Check out the new design

કુરઆન મજીદના શબ્દોનું ભાષાંતર - એમ્હારિક ભાષામાં અનુવાદ - આફ્રિકન એકેડમી * - ભાષાંતરોની અનુક્રમણિકા


શબ્દોનું ભાષાંતર સૂરહ: અન્ નિસા   આયત:
۞ لَّا يُحِبُّ ٱللَّهُ ٱلۡجَهۡرَ بِٱلسُّوٓءِ مِنَ ٱلۡقَوۡلِ إِلَّا مَن ظُلِمَۚ وَكَانَ ٱللَّهُ سَمِيعًا عَلِيمًا
148. አላህ በክፉ ንግግር መጮህን ከተበደለ ሰው ጩኸት በስተቀር አይወድም:: አላህ ሁሉን ሰሚ እና ሁሉን አዋቂ ነውና::
અરબી તફસીરો:
إِن تُبۡدُواْ خَيۡرًا أَوۡ تُخۡفُوهُ أَوۡ تَعۡفُواْ عَن سُوٓءٖ فَإِنَّ ٱللَّهَ كَانَ عَفُوّٗا قَدِيرًا
149. ደግ ነገርን ብትገልጹ ወይም ብትደብቁት ወይም ከመጥፎ ነገር (በደል) ይቅርታ ብታደርጉ አላህ ይቅር ባይ እና ቻይ ነው::
અરબી તફસીરો:
إِنَّ ٱلَّذِينَ يَكۡفُرُونَ بِٱللَّهِ وَرُسُلِهِۦ وَيُرِيدُونَ أَن يُفَرِّقُواْ بَيۡنَ ٱللَّهِ وَرُسُلِهِۦ وَيَقُولُونَ نُؤۡمِنُ بِبَعۡضٖ وَنَكۡفُرُ بِبَعۡضٖ وَيُرِيدُونَ أَن يَتَّخِذُواْ بَيۡنَ ذَٰلِكَ سَبِيلًا
150. እነዚያ በአላህና በመልዕክተኞቹ የሚክዱ፤ በአላህና በመልዕክተኞቹም መካከል መለየትን የሚፈልጉና «በከፊሉ እናምናለን በከፊሉ ደግሞ እንክዳለን» የሚሉ ሁሉ በዚህ መካከል መንገድን ሊይዙ የሚፈልጉ፣
અરબી તફસીરો:
أُوْلَٰٓئِكَ هُمُ ٱلۡكَٰفِرُونَ حَقّٗاۚ وَأَعۡتَدۡنَا لِلۡكَٰفِرِينَ عَذَابٗا مُّهِينٗا
151. በእውነቱ እነዚያ ከሓዲያን እነርሱው ናቸው:: ለከሓዲያንም አዋራጅን ቅጣት አዘጋጅተናል::
અરબી તફસીરો:
وَٱلَّذِينَ ءَامَنُواْ بِٱللَّهِ وَرُسُلِهِۦ وَلَمۡ يُفَرِّقُواْ بَيۡنَ أَحَدٖ مِّنۡهُمۡ أُوْلَٰٓئِكَ سَوۡفَ يُؤۡتِيهِمۡ أُجُورَهُمۡۚ وَكَانَ ٱللَّهُ غَفُورٗا رَّحِيمٗا
152. እነዚያ በአላህና በመልዕክተኞቹ ያመኑ፤ ከእነርሱም መካከል በአንዱም ያልለዩ ሰዎች እነዚያ ምንዳዎቻቸው በእርግጥ ይሰጣቸዋል:: አላህ መሀሪና አዛኝ ነውና::
અરબી તફસીરો:
يَسۡـَٔلُكَ أَهۡلُ ٱلۡكِتَٰبِ أَن تُنَزِّلَ عَلَيۡهِمۡ كِتَٰبٗا مِّنَ ٱلسَّمَآءِۚ فَقَدۡ سَأَلُواْ مُوسَىٰٓ أَكۡبَرَ مِن ذَٰلِكَ فَقَالُوٓاْ أَرِنَا ٱللَّهَ جَهۡرَةٗ فَأَخَذَتۡهُمُ ٱلصَّٰعِقَةُ بِظُلۡمِهِمۡۚ ثُمَّ ٱتَّخَذُواْ ٱلۡعِجۡلَ مِنۢ بَعۡدِ مَا جَآءَتۡهُمُ ٱلۡبَيِّنَٰتُ فَعَفَوۡنَا عَن ذَٰلِكَۚ وَءَاتَيۡنَا مُوسَىٰ سُلۡطَٰنٗا مُّبِينٗا
153. (መልዕክተኛችን ሙሐመድ ሆይ!) የመጽሐፉ ባለቤቶች እነርሱ ላይ ከሰማይ መጽሐፍን እንድታወርድ ይጠይቁሃል:: ከዚህም የከበደን ጥያቄ ከዚህ በፊት ሙሳን በእርግጥ ጠይቀዋል:: «አላህን በግልጽ አሳየን።» ብለዋል:: በበደላቸዉም ምክንያት መብረቅ ያዘቻቸው:: ከዚያም ተዓምራት ከመጡላቸው በኋላ ወይፈኑን አምላክ አድረገው ያዙ:: ከዚያ ያንን ይቅር አልን:: ሙሳንም ግልጽ ስልጣን ሰጠነው::
અરબી તફસીરો:
وَرَفَعۡنَا فَوۡقَهُمُ ٱلطُّورَ بِمِيثَٰقِهِمۡ وَقُلۡنَا لَهُمُ ٱدۡخُلُواْ ٱلۡبَابَ سُجَّدٗا وَقُلۡنَا لَهُمۡ لَا تَعۡدُواْ فِي ٱلسَّبۡتِ وَأَخَذۡنَا مِنۡهُم مِّيثَٰقًا غَلِيظٗا
154. በቃል ኪዳናቸው ምክንያት የጡር ተራራን ከበላያቸው አነሳን:: ለእነርሱም «ደጃፍን ስትገቡ አጎንብሳችሁ ግቡ።» አልን:: ለእነርሱም «በሰንበት ቀን ትዕዛዝን አትተላለፉ።» አልን:: ከእነርሱም ከባድን ቃል ኪዳን ያዝን::
અરબી તફસીરો:
 
શબ્દોનું ભાષાંતર સૂરહ: અન્ નિસા
સૂરહ માટે અનુક્રમણિકા પેજ નંબર
 
કુરઆન મજીદના શબ્દોનું ભાષાંતર - એમ્હારિક ભાષામાં અનુવાદ - આફ્રિકન એકેડમી - ભાષાંતરોની અનુક્રમણિકા

તેનું અનુવાદ મુહમ્મદ ઝૈન ઝહરુદ્ દીન દ્વારા કરવામાં આવ્યું. આફ્રિકા એકેડમી દ્વારા પ્રકાશિત.

બંધ કરો