કુરઆન મજીદના શબ્દોનું ભાષાંતર - એમ્હારિક ભાષાંતર - ઝૈન * - ભાષાંતરોની અનુક્રમણિકા


શબ્દોનું ભાષાંતર સૂરહ: સૉદ   આયત:

ሱረቱ ሷድ

صٓۚ وَٱلۡقُرۡءَانِ ذِي ٱلذِّكۡرِ
1. ሷድ፤ የግሳፄ ባለቤት በሆነው ቁርኣን እምላለሁ።
અરબી તફસીરો:
بَلِ ٱلَّذِينَ كَفَرُواْ فِي عِزَّةٖ وَشِقَاقٖ
2. ይልቁንም እነዚያ በአላህ የካዱ ሰዎች በከባድ ትዕቢትና በአጓጉል ክርክር ውስጥ ናቸው።
અરબી તફસીરો:
كَمۡ أَهۡلَكۡنَا مِن قَبۡلِهِم مِّن قَرۡنٖ فَنَادَواْ وَّلَاتَ حِينَ مَنَاصٖ
3. ከእነርሱ በፊት ከክፍለ ዘመናት ህዝቦች ብዙን አጥፍተናል:: ጊዜው የመሸሻና የማምለጫ ጊዜ ሳይሆንም (ለእርዳታ) ተጣሩ::
અરબી તફસીરો:
وَعَجِبُوٓاْ أَن جَآءَهُم مُّنذِرٞ مِّنۡهُمۡۖ وَقَالَ ٱلۡكَٰفِرُونَ هَٰذَا سَٰحِرٞ كَذَّابٌ
4. ከእነርሱ መካከል የሆነ አስፈራሪ ስለመጣላቸውም ተደነቁ:: ከሓዲያንም አሉ: «ይህ ድግምተኛ ጠንቋይ ውሸታም ነው።
અરબી તફસીરો:
أَجَعَلَ ٱلۡأٓلِهَةَ إِلَٰهٗا وَٰحِدًاۖ إِنَّ هَٰذَا لَشَيۡءٌ عُجَابٞ
5. «አማልዕክቶችን አንድ አምላክ አደረጋቸውን? ይህ አስደናቂ ነገር ነው።» አሉ።
અરબી તફસીરો:
وَٱنطَلَقَ ٱلۡمَلَأُ مِنۡهُمۡ أَنِ ٱمۡشُواْ وَٱصۡبِرُواْ عَلَىٰٓ ءَالِهَتِكُمۡۖ إِنَّ هَٰذَا لَشَيۡءٞ يُرَادُ
6. ከእነርሱም መካከል ባላባቶቹ (እንዲህ) እያሉ አዘገሙ: «ሂዱ በአማልክቶቻችሁም መገዛት ላይ ጽኑ:: ይህ ከእኛ የሚፈለግ ነገር ነውና
અરબી તફસીરો:
مَا سَمِعۡنَا بِهَٰذَا فِي ٱلۡمِلَّةِ ٱلۡأٓخِرَةِ إِنۡ هَٰذَآ إِلَّا ٱخۡتِلَٰقٌ
7. «ይህንንም አስተምህሮት ከኋለኛይቱ (ከመጨረሻይቱ) ሃይማኖት አልሰማንም:: ይህ ውሸትን መፍጠር እንጂ ሌላ አይደለም።
અરબી તફસીરો:
أَءُنزِلَ عَلَيۡهِ ٱلذِّكۡرُ مِنۢ بَيۡنِنَاۚ بَلۡ هُمۡ فِي شَكّٖ مِّن ذِكۡرِيۚ بَل لَّمَّا يَذُوقُواْ عَذَابِ
8. «ከመካከላችን በእርሱ ላይ ብቻ ቁርኣን ተወረደን?» (እያሉ አዘገሙ።) ይልቁን እነርሱ ከግሳጼየ በመጠራጠር ውስጥ ናቸው:: በእርግጥም ቅጣትን ገና አልቀመሱም::
અરબી તફસીરો:
أَمۡ عِندَهُمۡ خَزَآئِنُ رَحۡمَةِ رَبِّكَ ٱلۡعَزِيزِ ٱلۡوَهَّابِ
9. ወይስ የአሸናፊውና የለጋሹ ጌታህ የአላህ የችሮታው መካዚኖች እነርሱ ዘንድ ናቸውን?
