Check out the new design

Firo maanaaji al-quraan tedduɗo oo - Eggo Amhariiwo - Akademii Afrik * - Tippudi firooji ɗii


Firo maanaaji Simoore: Simoore nagge   Aaya:
لَّا يُؤَاخِذُكُمُ ٱللَّهُ بِٱللَّغۡوِ فِيٓ أَيۡمَٰنِكُمۡ وَلَٰكِن يُؤَاخِذُكُم بِمَا كَسَبَتۡ قُلُوبُكُمۡۗ وَٱللَّهُ غَفُورٌ حَلِيمٞ
225. ያለ አስተውሎት በምትፈጽሙት መሐላዎቻችሁ አላህ አይቀጣችሁም:: ግን ልቦቻችሁ በጽኑ ባሰቡበት መሐላዎቻችሁ ይይዛችኋል:: አላህ በጣም መሀሪ፤ ታጋሽ ነውና::
Faccirooji aarabeeji:
لِّلَّذِينَ يُؤۡلُونَ مِن نِّسَآئِهِمۡ تَرَبُّصُ أَرۡبَعَةِ أَشۡهُرٖۖ فَإِن فَآءُو فَإِنَّ ٱللَّهَ غَفُورٞ رَّحِيمٞ
226. እነዚያ ሚስቶቻቸውን ላለመገናኘት የሚምሉ ወንዶች ሁሉ ለማሰላሰያ ጊዜ አራት ወራት አላቸው:: እናም መሀላቸውን ቢያጥፉና ቢመለሱ አላህ መሀሪና አዛኝ ነው::
Faccirooji aarabeeji:
وَإِنۡ عَزَمُواْ ٱلطَّلَٰقَ فَإِنَّ ٱللَّهَ سَمِيعٌ عَلِيمٞ
227. ፍችን ለመፈጸም ጽኑ ውሳኔ ላይ ከደረሱ ደግሞ (ይፋቱ):: አላህም ሁሉን ሰሚ ሁሉንም አዋቂ ነዉና::
Faccirooji aarabeeji:
وَٱلۡمُطَلَّقَٰتُ يَتَرَبَّصۡنَ بِأَنفُسِهِنَّ ثَلَٰثَةَ قُرُوٓءٖۚ وَلَا يَحِلُّ لَهُنَّ أَن يَكۡتُمۡنَ مَا خَلَقَ ٱللَّهُ فِيٓ أَرۡحَامِهِنَّ إِن كُنَّ يُؤۡمِنَّ بِٱللَّهِ وَٱلۡيَوۡمِ ٱلۡأٓخِرِۚ وَبُعُولَتُهُنَّ أَحَقُّ بِرَدِّهِنَّ فِي ذَٰلِكَ إِنۡ أَرَادُوٓاْ إِصۡلَٰحٗاۚ وَلَهُنَّ مِثۡلُ ٱلَّذِي عَلَيۡهِنَّ بِٱلۡمَعۡرُوفِۚ وَلِلرِّجَالِ عَلَيۡهِنَّ دَرَجَةٞۗ وَٱللَّهُ عَزِيزٌ حَكِيمٌ
228. የተፈቱ ሴቶችም በራሳቸው ሶስትን የወር አበባ ይጠብቁ። በአላህና በመጨረሻው ቀን የሚያምኑ ከሆኑ አላህ በማህጸኖቻቸው ውስጥ የፈጠረውን ጽንስ ሊደብቁ አይፈቀድላቸዉም:: ባሎቻቸዉም እርቅን ከፈለጉ በእነዚህ ወራት ውስጥ የመመለስ መብታቸው ቅድሚያ ነው:: ለሴቶች ግዳጅ እንዳለባቸው ሁሉ ፍትሀዊ መብትም አላቸው:: ይሁንና ወንዶች (የበለጠ ሀላፊነትን ስለሚሸከሙ) ብልጫ አላቸው። (ተጥሎባቸዋል):: አላህ ሁሉን አሸናፊና ጥበበኛ ነውና::
