Check out the new design

કુરઆન મજીદના શબ્દોનું ભાષાંતર - એમ્હારિક ભાષામાં અનુવાદ - આફ્રિકન એકેડમી * - ભાષાંતરોની અનુક્રમણિકા


શબ્દોનું ભાષાંતર સૂરહ: અન્ નમલ   આયત:
أَمَّن يَبۡدَؤُاْ ٱلۡخَلۡقَ ثُمَّ يُعِيدُهُۥ وَمَن يَرۡزُقُكُم مِّنَ ٱلسَّمَآءِ وَٱلۡأَرۡضِۗ أَءِلَٰهٞ مَّعَ ٱللَّهِۚ قُلۡ هَاتُواْ بُرۡهَٰنَكُمۡ إِن كُنتُمۡ صَٰدِقِينَ
64. ወይስ መፍጠርን የሚጀምር ከዚያም የሚመልሰው፤ ከሰማይና ከምድርም ሲሳይን የሚሰጣቸሁ አምላክ ማን ሆነና? ከአላህ ጋር ሌላ ትክክለኛ አምላክ አለን? እውነተኞች እንደሆናችሁ አስረጃችሁን አምጡ በላቸው::
અરબી તફસીરો:
قُل لَّا يَعۡلَمُ مَن فِي ٱلسَّمَٰوَٰتِ وَٱلۡأَرۡضِ ٱلۡغَيۡبَ إِلَّا ٱللَّهُۚ وَمَا يَشۡعُرُونَ أَيَّانَ يُبۡعَثُونَ
65. (መልዕክተኛችን ሙሐመድ ሆይ!) «በሰማያትና በምድር ያለው ሁሉ ሩቅን ምስጢር አያውቅም:: አላህ ግን ያውቀዋል:: መቼ እንደሚቀሰቀሱም አያውቁም።» በላቸው።
અરબી તફસીરો:
بَلِ ٱدَّٰرَكَ عِلۡمُهُمۡ فِي ٱلۡأٓخِرَةِۚ بَلۡ هُمۡ فِي شَكّٖ مِّنۡهَاۖ بَلۡ هُم مِّنۡهَا عَمُونَ
66. በእውነት የመጨረሻይቱን ዓለም ሁኔታ ማወቃቸው ተሟላን? አይደለም። እነርሱ ከእርሷ በመጠራጠር ውስጥ ናቸው:: በእውነትም እነርሱ ከእርሷ እውሮች ናቸው::
અરબી તફસીરો:
وَقَالَ ٱلَّذِينَ كَفَرُوٓاْ أَءِذَا كُنَّا تُرَٰبٗا وَءَابَآؤُنَآ أَئِنَّا لَمُخۡرَجُونَ
67. እነዚያም በአላህ የካዱት አሉ፡- «እኛም አባቶቻችንም ዐፈር በሆንን ጊዜ እንደ ገና ከመቃብር የምንወጣ ነን?
અરબી તફસીરો:
لَقَدۡ وُعِدۡنَا هَٰذَا نَحۡنُ وَءَابَآؤُنَا مِن قَبۡلُ إِنۡ هَٰذَآ إِلَّآ أَسَٰطِيرُ ٱلۡأَوَّلِينَ
68. «ይህንን እኛም ሆነ ከእኛ በፊትም የነበሩት አባቶቻችን በእርግጥ ተቀጥረንበታል:: ይህ የመጀመሪያዎቹ ሰዎች ተረቶች እንጂ ሌላ አይደለም።» አሉ።
અરબી તફસીરો:
قُلۡ سِيرُواْ فِي ٱلۡأَرۡضِ فَٱنظُرُواْ كَيۡفَ كَانَ عَٰقِبَةُ ٱلۡمُجۡرِمِينَ
69. (መልዕክተኛችን ሙሐመድ ሆይ!) «በምድር ላይ ሂዱ የአመጸኞችም መጨረሻ እንዴት እንደነበረ ተመልክቱ።» በላቸው።
અરબી તફસીરો:
وَلَا تَحۡزَنۡ عَلَيۡهِمۡ وَلَا تَكُن فِي ضَيۡقٖ مِّمَّا يَمۡكُرُونَ
70. (መልዕክተኛችን ሙሐመድ ሆይ!) በእነርሱም ላይ አትዘን:: ከሚመክሩብህም ነገር በጭንቀት ውስጥ አትሁን::
અરબી તફસીરો:
وَيَقُولُونَ مَتَىٰ هَٰذَا ٱلۡوَعۡدُ إِن كُنتُمۡ صَٰدِقِينَ
71. «እውነተኞችም እንደሆናችሁ ይህ ቀጠሮ መቼ ነው?» ይላሉ።
અરબી તફસીરો:
قُلۡ عَسَىٰٓ أَن يَكُونَ رَدِفَ لَكُم بَعۡضُ ٱلَّذِي تَسۡتَعۡجِلُونَ
72. (መልዕክተኛችን ሙሐመድ ሆይ!) «የዚያ የምትቻኮሉበት ከፊሉ ለእናንተ የቀረበ መሆኑ ተረጋግጧል።» በላቸው።
અરબી તફસીરો:
وَإِنَّ رَبَّكَ لَذُو فَضۡلٍ عَلَى ٱلنَّاسِ وَلَٰكِنَّ أَكۡثَرَهُمۡ لَا يَشۡكُرُونَ
73. (መልዕክተኛችን ሙሐመድ ሆይ!) ጌታህም በሰዎች ላይ በእርግጥ የችሮታ ባለቤት ነው:: ግን አብዛኛዎቻቸው አያመሰግኑም::
અરબી તફસીરો:
وَإِنَّ رَبَّكَ لَيَعۡلَمُ مَا تُكِنُّ صُدُورُهُمۡ وَمَا يُعۡلِنُونَ
74. (መልዕክተኛችን ሙሐመድ ሆይ!) ጌታህም ልቦቻቸው የሚደብቁትንና የሚገልጹትን ያውቃል::
અરબી તફસીરો:
وَمَا مِنۡ غَآئِبَةٖ فِي ٱلسَّمَآءِ وَٱلۡأَرۡضِ إِلَّا فِي كِتَٰبٖ مُّبِينٍ
75. በሰማይም ሆነ በምድር ውስጥ ምንም የተደበቀ ነገር የለም:: ገላጭ በሆነው መጽሐፍ ውስጥ ያለ ቢሆን እንጂ::
અરબી તફસીરો:
إِنَّ هَٰذَا ٱلۡقُرۡءَانَ يَقُصُّ عَلَىٰ بَنِيٓ إِسۡرَٰٓءِيلَ أَكۡثَرَ ٱلَّذِي هُمۡ فِيهِ يَخۡتَلِفُونَ
76. ይህ ቁርኣን እነዚያ የኢስራኢል ልጆች እነርሱ በእርሱ ላይ የሚለያዩበትን ጉዳይ አብዛኛውን ይነግራል::
અરબી તફસીરો:
 
શબ્દોનું ભાષાંતર સૂરહ: અન્ નમલ
સૂરહ માટે અનુક્રમણિકા પેજ નંબર
 
કુરઆન મજીદના શબ્દોનું ભાષાંતર - એમ્હારિક ભાષામાં અનુવાદ - આફ્રિકન એકેડમી - ભાષાંતરોની અનુક્રમણિકા

તેનું અનુવાદ મુહમ્મદ ઝૈન ઝહરુદ્ દીન દ્વારા કરવામાં આવ્યું. આફ્રિકા એકેડમી દ્વારા પ્રકાશિત.

બંધ કરો