અરબી તફસીરો:
أَمۡ لَهُم مُّلۡكُ ٱلسَّمَٰوَٰتِ وَٱلۡأَرۡضِ وَمَا بَيۡنَهُمَاۖ فَلۡيَرۡتَقُواْ فِي ٱلۡأَسۡبَٰبِ
10. ወይስ የሰማይ የምድር እና የመካከላቸዉም ንግስና የእነርሱ ነውን? (ነው ካሉ) እስቲ በመሰላሎች ወደ ላይ ይውጡ::
અરબી તફસીરો:
جُندٞ مَّا هُنَالِكَ مَهۡزُومٞ مِّنَ ٱلۡأَحۡزَابِ
11. እነርሱም እዚያ ዘንድ ከአህዛብ ሁሉ ተሸናፊ የሆነ ሰራዊት ናቸው::
અરબી તફસીરો:
كَذَّبَتۡ قَبۡلَهُمۡ قَوۡمُ نُوحٖ وَعَادٞ وَفِرۡعَوۡنُ ذُو ٱلۡأَوۡتَادِ
12. ከእነርሱም በፊት የኑህ ህዝቦች፤ ዓድ እና የችካሎች ባለቤት የሆነው ፈርዖንም አስተባብለዋል።
અરબી તફસીરો:
وَثَمُودُ وَقَوۡمُ لُوطٖ وَأَصۡحَٰبُ لۡـَٔيۡكَةِۚ أُوْلَٰٓئِكَ ٱلۡأَحۡزَابُ
13. ሰሙድም፤ የሉጥ ሰዎችም፤ የአይካ ሰዎችም፤ አስተባበሉ:: እነዚህ አህዛቦቹ ናቸው::
અરબી તફસીરો:
إِن كُلٌّ إِلَّا كَذَّبَ ٱلرُّسُلَ فَحَقَّ عِقَابِ
14. ሁሉም መልዕክተኞችን ያስዋሹ እንጂ ሌላ አይደሉም:: ከዚያ ቅጣቴ ተረጋገጠባቸው::
અરબી તફસીરો:
وَمَا يَنظُرُ هَٰٓؤُلَآءِ إِلَّا صَيۡحَةٗ وَٰحِدَةٗ مَّا لَهَا مِن فَوَاقٖ
15. (መልዕክተኛችን ሙሐመድ ሆይ!) እነዚህ ያችን ለእርሷ መመለስ የሌላትን አንዲት ጩኸት ብቻ እንጂ ሌላን አይጠባበቁም::
અરબી તફસીરો:
وَقَالُواْ رَبَّنَا عَجِّل لَّنَا قِطَّنَا قَبۡلَ يَوۡمِ ٱلۡحِسَابِ
16. (በመሳለቅም) «ጌታችን ሆይ! ከምርመራው ቀን በፊት ቅጣታችንን አጣድፍልን» አሉ።
અરબી તફસીરો:
ٱصۡبِرۡ عَلَىٰ مَا يَقُولُونَ وَٱذۡكُرۡ عَبۡدَنَا دَاوُۥدَ ذَا ٱلۡأَيۡدِۖ إِنَّهُۥٓ أَوَّابٌ
17. (መልዕክተኛችን ሙሐመድ ሆይ!) በሚሉት ነገር ላይ ታገስ:: የሃኃይል ባለቤት የሆነውን ባሪያችንንም ዳውድን አውሳው:: እርሱ በጣም መላሳ ነው::
અરબી તફસીરો:
إِنَّا سَخَّرۡنَا ٱلۡجِبَالَ مَعَهُۥ يُسَبِّحۡنَ بِٱلۡعَشِيِّ وَٱلۡإِشۡرَاقِ
18. እኛ ተራራዎችን ከቀትር በኋላና በረፋዱም ከእርሱ ጋር የሚያወድሱ ሲሆን እንዲታዘዙት አገራንለት::
અરબી તફસીરો:
وَٱلطَّيۡرَ مَحۡشُورَةٗۖ كُلّٞ لَّهُۥٓ أَوَّابٞ
19. በራሪዎችንም (አእዋፍን) የሚሰበሰቡ ሆነው አገራንለት:: ሁሉም ለእርሱ ማወደስ የሚመላለስ ነው::
અરબી તફસીરો:
وَشَدَدۡنَا مُلۡكَهُۥ وَءَاتَيۡنَٰهُ ٱلۡحِكۡمَةَ وَفَصۡلَ ٱلۡخِطَابِ
20. ንግስናውንም አበረታንለት ጥበብንና ንግግርን መለየትንም ሰጠነው።
અરબી તફસીરો:
۞ وَهَلۡ أَتَىٰكَ نَبَؤُاْ ٱلۡخَصۡمِ إِذۡ تَسَوَّرُواْ ٱلۡمِحۡرَابَ
21. (መልዕክተኛችን ሙሐመድ ሆይ!) የተከራካሪዎቹ ወሬ መጥቶልሃልን? እልፍኙን (ምኩራቡን) በተንጠላጠሉ ጊዜ።
અરબી તફસીરો:
إِذۡ دَخَلُواْ عَلَىٰ دَاوُۥدَ فَفَزِعَ مِنۡهُمۡۖ قَالُواْ لَا تَخَفۡۖ خَصۡمَانِ بَغَىٰ بَعۡضُنَا عَلَىٰ بَعۡضٖ فَٱحۡكُم بَيۡنَنَا بِٱلۡحَقِّ وَلَا تُشۡطِطۡ وَٱهۡدِنَآ إِلَىٰ سَوَآءِ ٱلصِّرَٰطِ
