Check out the new design

કુરઆન મજીદના શબ્દોનું ભાષાંતર - એમ્હારિક ભાષામાં અનુવાદ - આફ્રિકન એકેડમી * - ભાષાંતરોની અનુક્રમણિકા


શબ્દોનું ભાષાંતર સૂરહ: આલિ ઇમરાન   આયત:
إِنَّ ٱلَّذِينَ كَفَرُواْ لَن تُغۡنِيَ عَنۡهُمۡ أَمۡوَٰلُهُمۡ وَلَآ أَوۡلَٰدُهُم مِّنَ ٱللَّهِ شَيۡـٔٗاۖ وَأُوْلَٰٓئِكَ هُمۡ وَقُودُ ٱلنَّارِ
10. እነዚያ የካዱትን ገንዘቦቻቸውና ልጆቻቸው ከአላህ (ቅጣት) አያስጥሏቸዉም። እነዚያም እነርሱ የእሳት ማገዶዎች ናቸው።
અરબી તફસીરો:
كَدَأۡبِ ءَالِ فِرۡعَوۡنَ وَٱلَّذِينَ مِن قَبۡلِهِمۡۚ كَذَّبُواْ بِـَٔايَٰتِنَا فَأَخَذَهُمُ ٱللَّهُ بِذُنُوبِهِمۡۗ وَٱللَّهُ شَدِيدُ ٱلۡعِقَابِ
11. ምሳሊያቸው ልክ እንደ ፈርዖን ቤተሰቦችና እንደነዚያ ከበፊታቸዉም እንደነበሩት ሕዝቦች ልማድ ነው:: በአናቅጻችን አስተባበሉ:: እናም አላህ በኃጢአቶቻቸው ቀጣቸው:: አላህ ቅጣተ ብርቱ ነውና::
અરબી તફસીરો:
قُل لِّلَّذِينَ كَفَرُواْ سَتُغۡلَبُونَ وَتُحۡشَرُونَ إِلَىٰ جَهَنَّمَۖ وَبِئۡسَ ٱلۡمِهَادُ
12. (መልዕክተኛችን ሙሐመድ ሆይ!) ለእነዚያ በአላህ ለካዱ ሰዎች «በቅርብ ጊዜ ትሸነፋላችሁ:: ከዚያም በገሀነም ትሰበሰባላችሁ:: ምንጣፊቱም (ገሀነም) ምን ትከፋ!» በላቸው::
અરબી તફસીરો:
قَدۡ كَانَ لَكُمۡ ءَايَةٞ فِي فِئَتَيۡنِ ٱلۡتَقَتَاۖ فِئَةٞ تُقَٰتِلُ فِي سَبِيلِ ٱللَّهِ وَأُخۡرَىٰ كَافِرَةٞ يَرَوۡنَهُم مِّثۡلَيۡهِمۡ رَأۡيَ ٱلۡعَيۡنِۚ وَٱللَّهُ يُؤَيِّدُ بِنَصۡرِهِۦ مَن يَشَآءُۚ إِنَّ فِي ذَٰلِكَ لَعِبۡرَةٗ لِّأُوْلِي ٱلۡأَبۡصَٰرِ
13. በእነዚያ (የበድር) ቀን በተጋጠሙት ሁለት ቡድኖች ለእናንተ ብዙ ተዓምራት አሉ:: አንደኛዋ ቡድን በአላህ መንገድ ትጋደላለች:: ሌላይቱ ቡድን ደግሞ ከሓዲ ናት። በዓይን አስተያየት እጥፋቸው ሆነው ያዩዋቸዋል (በቁጥር የነርሱ እጥፍ ሁነው በአይናቸው ተመለከቷቸው)። አላህ በእርዳታው የሚሻውን ሁሉ ያበረታልና። በዚህ ውስጥ ለማስተዋል ባለቤቶች ሁሉ በእርግጥ መገሰጫ አለበት::
અરબી તફસીરો:
زُيِّنَ لِلنَّاسِ حُبُّ ٱلشَّهَوَٰتِ مِنَ ٱلنِّسَآءِ وَٱلۡبَنِينَ وَٱلۡقَنَٰطِيرِ ٱلۡمُقَنطَرَةِ مِنَ ٱلذَّهَبِ وَٱلۡفِضَّةِ وَٱلۡخَيۡلِ ٱلۡمُسَوَّمَةِ وَٱلۡأَنۡعَٰمِ وَٱلۡحَرۡثِۗ ذَٰلِكَ مَتَٰعُ ٱلۡحَيَوٰةِ ٱلدُّنۡيَاۖ وَٱللَّهُ عِندَهُۥ حُسۡنُ ٱلۡمَـَٔابِ
14. ከሴቶች፣ ከወንዶች ልጆች፣ ከወርቅ፣ ከብር፣ ከተከማቹ ገንዘቦች፣ ከተሰማሩ ፈረሶች፣ ከግመል ከከብትና ከፍየል፣ ከአዝመራም የሆኑ ፍላጎቶችን መውደድ ለሰዎች ተሸለመላቸው (ሰዎች ዘንድ የተወደዱ ተደረገላቸው)። ይህ ሁሉ የቅርቢቱ ሕይወት መጠቃቀሚያ ብቻ ነው:: አላህ ግን እርሱ ዘንድ መልካም የሆነ መመለሻ (ገነት) አለው::
અરબી તફસીરો:
۞ قُلۡ أَؤُنَبِّئُكُم بِخَيۡرٖ مِّن ذَٰلِكُمۡۖ لِلَّذِينَ ٱتَّقَوۡاْ عِندَ رَبِّهِمۡ جَنَّٰتٞ تَجۡرِي مِن تَحۡتِهَا ٱلۡأَنۡهَٰرُ خَٰلِدِينَ فِيهَا وَأَزۡوَٰجٞ مُّطَهَّرَةٞ وَرِضۡوَٰنٞ مِّنَ ٱللَّهِۗ وَٱللَّهُ بَصِيرُۢ بِٱلۡعِبَادِ
15. (መልዕክተኛችን ሙሐመድ ሆይ!) «ከዚህ ከተዋበላችሁ ጉዳይ የሚበልጥን ልንገራችሁን? እርሱም ለእነዚያ አላህን ለሚፈሩ ሁሉ በጌታቸው ዘንድ በስራቸው ወንዞች የሚፈሱባቸው ገነቶች በውስጧ ሁልጊዜ ነዋሪዎች ሲሆኑ ንጹህ ሚስቶችና ከአላህ የሆነ ውዴታም አለላቸው:: አላህም ባርያዎቹን ተመልካች ነው።» በላቸው።
અરબી તફસીરો:
 
શબ્દોનું ભાષાંતર સૂરહ: આલિ ઇમરાન
સૂરહ માટે અનુક્રમણિકા પેજ નંબર
 
કુરઆન મજીદના શબ્દોનું ભાષાંતર - એમ્હારિક ભાષામાં અનુવાદ - આફ્રિકન એકેડમી - ભાષાંતરોની અનુક્રમણિકા

તેનું અનુવાદ મુહમ્મદ ઝૈન ઝહરુદ્ દીન દ્વારા કરવામાં આવ્યું. આફ્રિકા એકેડમી દ્વારા પ્રકાશિત.

બંધ કરો