِٱلۡحَقِّۖ لَتَدۡخُلُنَّ ٱلۡمَسۡجِدَ ٱلۡحَرَامَ إِن شَآءَ ٱللَّهُ ءَامِنِينَ مُحَلِّقِينَ رُءُوسَكُمۡ وَمُقَصِّرِينَ لَا تَخَافُونَۖ فَعَلِمَ مَا لَمۡ تَعۡلَمُواْ فَجَعَلَ مِن دُونِ ذَٰلِكَ فَتۡحٗا قَرِيبًا
27. ህልሙ እውነተኛ ሲሆን አላህ የፈለገ አንደሆነ ጸጥተኞች ሆናችሁ ራሳችሁን ላጭታችሁ አሳጥራችሁ የማትፈሩ ስትሆኑ የተከበረውን መስጊድ በእርግጥ ትገባላችሁ ያለውን ህልም አሏህ ለመልዕክተኛው(ለሙሀመድ) እውነት አደረገለት:: አላህ (ከእርቁ) ከመመለሳችሁ ሂደት ያላወቃችሁትንም ነገር አወቀ:: እናም ከዚህ በፊት ቅርብን የመክፈት እርቅ አደረገ::
تفسیرهای عربی:
هُوَ ٱلَّذِيٓ أَرۡسَلَ رَسُولَهُۥ بِٱلۡهُدَىٰ وَدِينِ ٱلۡحَقِّ لِيُظۡهِرَهُۥ عَلَى ٱلدِّينِ كُلِّهِۦۚ وَكَفَىٰ بِٱللَّهِ شَهِيدٗا
28. እርሱ (አላህ) ያ መልዕክተኛውን (ነብዩ ሙሐመድን) በመሪ መጽሐፍና በእውነተኛ ሀይማኖት በሁሉ ላይ ሊያልቀው (የበላይ ሊያደርገው) የላከ ነው:: መስካሪነትም አላህ በቃ።
تفسیرهای عربی:
مُّحَمَّدٞ رَّسُولُ ٱللَّهِۚ وَٱلَّذِينَ مَعَهُۥٓ أَشِدَّآءُ عَلَى ٱلۡكُفَّارِ رُحَمَآءُ بَيۡنَهُمۡۖ تَرَىٰهُمۡ رُكَّعٗا سُجَّدٗا يَبۡتَغُونَ فَضۡلٗا مِّنَ ٱللَّهِ وَرِضۡوَٰنٗاۖ سِيمَاهُمۡ فِي وُجُوهِهِم مِّنۡ أَثَرِ ٱلسُّجُودِۚ ذَٰلِكَ مَثَلُهُمۡ فِي ٱلتَّوۡرَىٰةِۚ وَمَثَلُهُمۡ فِي ٱلۡإِنجِيلِ كَزَرۡعٍ أَخۡرَجَ شَطۡـَٔهُۥ فَـَٔازَرَهُۥ فَٱسۡتَغۡلَظَ فَٱسۡتَوَىٰ عَلَىٰ سُوقِهِۦ يُعۡجِبُ ٱلزُّرَّاعَ لِيَغِيظَ بِهِمُ ٱلۡكُفَّارَۗ وَعَدَ ٱللَّهُ ٱلَّذِينَ ءَامَنُواْ وَعَمِلُواْ ٱلصَّٰلِحَٰتِ مِنۡهُم مَّغۡفِرَةٗ وَأَجۡرًا عَظِيمَۢا
29. የአላህ መልዕክተኛ (ነብዩ) ሙሐመድ እና እነዚያም የእርሱ ጓደኞች በከሓዲያን ላይ ብርቱዎች በመካከላቸው ተዛዛኞች ናቸው:: አጎንባሾች፤ ሰጋጆች፤ ሆነው ታያቸዋልህ:: ችሮታንና ውዴታን ሁልጊዜም ከአላህ ይፈልጋሉ:: ምልክታቸው ከስግደታቸው ፈለግ ስትሆን በፊታቸው ላይ ናት:: ይህ በተውራት (የተነገረላቸው) ጸባያቸው ነው:: በኢንጅል ውስጥ የተጠቀሰው ምሳሌያቸው ደግሞ ቀንዘሉን እንደ አወጣ አዝመራና (ቀንዘሉን) እንዳበረታው እንደ ወፍራምና ገበሬዎቹን የሚያስደነቅ ሆኖ አገዳዎቹ ላይ ተስተካክሎ እንደቆመ (አዝመራ) ነው:: ያበረታቸውና ከሓዲያን በእርሱ ሊያሰቆጭ ነው:: አላህ እነዚያን በእሱ ያመኑትንና ከእነርሱ በጎዎችን ተግባራት የሰሩትን ሁሉ ምህረትንና ታላቅ ምንዳን ቃል ገበቶላቸዋል::
تفسیرهای عربی:
 
ترجمهٔ معانی سوره: سوره فتح
فهرست سوره ها شماره صفحه
 
ترجمهٔ معانی قرآن کریم - الترجمة الأمهرية - زين - لیست ترجمه ها

ترجمة معاني القرآن الكريم إلى اللغة الأمهرية ترجمها محمد زين نهر الدين صادرة عن أكاديمية أفريقيا.

بستن