22. በዳውድ ላይም በገቡ ጊዜ ከእነርሱም ሁኔታ በደነገጠ ጊዜ (እንዲህ) አሉት: «አትፍራ። እኛ ከፊላችን በከፊሉ ላይ ወሰን ያለፈ ሁለት ተከራካሪዎች ነን። በመካከላችንም በእውነት ፍረድ። አታዳላም። ወደ ትክክለኛው መንገድም ምራን።
અરબી તફસીરો:
إِنَّ هَٰذَآ أَخِي لَهُۥ تِسۡعٞ وَتِسۡعُونَ نَعۡجَةٗ وَلِيَ نَعۡجَةٞ وَٰحِدَةٞ فَقَالَ أَكۡفِلۡنِيهَا وَعَزَّنِي فِي ٱلۡخِطَابِ
23. «ይህ ወንድሜ ነው:: ለእርሱ ዘጠና ዘጠኝ ሴት በጎች አሉት ለእኔም አንዲት ሴት በግ አለችኝ ‹እርሷንም ለእኔ አድርጋት› አለኝ:: በንግግርም አሸነፈኝ።» አለው::
અરબી તફસીરો:
قَالَ لَقَدۡ ظَلَمَكَ بِسُؤَالِ نَعۡجَتِكَ إِلَىٰ نِعَاجِهِۦۖ وَإِنَّ كَثِيرٗا مِّنَ ٱلۡخُلَطَآءِ لَيَبۡغِي بَعۡضُهُمۡ عَلَىٰ بَعۡضٍ إِلَّا ٱلَّذِينَ ءَامَنُواْ وَعَمِلُواْ ٱلصَّٰلِحَٰتِ وَقَلِيلٞ مَّا هُمۡۗ وَظَنَّ دَاوُۥدُ أَنَّمَا فَتَنَّٰهُ فَٱسۡتَغۡفَرَ رَبَّهُۥ وَخَرَّۤ رَاكِعٗاۤ وَأَنَابَ۩
24. «ሴት በግህን ወደ በጎቹ ለመቀላቀል በመጠየቁ በእርግጥ በደለህ። ከተጋሪዎች ብዙዎቹ ከፊላቸው በከፊሉ ላይ ወሰን ያልፋሉ:: እነዚያ ያመኑትና መልካሞችን የሰሩት ብቻ ሲቀሩ፤ እነርሱም በጣም ጥቂቶች ናቸው።» አለ:: ዳውድም የፈተንነው መሆኑን ወዲያዉኑ አወቀ:: ከጌታዉም ምህረትን ለመነና ሰጋጅ ሆኖም ወደቀ። በመጸጸትም ተመለሰ:: {1}
{1} እዚህ አንድ ሱጁድ ይደረጋል
અરબી તફસીરો:
فَغَفَرۡنَا لَهُۥ ذَٰلِكَۖ وَإِنَّ لَهُۥ عِندَنَا لَزُلۡفَىٰ وَحُسۡنَ مَـَٔابٖ
25. ያንንም ማርነው። ለእርሱም እኛ ዘንድ የመቅረብ ክብር መልካም መመለሻም አለው።
અરબી તફસીરો:
يَٰدَاوُۥدُ إِنَّا جَعَلۡنَٰكَ خَلِيفَةٗ فِي ٱلۡأَرۡضِ فَٱحۡكُم بَيۡنَ ٱلنَّاسِ بِٱلۡحَقِّ وَلَا تَتَّبِعِ ٱلۡهَوَىٰ فَيُضِلَّكَ عَن سَبِيلِ ٱللَّهِۚ إِنَّ ٱلَّذِينَ يَضِلُّونَ عَن سَبِيلِ ٱللَّهِ لَهُمۡ عَذَابٞ شَدِيدُۢ بِمَا نَسُواْ يَوۡمَ ٱلۡحِسَابِ
26. (እኛም አልነው) «ዳውድ ሆይ! እኛ በምድር ላይ ምትክ አድርገንሀልና በሰዎች መካከል በእውነት ፍረድ:: የግል ዝንባሌህንም አትከተል:: ከአላህ መንገድ ያሳስተሃልና።» እነዚያ ከአላህ መንገድ የሚሳሳቱ ሁሉ የምርመራውን ቀን በመርሳታቸው ለእነርሱ ብርቱ ቅጣት አለባቸው::
અરબી તફસીરો:
وَمَا خَلَقۡنَا ٱلسَّمَآءَ وَٱلۡأَرۡضَ وَمَا بَيۡنَهُمَا بَٰطِلٗاۚ ذَٰلِكَ ظَنُّ ٱلَّذِينَ كَفَرُواْۚ فَوَيۡلٞ لِّلَّذِينَ كَفَرُواْ مِنَ ٱلنَّارِ
27. ሰማይን ምድርና በመካከላቸዉም ያለውን ሁሉ ለከንቱ አልፈጠርንም:: ይህ የእነዚያ የካዱት ሰዎች ጥርጣሬ ነው:: ለእነዚያም ለካዱት ሰዎች ሁሉ ከእሳት ወዮላቸው።
અરબી તફસીરો:
أَمۡ نَجۡعَلُ ٱلَّذِينَ ءَامَنُواْ وَعَمِلُواْ ٱلصَّٰلِحَٰتِ كَٱلۡمُفۡسِدِينَ فِي ٱلۡأَرۡضِ أَمۡ نَجۡعَلُ ٱلۡمُتَّقِينَ كَٱلۡفُجَّارِ
28. በእውነቱ እነዚያ ያመኑትና መልካም ተግባሮችን የሰሩትን ልክ በምድር ውስጥ እንደሚያጠፉት እናደርጋለንን? ወይስ አላህን ፈሪዎችን ልክ እንደ ከሓዲያን እናደርጋለን?