Faccirooji aarabeeji:
ٱلطَّلَٰقُ مَرَّتَانِۖ فَإِمۡسَاكُۢ بِمَعۡرُوفٍ أَوۡ تَسۡرِيحُۢ بِإِحۡسَٰنٖۗ وَلَا يَحِلُّ لَكُمۡ أَن تَأۡخُذُواْ مِمَّآ ءَاتَيۡتُمُوهُنَّ شَيۡـًٔا إِلَّآ أَن يَخَافَآ أَلَّا يُقِيمَا حُدُودَ ٱللَّهِۖ فَإِنۡ خِفۡتُمۡ أَلَّا يُقِيمَا حُدُودَ ٱللَّهِ فَلَا جُنَاحَ عَلَيۡهِمَا فِيمَا ٱفۡتَدَتۡ بِهِۦۗ تِلۡكَ حُدُودُ ٱللَّهِ فَلَا تَعۡتَدُوهَاۚ وَمَن يَتَعَدَّ حُدُودَ ٱللَّهِ فَأُوْلَٰٓئِكَ هُمُ ٱلظَّٰلِمُونَ
229. የመመለስ እድል የሚሰጠው ፍቺ ሁለት ጊዜ ብቻ ነው:: ከዚያም በመልካም መያዝ ወይም በበጎ አኳኋን ማሰናበት ነው:: (ባሎች ሆይ!) የአላህን ህግጋት ያለማክበር ስጋት ካልኖረባቸው በስተቀር ከሰጣችኋቸው ነገር ምንንም ልትወስዱ ለእናንተ አይፈቀድላችሁም:: የአላህን ሕግጋት አለመጠበቃቸውን ብትገነዘቡ ነፃ ለማውጣት በምትፈጽመው ነገር በሁለቱም ላይ ኃጢአት የለባቸዉም:: እኒህ የአላህ ሕግጋት ናቸው:: አትተላለፏቸው:: እነዚያ እነርሱ የአላህን ሕግጋት የሚተላለፉ ሁሉ (በደለኞች) አጥፊዎች ናቸው::
Faccirooji aarabeeji:
فَإِن طَلَّقَهَا فَلَا تَحِلُّ لَهُۥ مِنۢ بَعۡدُ حَتَّىٰ تَنكِحَ زَوۡجًا غَيۡرَهُۥۗ فَإِن طَلَّقَهَا فَلَا جُنَاحَ عَلَيۡهِمَآ أَن يَتَرَاجَعَآ إِن ظَنَّآ أَن يُقِيمَا حُدُودَ ٱللَّهِۗ وَتِلۡكَ حُدُودُ ٱللَّهِ يُبَيِّنُهَا لِقَوۡمٖ يَعۡلَمُونَ
230. ከዚያም ለሶስተኛ ጊዜ ከፈታት በኋላ ሌላን ባል እስካላገባች (ከዚያም እስካልተፈታች ወይም እስካልሞተባት) ድረስ ለእርሱ አትፈቀደለትም:: ሁለተኛው ባል ከፈታት የአላህን ሕግጋት እንደሚጠብቁ ተስፋ ካደረጉ በመማለሳቸው በሁለቱም ላይ ኃጢኣት የለባቸውም:: እነኚህ የአላህ ሕግጋት ናቸው:: ለሚያውቁ ሕዝቦች ሁሉ ያብራራላቸዋል::
Faccirooji aarabeeji:
 
Firo maanaaji Simoore: Simoore nagge
Tippudi cimooje Tonngoode hello ngoo
 
Firo maanaaji al-quraan tedduɗo oo - Eggo Amhariiwo - Akademii Afrik - Tippudi firooji ɗii

Eggo mum - Muhammad Zain Zahr al-Din. E haala Akademii Afrik.

Uddude