કુરઆન મજીદના શબ્દોનું ભાષાંતર - એમ્હારિક ભાષાંતર - ઝૈન * - ભાષાંતરોની અનુક્રમણિકા


શબ્દોનું ભાષાંતર સૂરહ: અલ્ હાકકહ   આયત:

ሱረቱ አል ሓቃህ

ٱلۡحَآقَّةُ
1. እውነትን አረጋጋጪቱ (ትንሳኤ)::
અરબી તફસીરો:
مَا ٱلۡحَآقَّةُ
2. አረጋጋጪቱ (እርሷ) ምንድን ናት!
અરબી તફસીરો:
وَمَآ أَدۡرَىٰكَ مَا ٱلۡحَآقَّةُ
3. (መልዕክተኛችን ሙሐመድ ሆይ!) አረጋግጪቱም ምን እንደሆነች ምን አሳወቀህ?
અરબી તફસીરો:
كَذَّبَتۡ ثَمُودُ وَعَادُۢ بِٱلۡقَارِعَةِ
4. የሰሙድና የዓድ ህዝቦች በቆርቋሪይቱ (ትንሳኤ) ቀን አስተባበሉ::
અરબી તફસીરો:
فَأَمَّا ثَمُودُ فَأُهۡلِكُواْ بِٱلطَّاغِيَةِ
5. የሰሙድ ህዝቦችማ ወሰን በሌላት ነፋስ ጩኸት ተጠፉ::
અરબી તફસીરો:
وَأَمَّا عَادٞ فَأُهۡلِكُواْ بِرِيحٖ صَرۡصَرٍ عَاتِيَةٖ
6. የዓድ ህዝቦችማ በኃይል በምትንሻሻ ብርቱ ነፋስ ተጠፉ::
અરબી તફસીરો:
سَخَّرَهَا عَلَيۡهِمۡ سَبۡعَ لَيَالٖ وَثَمَٰنِيَةَ أَيَّامٍ حُسُومٗاۖ فَتَرَى ٱلۡقَوۡمَ فِيهَا صَرۡعَىٰ كَأَنَّهُمۡ أَعۡجَازُ نَخۡلٍ خَاوِيَةٖ
7. ተከታታይ በሆነ ሰባት ሌሊቶችና ስምንት ቀናቶች ውስጥ በእነርሱ ላይ ለቀቃት:: ህዝቦችንም፤ በውስጧ የተጣሉ ሆነው ልክ ክፍት እደሆኑ የበሰበሱ የዘንባባ ግንዶች ታያቸዋለህ::
અરબી તફસીરો:
فَهَلۡ تَرَىٰ لَهُم مِّنۢ بَاقِيَةٖ
8. ከእነርሱ መካከል ቀሪን ታያለህን?
અરબી તફસીરો:
وَجَآءَ فِرۡعَوۡنُ وَمَن قَبۡلَهُۥ وَٱلۡمُؤۡتَفِكَٰتُ بِٱلۡخَاطِئَةِ
9. ፈርዖን፤ ከበፊቱ የነበሩትን ሰዎችም፤ ተገልባጮችም (የሉጥ ሰዎች ከተሞች) ኃጢአት ፈጸሙ።
અરબી તફસીરો:
فَعَصَوۡاْ رَسُولَ رَبِّهِمۡ فَأَخَذَهُمۡ أَخۡذَةٗ رَّابِيَةً
10. የጌታቸውንም መልዕክተኛ ትዕዛዝ ጣሱ፤ የበረታችንም ቅጣት ቀጣቸው::
અરબી તફસીરો:
إِنَّا لَمَّا طَغَا ٱلۡمَآءُ حَمَلۡنَٰكُمۡ فِي ٱلۡجَارِيَةِ
11. እኛ ውሃው ባየለ ጊዜ በተንሳፋፊይቱ ታንኳ ውስጥ ጫንናችሁ::
અરબી તફસીરો:
لِنَجۡعَلَهَا لَكُمۡ تَذۡكِرَةٗ وَتَعِيَهَآ أُذُنٞ وَٰعِيَةٞ
12. ይህንም ያደረግነው ለእናንተ መገሰጫ ልናደርጋትና አጥኚ የሆነችም ጆሮ ታጠናት ዘንድ ነው::
અરબી તફસીરો:
فَإِذَا نُفِخَ فِي ٱلصُّورِ نَفۡخَةٞ وَٰحِدَةٞ
13. በቀንዱ አንዲት መነፋት በተነፋች ጊዜ::
અરબી તફસીરો:
وَحُمِلَتِ ٱلۡأَرۡضُ وَٱلۡجِبَالُ فَدُكَّتَا دَكَّةٗ وَٰحِدَةٗ
14. ምድርና ጋራዎች (ከየስፍራቸው) በተነሱና አንዲትን መሰባበር በተሰባበሩ ጊዜ፤
અરબી તફસીરો:
فَيَوۡمَئِذٖ وَقَعَتِ ٱلۡوَاقِعَةُ
15. በዚያ ቀን (ትንሳኤ) ትከሰታለች::
અરબી તફસીરો:
وَٱنشَقَّتِ ٱلسَّمَآءُ فَهِيَ يَوۡمَئِذٖ وَاهِيَةٞ
16. ሰማይም ትቀደዳለች:: በመሆኑም እርሷ በዚያ ቀን ደካማ ናት፤
અરબી તફસીરો:
وَٱلۡمَلَكُ عَلَىٰٓ أَرۡجَآئِهَاۚ وَيَحۡمِلُ عَرۡشَ رَبِّكَ فَوۡقَهُمۡ يَوۡمَئِذٖ ثَمَٰنِيَةٞ
17. መላዕክትም በየጫፎቿ ላይ ይሆናሉ:: የጌታህንም ዓርሽ በዚያ ቀን ስምንት መላዕክት ከበላያቸው ይሸከማሉ::
અરબી તફસીરો:
يَوۡمَئِذٖ تُعۡرَضُونَ لَا تَخۡفَىٰ مِنكُمۡ خَافِيَةٞ
18. በዚያ ቀን ከናንተ ተደባቂ (ነገሮች) የማይደበቁ ሲሆኑ ትቀረባላችሁ::
અરબી તફસીરો:
فَأَمَّا مَنۡ أُوتِيَ كِتَٰبَهُۥ بِيَمِينِهِۦ فَيَقُولُ هَآؤُمُ ٱقۡرَءُواْ كِتَٰبِيَهۡ
19. ያ መጽሀፉን በቀኝ እጁ የተሰጠ ሰውማ (ለጓደኞቹ እንዲህ) ይላል: «እንኩ መጽሐፌን አንብቡ፤
અરબી તફસીરો:
إِنِّي ظَنَنتُ أَنِّي مُلَٰقٍ حِسَابِيَهۡ
20. «እኔ ምርመራየን የምገናኝ መሆኔን አረጋገጥኩ።» (ይላል)
અરબી તફસીરો:
فَهُوَ فِي عِيشَةٖ رَّاضِيَةٖ
21. እርሱም በተወደደች ኑሮ ውስጥ ይሆናል::
અરબી તફસીરો:
فِي جَنَّةٍ عَالِيَةٖ
22. በከፍተኛይቱ ገነት ውስጥ፤
અરબી તફસીરો:
قُطُوفُهَا دَانِيَةٞ
23. ፍሬዎቿ ቅርቦች የሆኑ::
અરબી તફસીરો:
كُلُواْ وَٱشۡرَبُواْ هَنِيٓـَٔۢا بِمَآ أَسۡلَفۡتُمۡ فِي ٱلۡأَيَّامِ ٱلۡخَالِيَةِ
24. በአለፉት ቀናት ውስጥ (በምድረ ዓለም) ባስቀደማችሁት ምክንያት ብሉ፤ ጠጡም ይባላሉ::
અરબી તફસીરો:
وَأَمَّا مَنۡ أُوتِيَ كِتَٰبَهُۥ بِشِمَالِهِۦ فَيَقُولُ يَٰلَيۡتَنِي لَمۡ أُوتَ كِتَٰبِيَهۡ
25. ያ መጽሐፉን በግራው የተሰጠ ሰው ደግሞ (እንዲህ) ይላል: «ዋ ጥፋቴ ምነው መጽሐፌን ባልተሰጠሁ፤
અરબી તફસીરો:
وَلَمۡ أَدۡرِ مَا حِسَابِيَهۡ
26. «ምርመራዬም ምን እንደሆነ ባላወቅሁ፤
અરબી તફસીરો:
يَٰلَيۡتَهَا كَانَتِ ٱلۡقَاضِيَةَ
27. «ሞት ምነው የህይወቴ የመጨረሻ ፍፃሜ በሆነች፤
અરબી તફસીરો:
مَآ أَغۡنَىٰ عَنِّي مَالِيَهۡۜ
28. «ገንዘቤ ከእኔ ምንንም አልጠቀመኝም፤
અરબી તફસીરો:
هَلَكَ عَنِّي سُلۡطَٰنِيَهۡ
29. «ስልጣኔ ከእኔ ላይ ጠፋ» ይላል::
અરબી તફસીરો:
خُذُوهُ فَغُلُّوهُ
30. ያዙት ከዚያ እጁን ከአንገቱ ጋር እሰሩት፤
અરબી તફસીરો:
ثُمَّ ٱلۡجَحِيمَ صَلُّوهُ
31. ከዚያ በእሳት ውስጥ አስገቡት፤
અરબી તફસીરો:
ثُمَّ فِي سِلۡسِلَةٖ ذَرۡعُهَا سَبۡعُونَ ذِرَاعٗا فَٱسۡلُكُوهُ
32. ከዚም እርዝመቷ ሰባ ክንድ በሆነች ሰንሰለት ውስጥ አስገቡት።
અરબી તફસીરો:
إِنَّهُۥ كَانَ لَا يُؤۡمِنُ بِٱللَّهِ ٱلۡعَظِيمِ
33. እርሱ ታላቅ በሆነው አላህ አያምንም ነበርና፤
અરબી તફસીરો:
وَلَا يَحُضُّ عَلَىٰ طَعَامِ ٱلۡمِسۡكِينِ