અરબી તફસીરો:
كِتَٰبٌ أَنزَلۡنَٰهُ إِلَيۡكَ مُبَٰرَكٞ لِّيَدَّبَّرُوٓاْ ءَايَٰتِهِۦ وَلِيَتَذَكَّرَ أُوْلُواْ ٱلۡأَلۡبَٰبِ
29. ይህ መጽሀፍ ወደ አንተ ያወረድነው ብሩክ መጽሀፍ ነው:: አናቅጽን እንዲያስተነትኑና የአእምሮ ባላቤቶችም እንዲገሰጹበት አወረድነው::
અરબી તફસીરો:
وَوَهَبۡنَا لِدَاوُۥدَ سُلَيۡمَٰنَۚ نِعۡمَ ٱلۡعَبۡدُ إِنَّهُۥٓ أَوَّابٌ
30. ለዳውድም ሱለይማንን ሰጠነው:: ሱለይማን ምን ያምር ባሪያ ነው:: እርሱ ወደ ጌታው መላሳ ነውና::
અરબી તફસીરો:
إِذۡ عُرِضَ عَلَيۡهِ بِٱلۡعَشِيِّ ٱلصَّٰفِنَٰتُ ٱلۡجِيَادُ
31. በእርሱ ላይ ከቀትር በኋላ በሶስት እግሮችና በአራተኛው እግር ኮቴ ጫፍ የሚቆሙ ጮሌ ፈረሶች በተቀረቡለት ጊዜ (የሆነዉን አስታውስ)::
અરબી તફસીરો:
فَقَالَ إِنِّيٓ أَحۡبَبۡتُ حُبَّ ٱلۡخَيۡرِ عَن ذِكۡرِ رَبِّي حَتَّىٰ تَوَارَتۡ بِٱلۡحِجَابِ
32. (እንዲህም) አለ: «ጸሀይ በግርዶ እስከተደበቀች ድረስ ጌታየን ከማስታወስ ፈንታ ፈረስን መውደድን መረጥኩ!
અરબી તફસીરો:
رُدُّوهَا عَلَيَّۖ فَطَفِقَ مَسۡحَۢا بِٱلسُّوقِ وَٱلۡأَعۡنَاقِ
33. «በሉ ፈረሶችን ወደ እኔ መልሷቸው።» (አለ)። ከዚያም እግሮቻቸዉንና አንገቶቻቸዉን መቁረጥ ያዘ::
અરબી તફસીરો:
وَلَقَدۡ فَتَنَّا سُلَيۡمَٰنَ وَأَلۡقَيۡنَا عَلَىٰ كُرۡسِيِّهِۦ جَسَدٗا ثُمَّ أَنَابَ
34. ሱለይማንንም በእርግጥ ፈተንነው። በመንበሩም ላይ የሆነ አካልን ጣልን:: ከዚያም በመጸጸት ተመለሰ።
અરબી તફસીરો:
قَالَ رَبِّ ٱغۡفِرۡ لِي وَهَبۡ لِي مُلۡكٗا لَّا يَنۢبَغِي لِأَحَدٖ مِّنۢ بَعۡدِيٓۖ إِنَّكَ أَنتَ ٱلۡوَهَّابُ
35. «ጌታዬ ሆይ! ማረኝ ከእኔ በኋላ ለአንድም የማይገባን ንግስናንም ስጠኝ:: ለጋሹ አንተ ብቻ ነህና» አለ።
અરબી તફસીરો:
فَسَخَّرۡنَا لَهُ ٱلرِّيحَ تَجۡرِي بِأَمۡرِهِۦ رُخَآءً حَيۡثُ أَصَابَ
36. ንፋስንም በትዕዛዙ ወደ ፈለገበት ስፍራ ልዝብ ሆና የምትነፍስ ስትሆን ገራንለት::
અરબી તફસીરો:
وَٱلشَّيَٰطِينَ كُلَّ بَنَّآءٖ وَغَوَّاصٖ
37. ሰይጣናትንም ገንቢዎችንና ሰማጮችን ሁሉ ገራንለት::
અરબી તફસીરો:
وَءَاخَرِينَ مُقَرَّنِينَ فِي ٱلۡأَصۡفَادِ
38. ሌሎችንም በሰንሰለቶች ተቆራኞችን ገራንለት::
અરબી તફસીરો:
هَٰذَا عَطَآؤُنَا فَٱمۡنُنۡ أَوۡ أَمۡسِكۡ بِغَيۡرِ حِسَابٖ
39. ይህ ስጦታችን ነው ያለ ግምት ለግስ:: ወይም ጨብጥ (አልነው)።
અરબી તફસીરો:
