Check out the new design

Firo maanaaji al-quraan tedduɗo oo - Eggo Amhariiwo - Akademii Afrik * - Tippudi firooji ɗii


Firo maanaaji Simoore: Simoore nagge   Aaya:
فَلَمَّا فَصَلَ طَالُوتُ بِٱلۡجُنُودِ قَالَ إِنَّ ٱللَّهَ مُبۡتَلِيكُم بِنَهَرٖ فَمَن شَرِبَ مِنۡهُ فَلَيۡسَ مِنِّي وَمَن لَّمۡ يَطۡعَمۡهُ فَإِنَّهُۥ مِنِّيٓ إِلَّا مَنِ ٱغۡتَرَفَ غُرۡفَةَۢ بِيَدِهِۦۚ فَشَرِبُواْ مِنۡهُ إِلَّا قَلِيلٗا مِّنۡهُمۡۚ فَلَمَّا جَاوَزَهُۥ هُوَ وَٱلَّذِينَ ءَامَنُواْ مَعَهُۥ قَالُواْ لَا طَاقَةَ لَنَا ٱلۡيَوۡمَ بِجَالُوتَ وَجُنُودِهِۦۚ قَالَ ٱلَّذِينَ يَظُنُّونَ أَنَّهُم مُّلَٰقُواْ ٱللَّهِ كَم مِّن فِئَةٖ قَلِيلَةٍ غَلَبَتۡ فِئَةٗ كَثِيرَةَۢ بِإِذۡنِ ٱللَّهِۗ وَٱللَّهُ مَعَ ٱلصَّٰبِرِينَ
249. ጧሉትም በሰራዊቱ ታጅቦ በመጣ ጊዜ ‹‹አላህ በወንዝ ውሃ ይፈትናችኃል:: እናም ከእርሱ የጠጣ ሰው ሁሉ ከእኔ አይደለም:: እሱን ያልቀመሰው ሰው ግን በእጁ አንድ እፍኝ ያህል የዘገነ ሰው ብቻ ሲቀር እርሱ ከእኔ ነው›› አለ:: ከእነርሱም መካከል ጥቂቶች ሲቀሩ ከእርሱ ጠጡ:: እርሱና እነዚያ ከእርሱ ጋር ያመኑት ወንዙን ባለፉት ጊዜ፡- «ጃሉትን (ጎልያድን) እና ሰራዊቱን ለመዋጋት በቂ ችሎታና ጥንካሬ የለንም።» አሉት:: እነዚያ ከአላህ ጋር እንደሚገናኙ የሚያረጋግጡትም «ጥቂት ቡድን በአላህ ፈቃድ ብዙውን ቡድን ያሸነፈበት አጋጣሚ ብዙ ነው:: አላህ ከታጋሾች ጋር ነውና።» አሉ።
Faccirooji aarabeeji:
وَلَمَّا بَرَزُواْ لِجَالُوتَ وَجُنُودِهِۦ قَالُواْ رَبَّنَآ أَفۡرِغۡ عَلَيۡنَا صَبۡرٗا وَثَبِّتۡ أَقۡدَامَنَا وَٱنصُرۡنَا عَلَى ٱلۡقَوۡمِ ٱلۡكَٰفِرِينَ
250. ለጃሉትና ለሰራዊቱ በተሰለፉም ጊዜ፡- «ጌታችን ሆይ! ትግስትን ለግሰን:: እግሮቻችንን አጽናልን:: በከሓዲያን ሕዝቦችም ላይ እርዳን።» አሉ።
Faccirooji aarabeeji:
فَهَزَمُوهُم بِإِذۡنِ ٱللَّهِ وَقَتَلَ دَاوُۥدُ جَالُوتَ وَءَاتَىٰهُ ٱللَّهُ ٱلۡمُلۡكَ وَٱلۡحِكۡمَةَ وَعَلَّمَهُۥ مِمَّا يَشَآءُۗ وَلَوۡلَا دَفۡعُ ٱللَّهِ ٱلنَّاسَ بَعۡضَهُم بِبَعۡضٖ لَّفَسَدَتِ ٱلۡأَرۡضُ وَلَٰكِنَّ ٱللَّهَ ذُو فَضۡلٍ عَلَى ٱلۡعَٰلَمِينَ
251. እናም በአላህ ፈቃድ ድል መቷቸው:: ነብዩ ዳውድም ጃሉትን ገደለ:: ለዳውድ ንግሥናን፤ ጥበብን እና ነብይነትን አላህ ሰጣቸው:: ከሚሻው ነገር ሁሉ አሳወቀው:: አላህ ሰዎችን ከፊላቸውን በከፊሉ መመለሱ (መከላከሉ) ባልነበረ ኖሮ ምድር በጠቅላላ በተበላሸች ነበር:: ግን አላህ በዓለማት ላይ የችሮታ ባለቤት ነው::
Faccirooji aarabeeji:
تِلۡكَ ءَايَٰتُ ٱللَّهِ نَتۡلُوهَا عَلَيۡكَ بِٱلۡحَقِّۚ وَإِنَّكَ لَمِنَ ٱلۡمُرۡسَلِينَ
252. እነዚህ አናቅጽ በእውነት ባንተ ላይ የምናነባቸው ሲሆኑ የአላህ አናቅጽ ናቸው:: አንተም በእርግጥ ከመልዕክተኞቹ መካከል አንዱ ነህ::
Faccirooji aarabeeji:
 
Firo maanaaji Simoore: Simoore nagge
Tippudi cimooje Tonngoode hello ngoo
 
Firo maanaaji al-quraan tedduɗo oo - Eggo Amhariiwo - Akademii Afrik - Tippudi firooji ɗii

Eggo mum - Muhammad Zain Zahr al-Din. E haala Akademii Afrik.

Uddude