Check out the new design

કુરઆન મજીદના શબ્દોનું ભાષાંતર - એમ્હારિક ભાષામાં અનુવાદ - આફ્રિકન એકેડમી * - ભાષાંતરોની અનુક્રમણિકા


શબ્દોનું ભાષાંતર સૂરહ: અલ્ અન્ફાલ   આયત:
وَمَا لَهُمۡ أَلَّا يُعَذِّبَهُمُ ٱللَّهُ وَهُمۡ يَصُدُّونَ عَنِ ٱلۡمَسۡجِدِ ٱلۡحَرَامِ وَمَا كَانُوٓاْ أَوۡلِيَآءَهُۥٓۚ إِنۡ أَوۡلِيَآؤُهُۥٓ إِلَّا ٱلۡمُتَّقُونَ وَلَٰكِنَّ أَكۡثَرَهُمۡ لَا يَعۡلَمُونَ
34. እነርሱ ከተከበረው መስጊድ የሚከለክሉ ሲሆኑ አላህ የማይቀጣቸው ለመሆኑ ለእነርሱ ምን ዋስትና አላቸው? የቤቱ ጠባቂዎቹ አልነበሩም:: ጠባቂዎቹም ክሕደትን ተጠንቃቂዎቹ እንጂ ሌሎቹ አይደሉም:: ግን አብዛኛዎቹ አያውቁም::
અરબી તફસીરો:
وَمَا كَانَ صَلَاتُهُمۡ عِندَ ٱلۡبَيۡتِ إِلَّا مُكَآءٗ وَتَصۡدِيَةٗۚ فَذُوقُواْ ٱلۡعَذَابَ بِمَا كُنتُمۡ تَكۡفُرُونَ
35. በከዕባ ውስጥ ስግደታቸውም ማፏጨትና ማጨብጨብ እንጂ ሌላ አልነበረም። «ትክዱት በነበራችሁትም ነገር ቅጣትን ቅመሱ» (ይባላሉ)::
અરબી તફસીરો:
إِنَّ ٱلَّذِينَ كَفَرُواْ يُنفِقُونَ أَمۡوَٰلَهُمۡ لِيَصُدُّواْ عَن سَبِيلِ ٱللَّهِۚ فَسَيُنفِقُونَهَا ثُمَّ تَكُونُ عَلَيۡهِمۡ حَسۡرَةٗ ثُمَّ يُغۡلَبُونَۗ وَٱلَّذِينَ كَفَرُوٓاْ إِلَىٰ جَهَنَّمَ يُحۡشَرُونَ
36. እነዚያ የካዱት ከአላህ መንገድ ሊከለክሉ ገንዘቦቻቸውን ያወጣሉ:: በእርግጥም ያወጡታል:: ከዚያ ግን በእነርሱ ላይ ጸጸት ይሆንባቸዋል:: ከዚያም ይሸነፋሉ:: እነዚያም የካዱት ሁሉ ወደ ገሀነም ይሰበሰባሉ::
અરબી તફસીરો:
لِيَمِيزَ ٱللَّهُ ٱلۡخَبِيثَ مِنَ ٱلطَّيِّبِ وَيَجۡعَلَ ٱلۡخَبِيثَ بَعۡضَهُۥ عَلَىٰ بَعۡضٖ فَيَرۡكُمَهُۥ جَمِيعٗا فَيَجۡعَلَهُۥ فِي جَهَنَّمَۚ أُوْلَٰٓئِكَ هُمُ ٱلۡخَٰسِرُونَ
37. አላህ መጥፎውን ነገር ከመልካሙ ሊለይ መጥፎውንም ከፊሉን በከፊሉ ላይ ሊያደርግና በአንድ ላይ ሊያነባብረው በገሀነም ውስጥም ሊያደርገው (ይሰበሰባሉ):: እነዚያ እነርሱ ከሳሪዎቹ ናቸው::
અરબી તફસીરો:
قُل لِّلَّذِينَ كَفَرُوٓاْ إِن يَنتَهُواْ يُغۡفَرۡ لَهُم مَّا قَدۡ سَلَفَ وَإِن يَعُودُواْ فَقَدۡ مَضَتۡ سُنَّتُ ٱلۡأَوَّلِينَ
38. (መልዕክተኛችን ሙሐመድ ሆይ!) ለእነዚያ በአላህ ለካዱት ቢከለከሉ ለእነርሱ በእርግጥ ያለፈውን ሥራ ምሕረት እንደሚደረግላቸው፤ ወደ መጋደል ቢመለሱም (እንደምናጠፋቸው ንገራቸው)። የቀድሞዎቹ ሕዝቦች ልማድ በእርግጥ አልፏልና።
અરબી તફસીરો:
وَقَٰتِلُوهُمۡ حَتَّىٰ لَا تَكُونَ فِتۡنَةٞ وَيَكُونَ ٱلدِّينُ كُلُّهُۥ لِلَّهِۚ فَإِنِ ٱنتَهَوۡاْ فَإِنَّ ٱللَّهَ بِمَا يَعۡمَلُونَ بَصِيرٞ
39. ሁከት እስከሚጠፋና ሃይማኖት ሁሉ ለአላህ ብቻ እስከሚሆንም ድረስ ተጋደሏቸው:: ቢከለከሉም አላህ የሚሠሩትን ሁሉ ተመልካች ነው::
અરબી તફસીરો:
وَإِن تَوَلَّوۡاْ فَٱعۡلَمُوٓاْ أَنَّ ٱللَّهَ مَوۡلَىٰكُمۡۚ نِعۡمَ ٱلۡمَوۡلَىٰ وَنِعۡمَ ٱلنَّصِيرُ
40. (ሙስሊሞች ሆይ!) ከእምነት ቢዞሩም አላህ ረዳታችሁ መሆኑን እወቁ:: እርሱ ምን ያምር ጠባቂ! ምን ያምርም ረዳት ነው!
અરબી તફસીરો:
 
શબ્દોનું ભાષાંતર સૂરહ: અલ્ અન્ફાલ
સૂરહ માટે અનુક્રમણિકા પેજ નંબર
 
કુરઆન મજીદના શબ્દોનું ભાષાંતર - એમ્હારિક ભાષામાં અનુવાદ - આફ્રિકન એકેડમી - ભાષાંતરોની અનુક્રમણિકા

તેનું અનુવાદ મુહમ્મદ ઝૈન ઝહરુદ્ દીન દ્વારા કરવામાં આવ્યું. આફ્રિકા એકેડમી દ્વારા પ્રકાશિત.

બંધ કરો