وَإِنَّ لَهُۥ عِندَنَا لَزُلۡفَىٰ وَحُسۡنَ مَـَٔابٖ
40. ለእርሱም እኛ ዘንድ መቅረብ መልካም መመለሻም በእርግጥ አለው::
અરબી તફસીરો:
وَٱذۡكُرۡ عَبۡدَنَآ أَيُّوبَ إِذۡ نَادَىٰ رَبَّهُۥٓ أَنِّي مَسَّنِيَ ٱلشَّيۡطَٰنُ بِنُصۡبٖ وَعَذَابٍ
41. (መልዕክተኛችን ሙሐመድ ሆይ!) ባሪያችን አዩብንም: «እኔ ሰይጣን በጉዳትና በስቃይ ነካኝ» ሲል ጌታውን በተጣራ ጊዜ።የሆነውን አስታውስ
અરબી તફસીરો:
ٱرۡكُضۡ بِرِجۡلِكَۖ هَٰذَا مُغۡتَسَلُۢ بَارِدٞ وَشَرَابٞ
42. በእግርህ ምድርን ምታ:: ይህ ቀዝቃዛ መታጠቢያ መጠጥም ነው (ተባለ)::
અરબી તફસીરો:
وَوَهَبۡنَا لَهُۥٓ أَهۡلَهُۥ وَمِثۡلَهُم مَّعَهُمۡ رَحۡمَةٗ مِّنَّا وَذِكۡرَىٰ لِأُوْلِي ٱلۡأَلۡبَٰبِ
43. ለእርሱ ከእኛ ዘንድ በሆነ ችሮታ ባለ አእምሮዎችንም ለመገሰጽ ቤተሰቦቹንም ከእነርሱ ጋር መሰላቸውን ሰጠነው።
અરબી તફસીરો:
وَخُذۡ بِيَدِكَ ضِغۡثٗا فَٱضۡرِب بِّهِۦ وَلَا تَحۡنَثۡۗ إِنَّا وَجَدۡنَٰهُ صَابِرٗاۚ نِّعۡمَ ٱلۡعَبۡدُ إِنَّهُۥٓ أَوَّابٞ
44. «በእጅህ ጭብጥ አርጩሜን ያዝ በእርሱም (ሚስትህን) ምታ። ማላህንም አታፍርስ።» (አልነው) እነሆ ታጋሽ ሆኖ አገኘነው:: ምን ያምር ባሪያ ነው:: እርሱም በጣም መላሳ ነው።
અરબી તફસીરો:
وَٱذۡكُرۡ عِبَٰدَنَآ إِبۡرَٰهِيمَ وَإِسۡحَٰقَ وَيَعۡقُوبَ أُوْلِي ٱلۡأَيۡدِي وَٱلۡأَبۡصَٰرِ
45. (መልዕክተኛችን ሙሐመድ ሆይ!) እንዚያን የኅይልና የማስተዋል ባለቤቶች የሆኑትን ባሮቻችንም ኢብራሂምን ኢስሐቅንና ያዕቆብንም ለህዝቦችህ አውሳላቸው።
અરબી તફસીરો:
إِنَّآ أَخۡلَصۡنَٰهُم بِخَالِصَةٖ ذِكۡرَى ٱلدَّارِ
46. እኛ ጥሩ በሆነች ጠባይ መረጥናቸው፤ እርሷም የመጨረሻይቱን አገር ማስታወስ ናት::
અરબી તફસીરો:
وَإِنَّهُمۡ عِندَنَا لَمِنَ ٱلۡمُصۡطَفَيۡنَ ٱلۡأَخۡيَارِ
47. እነርሱም እኛ ዘንድ ከመልካሞቹ ምርጦች ናቸው::
અરબી તફસીરો:
وَٱذۡكُرۡ إِسۡمَٰعِيلَ وَٱلۡيَسَعَ وَذَا ٱلۡكِفۡلِۖ وَكُلّٞ مِّنَ ٱلۡأَخۡيَارِ
48. (መልዕክተኛችን ሙሐመድ ሆይ!) ኢስማኢልንም፤ ኢልያስንም፤ ዙልኪፍልንም አውሳ፤ ሁሉም ከበላጮቹ ናቸው::
અરબી તફસીરો:
هَٰذَا ذِكۡرٞۚ وَإِنَّ لِلۡمُتَّقِينَ لَحُسۡنَ مَـَٔابٖ
49. (መልዕክተኛችን ሙሐመድ ሆይ!) ይህ መልካም ዝና ነው:: አላህን ለሚፈሩም በእርግጥ ውብ የሆነ መመለሻ አላቸው።
અરબી તફસીરો:
جَنَّٰتِ عَدۡنٖ مُّفَتَّحَةٗ لَّهُمُ ٱلۡأَبۡوَٰبُ