34. ድሆችንም በማብላት ላይ አያነሳሳም ነበርና::
અરબી તફસીરો:
فَلَيۡسَ لَهُ ٱلۡيَوۡمَ هَٰهُنَا حَمِيمٞ
35. ለእርሱ ዛሬ እዚህ ቦታ ዘመድ ማንም የለዉም::
અરબી તફસીરો:
وَلَا طَعَامٌ إِلَّا مِنۡ غِسۡلِينٖ
36. ምግብም ከእሳት ሰዎች ቁስል እጣቢ እዥ በስተቀር የለዉም::
અરબી તફસીરો:
لَّا يَأۡكُلُهُۥٓ إِلَّا ٱلۡخَٰطِـُٔونَ
37. ይህን ምግብ ኃጢአተኞች እንጂ ሌላ አይበላዉም ይባላል::
અરબી તફસીરો:
فَلَآ أُقۡسِمُ بِمَا تُبۡصِرُونَ
38. በምታዩት ነገር ሁሉ እምላለሁ ::
અરબી તફસીરો:
وَمَا لَا تُبۡصِرُونَ
39. በማታዩትም ነገር ሁሉ እምላለሁ ::
અરબી તફસીરો:
إِنَّهُۥ لَقَوۡلُ رَسُولٖ كَرِيمٖ
40. ቁርኣን የተከበረው መልዕክተኛ ቃል ነው።
અરબી તફસીરો:
وَمَا هُوَ بِقَوۡلِ شَاعِرٖۚ قَلِيلٗا مَّا تُؤۡمِنُونَ
41. እርሱም የባለ ቅኔ ገጣሚ ቃል አይደለም:: ጥቂትን ብቻ ታምናላችሁ::
અરબી તફસીરો:
وَلَا بِقَوۡلِ كَاهِنٖۚ قَلِيلٗا مَّا تَذَكَّرُونَ
42. የጠንቋይም ቃል አይደለም:: ጥቂትን ብቻ ታስታውሳላችሁ::
અરબી તફસીરો:
تَنزِيلٞ مِّن رَّبِّ ٱلۡعَٰلَمِينَ
43. ከዓለማት ጌታ የተወረደ ነው::
અરબી તફસીરો:
وَلَوۡ تَقَوَّلَ عَلَيۡنَا بَعۡضَ ٱلۡأَقَاوِيلِ
44. በእኛ ላይም ከፊልን ቃላት እንኳን (ያላልነው) በቀጠፈ ኖሮ፤
અરબી તફસીરો:
لَأَخَذۡنَا مِنۡهُ بِٱلۡيَمِينِ
45. በኃይል በቀጣነው ነበር::
અરબી તફસીરો:
ثُمَّ لَقَطَعۡنَا مِنۡهُ ٱلۡوَتِينَ
46. ከዚያ ከእርሱ የልቡን ስር የተንጠላጠለበትን (ጅማት) በቆረጥን ነበር::
અરબી તફસીરો:
فَمَا مِنكُم مِّنۡ أَحَدٍ عَنۡهُ حَٰجِزِينَ
47. ከናንተም ውስጥ ከእርሱ ላይ ከልካዮች ምንም አይኖሩም።
અરબી તફસીરો:
وَإِنَّهُۥ لَتَذۡكِرَةٞ لِّلۡمُتَّقِينَ
48. እርሱ (ቁርኣን) ለጥንቅቆቹ ብቻ መገሰጫ ነው::
અરબી તફસીરો:
وَإِنَّا لَنَعۡلَمُ أَنَّ مِنكُم مُّكَذِّبِينَ
49. እኛም ከናንተ ውስጥ አስተባባዩች መኖራቸውን በእርግጥ እናውቃለን::
અરબી તફસીરો:
وَإِنَّهُۥ لَحَسۡرَةٌ عَلَى ٱلۡكَٰفِرِينَ
50. እርሱ (ቁርኣንም) በከሓዲያን ላይ ጸጸት ነው::
અરબી તફસીરો:
وَإِنَّهُۥ لَحَقُّ ٱلۡيَقِينِ
51. እርሱም የተረጋገጠ እውነት ነው::
અરબી તફસીરો:
فَسَبِّحۡ بِٱسۡمِ رَبِّكَ ٱلۡعَظِيمِ
52. እናም የታላቁን ጌታህን ስም (ታላቁን ጌታህን) አጥራው::
અરબી તફસીરો:
 
શબ્દોનું ભાષાંતર સૂરહ: અલ્ હાકકહ
સૂરહ માટે અનુક્રમણિકા પેજ નંબર
 
કુરઆન મજીદના શબ્દોનું ભાષાંતર - એમ્હારિક ભાષાંતર - ઝૈન - ભાષાંતરોની અનુક્રમણિકા

અમ્હેરિક ભાષાતર

બંધ કરો