50. በሮቻቸው ለእነርሱ የተከፈቱ ሲሆኑ የመኖሪያ ገነቶች አሏቸው::
અરબી તફસીરો:
مُتَّكِـِٔينَ فِيهَا يَدۡعُونَ فِيهَا بِفَٰكِهَةٖ كَثِيرَةٖ وَشَرَابٖ
51. በእርሷ ውስጥ የተደገፉ ሆነው በውስጧ በብዙ እሸቶችና በመጠጥም ያዝዛሉ::
અરબી તફસીરો:
۞ وَعِندَهُمۡ قَٰصِرَٰتُ ٱلطَّرۡفِ أَتۡرَابٌ
52. እነርሱ ዘንድም ዓይኖቻቸውን በባሎቻቸው ላይ አሳጣሪዎች እኩያዎች ሴቶች አሉ::
અરબી તફસીરો:
هَٰذَا مَا تُوعَدُونَ لِيَوۡمِ ٱلۡحِسَابِ
53. ይህ ለምርመራው ቀን የምትቀጠሩት ተስፋ ነው::
અરબી તફસીરો:
إِنَّ هَٰذَا لَرِزۡقُنَا مَا لَهُۥ مِن نَّفَادٍ
54. ይህ ሲሳያችን ነው:: ለእርሱ ምንም ማለቅ የለዉም::
અરબી તફસીરો:
هَٰذَاۚ وَإِنَّ لِلطَّٰغِينَ لَشَرَّ مَـَٔابٖ
55. ይህ (ለትክክለኛ አማኞች ሲሆን።) ለጠማሞችም በጣም የከፋ መመለሻ አላቸው::
અરબી તફસીરો:
جَهَنَّمَ يَصۡلَوۡنَهَا فَبِئۡسَ ٱلۡمِهَادُ
56. የሚገቧት ስትሆን ገሀነም አለቻቸው:: ምንጣፊቱም ምንኛ ከፋች::
અરબી તફસીરો:
هَٰذَا فَلۡيَذُوقُوهُ حَمِيمٞ وَغَسَّاقٞ
57. ይህ ለከሓዲያን ነው:: ይቅመሱትም የፈላ ውሃና እዥ ነው::
અરબી તફસીરો:
وَءَاخَرُ مِن شَكۡلِهِۦٓ أَزۡوَٰجٌ
58. ሌላም እነርሱን ከመሰሉ ብዙ አይነቶች አሉ::
અરબી તફસીરો:
هَٰذَا فَوۡجٞ مُّقۡتَحِمٞ مَّعَكُمۡ لَا مَرۡحَبَۢا بِهِمۡۚ إِنَّهُمۡ صَالُواْ ٱلنَّارِ
59. ይህ ከናንተ ጋር በመጋፈጥ ገቢ ቡድን ነው (ይባላሉ):: ለእነርሱ አይስፋቸዉም:: እነርሱ እሳትን ገቢዎች ናቸውና (ይላሉ)::
અરબી તફસીરો:
قَالُواْ بَلۡ أَنتُمۡ لَا مَرۡحَبَۢا بِكُمۡۖ أَنتُمۡ قَدَّمۡتُمُوهُ لَنَاۖ فَبِئۡسَ ٱلۡقَرَارُ
60. ተከታዮቹም ይላሉ፡- «ይልቁን እናንተ አይስፋችሁ። እናንተ ክህደቱን ለእኛ አቀረባችሁት መርጊያይቱም ገሀነም ከፋች።»
અરબી તફસીરો:
قَالُواْ رَبَّنَا مَن قَدَّمَ لَنَا هَٰذَا فَزِدۡهُ عَذَابٗا ضِعۡفٗا فِي ٱلنَّارِ
61. «ጌታችን ሆይ! ይህንን ያቀረበልንን ሰው በእሳት ውስጥ ድርብ ቅጣትን ጨምርለት» ይላሉ።
અરબી તફસીરો:
وَقَالُواْ مَا لَنَا لَا نَرَىٰ رِجَالٗا كُنَّا نَعُدُّهُم مِّنَ ٱلۡأَشۡرَارِ
62. ይላሉም «ለእኛ ምን አለን? ከመጥፎዎች እንቆጥራቸው የነበሩትን ሰዎች እዚህ አናይምሳ።
અરબી તફસીરો:
أَتَّخَذۡنَٰهُمۡ سِخۡرِيًّا أَمۡ زَاغَتۡ عَنۡهُمُ ٱلۡأَبۡصَٰرُ
63. «(ሳይገባቸው) መቀለጃ አድርገን ይዘናቸው ነውን? ወይስ ዓይኖቻችን ከእነርሱ ዋለሉ?»
અરબી તફસીરો:
إِنَّ ذَٰلِكَ لَحَقّٞ تَخَاصُمُ أَهۡلِ ٱلنَّارِ
64. ይህ በእርግጥ እውነት ነው:: እርሱም የእሳት ሰዎች የእርስ በርስ የመካሰስ ወሬ ነው::
અરબી તફસીરો:
قُلۡ إِنَّمَآ أَنَا۠ مُنذِرٞۖ وَمَا مِنۡ إِلَٰهٍ إِلَّا ٱللَّهُ ٱلۡوَٰحِدُ ٱلۡقَهَّارُ
65. (መልዕክተኛችን ሙሐመድ ሆይ!) በል: «እኔ አስፈራሪ ብቻ ነኝ። ኃያልና አንድ ከሆነ አላህ በስተቀር ምንም አምላክ የለም።
અરબી તફસીરો:
رَبُّ ٱلسَّمَٰوَٰتِ وَٱلۡأَرۡضِ وَمَا بَيۡنَهُمَا ٱلۡعَزِيزُ ٱلۡغَفَّٰرُ
66. «የሰማያትና የምድር በመካከላቸዉም ያለው ሁሉ ጌታ አሸናፊና መሐሪ ነው።»
અરબી તફસીરો:
قُلۡ هُوَ نَبَؤٌاْ عَظِيمٌ
67. (መልዕክተኛችን ሙሐመድ ሆይ!) በል: «እርሱ (ቁርኣን) ታላቅ ዜና ነው።
અરબી તફસીરો:
أَنتُمۡ عَنۡهُ مُعۡرِضُونَ
68. «እናንተ ከእርሱ ዘንጊዎች ናችሁ።
અરબી તફસીરો:
مَا كَانَ لِيَ مِنۡ عِلۡمِۭ بِٱلۡمَلَإِ ٱلۡأَعۡلَىٰٓ إِذۡ يَخۡتَصِمُونَ
69. «በሚከራከሩ ጊዜ በላይኛዋ ሰራዊት ለእኔ ምንም እውቀት አልነበረኝም።
અરબી તફસીરો:
إِن يُوحَىٰٓ إِلَيَّ إِلَّآ أَنَّمَآ أَنَا۠ نَذِيرٞ مُّبِينٌ
70. «ወደ እኔም አስፈራሪ ገላጭ በመሆኔ እንጂ በሌላ አይወርድልኝም።» በል::
અરબી તફસીરો:
إِذۡ قَالَ رَبُّكَ لِلۡمَلَٰٓئِكَةِ إِنِّي خَٰلِقُۢ بَشَرٗا مِّن طِينٖ
71. (መልዕክተኛችን ሙሐመድ ሆይ!) «ጌታህ ለመላዕክት እኔ ሰውን ከጭቃ ፈጣሪ ነኝ ባለ ጊዜ (የነበረዉን አስታውስ)::
અરબી તફસીરો:
فَإِذَا سَوَّيۡتُهُۥ وَنَفَخۡتُ فِيهِ مِن رُّوحِي فَقَعُواْ لَهُۥ سَٰجِدِينَ
72. «ፍጥረቱንም ባስተካከልኩና ከመንፈሴ በነፋሁበትም ጊዜ ሁላችሁም ለእርሱ ሰጋጆች ሆናችሁ ውደቁ።» (አልኩ።)
અરબી તફસીરો:
فَسَجَدَ ٱلۡمَلَٰٓئِكَةُ كُلُّهُمۡ أَجۡمَعُونَ
73. መላው መላዕክትም በአንድነት ሰገዱ።
અરબી તફસીરો:
إِلَّآ إِبۡلِيسَ ٱسۡتَكۡبَرَ وَكَانَ مِنَ ٱلۡكَٰفِرِينَ
74. ዲያብሎስ ብቻ ሲቀር። ኮራም። ከከሓዲያንም ሆነ።
અરબી તફસીરો:
قَالَ يَٰٓإِبۡلِيسُ مَا مَنَعَكَ أَن تَسۡجُدَ لِمَا خَلَقۡتُ بِيَدَيَّۖ أَسۡتَكۡبَرۡتَ أَمۡ كُنتَ مِنَ ٱلۡعَالِينَ
75. አላህ «ዲያብሎስ ሆይ! በሁለት እጆቼ ለፈጠርኩት ለአደም ከመስገድ ምን ከለከለህ? ኮርተህ ነው? ወይስ ፊቱኑ ከትዕቢተኞች ነበርክ?» አለው።
અરબી તફસીરો:
قَالَ أَنَا۠ خَيۡرٞ مِّنۡهُ خَلَقۡتَنِي مِن نَّارٖ وَخَلَقۡتَهُۥ مِن طِينٖ
76. ዲያብሎስም «እኔ ከእርሱ የተሻልኩ ነኝ። እኔን ከእሳት የፈጠርከኝ ስትሆን እሱን ግን ከጭቃ ነው የፈጠርከው።» አለ።
અરબી તફસીરો:
قَالَ فَٱخۡرُجۡ مِنۡهَا فَإِنَّكَ رَجِيمٞ
77. (አላህም) አለ፡- «ከእርሷ ውጣ። አንተ የተባረርክ ነህና።
અરબી તફસીરો:
وَإِنَّ عَلَيۡكَ لَعۡنَتِيٓ إِلَىٰ يَوۡمِ ٱلدِّينِ
78. «እርግማኔም እስከ ፍርዱ ቀን ድረስ ባንተ ላይ ይሁን።» አለው።
અરબી તફસીરો:
قَالَ رَبِّ فَأَنظِرۡنِيٓ إِلَىٰ يَوۡمِ يُبۡعَثُونَ
79. (ዲያብሎስም) «ጌታየ ሆይ! እስከሚቀሰቀሱበት ቀን ድረስ እባክህ አቆየኝ።» አለ
અરબી તફસીરો:
قَالَ فَإِنَّكَ مِنَ ٱلۡمُنظَرِينَ
80. (አላህም) አለ፡- «አንተ ከሚቆዩት ነህ።
અરબી તફસીરો:
إِلَىٰ يَوۡمِ ٱلۡوَقۡتِ ٱلۡمَعۡلُومِ
81. «እስከ ታወቀው ወቅት ቀን ድረስ።»
અરબી તફસીરો:
قَالَ فَبِعِزَّتِكَ لَأُغۡوِيَنَّهُمۡ أَجۡمَعِينَ
82. (እርሱም) አለ: «በአሸናፊነትህ ይሁንብኝ ሁላቸዉንም አሳስታቸዋለሁ።
અરબી તફસીરો:
إِلَّا عِبَادَكَ مِنۡهُمُ ٱلۡمُخۡلَصِينَ
83. «ከእነርሱ መካከል ምርጥ ባሮችህ ብቻ ሲቀሩ።»
અરબી તફસીરો:
قَالَ فَٱلۡحَقُّ وَٱلۡحَقَّ أَقُولُ
84. (አላህም) አለ: «እውነቱም ከእኔ ነው:: እውነትንም እላለሁ(እናገራለሁ)።
અરબી તફસીરો:
لَأَمۡلَأَنَّ جَهَنَّمَ مِنكَ وَمِمَّن تَبِعَكَ مِنۡهُمۡ أَجۡمَعِينَ
85. «በአንተና ከእነርሱ መካከል በተከተሉህም ባንድ ላይ ገሀነምን በእርግጥ እሞላታለሁ» አለው።
અરબી તફસીરો:
قُلۡ مَآ أَسۡـَٔلُكُمۡ عَلَيۡهِ مِنۡ أَجۡرٖ وَمَآ أَنَا۠ مِنَ ٱلۡمُتَكَلِّفِينَ
86.(መልዕክተኛችን ሙሐመድ ሆይ!) በል: «በእርሱ ላይ ምንም ዋጋ አል ጠይቃችሁም:: እኔም ከተግደርዳሪዎቹ አይደለሁም።
અરબી તફસીરો:
إِنۡ هُوَ إِلَّا ذِكۡرٞ لِّلۡعَٰلَمِينَ
87. «እርሱ (ቁርኣን) ለዓለማት መገሰጫ እንጂ ሌላ አይደለም።
અરબી તફસીરો:
وَلَتَعۡلَمُنَّ نَبَأَهُۥ بَعۡدَ حِينِۭ
88. «የትንቢቱን እውነትነት ከጊዜ በኋላም ቢሆን በእርግጥ ታውቁታላችሁ።» በላቸው።
અરબી તફસીરો:
 
શબ્દોનું ભાષાંતર સૂરહ: સૉદ
સૂરહ માટે અનુક્રમણિકા પેજ નંબર
 
કુરઆન મજીદના શબ્દોનું ભાષાંતર - એમ્હારિક ભાષાંતર - ઝૈન - ભાષાંતરોની અનુક્રમણિકા

અમ્હેરિક ભાષાતર

બંધ કરો