Check out the new design

Fassarar Ma'anonin Alqura'ni - Fassarar Amhariyanci - Akadamar Afirka * - Teburin Bayani kan wasu Fassarori


Fassarar Ma'anoni Sura: Al'bakara   Aya:
۞ وَٱذۡكُرُواْ ٱللَّهَ فِيٓ أَيَّامٖ مَّعۡدُودَٰتٖۚ فَمَن تَعَجَّلَ فِي يَوۡمَيۡنِ فَلَآ إِثۡمَ عَلَيۡهِ وَمَن تَأَخَّرَ فَلَآ إِثۡمَ عَلَيۡهِۖ لِمَنِ ٱتَّقَىٰۗ وَٱتَّقُواْ ٱللَّهَ وَٱعۡلَمُوٓاْ أَنَّكُمۡ إِلَيۡهِ تُحۡشَرُونَ
203. (ሙስሊሞች ሆይ!) በእነዚያ በተወሰኑ ቀናት ውስጥ አላህን አውሱ:: በሁለት ቀናት ውስጥ ለመሄድ የተቻኮለ ሰው በእርሱ ላይ ኃጢአት የለበትም:: የቆየም ሰው ኃጢአት የለበትም:: ይህም (ምህረት) አላህን ለፈራ ሰው ሁሉ ነው:: አላህንም ፍሩ:: እናንተ ወደ እርሱ የምትሰበሰቡ መሆናችሁንም እወቁ::
Tafsiran larabci:
وَمِنَ ٱلنَّاسِ مَن يُعۡجِبُكَ قَوۡلُهُۥ فِي ٱلۡحَيَوٰةِ ٱلدُّنۡيَا وَيُشۡهِدُ ٱللَّهَ عَلَىٰ مَا فِي قَلۡبِهِۦ وَهُوَ أَلَدُّ ٱلۡخِصَامِ
204. ከሰዎችም መካከል እርሱ ክርክረ ብርቱ ሲሆን በቅርቢቱ ሕይወት ንግግሩ የሚያስደስትህ (የሚደንቅህ) ፤ በልቡ ውስጥ በሚያጠነጥነውም አላህን የሚያስመሰክር ሰው አለ።
Tafsiran larabci:
وَإِذَا تَوَلَّىٰ سَعَىٰ فِي ٱلۡأَرۡضِ لِيُفۡسِدَ فِيهَا وَيُهۡلِكَ ٱلۡحَرۡثَ وَٱلنَّسۡلَۚ وَٱللَّهُ لَا يُحِبُّ ٱلۡفَسَادَ
205. (ካንተ) በዞረ ጊዜ በውስጧ ሊያበላሽና አዝመራንና እንሰሳዎችን ሊያጠፋ በምድር ላይ ይሮጣል:: አላህም ጥፋትን አይወድም፡፡
Tafsiran larabci:
وَإِذَا قِيلَ لَهُ ٱتَّقِ ٱللَّهَ أَخَذَتۡهُ ٱلۡعِزَّةُ بِٱلۡإِثۡمِۚ فَحَسۡبُهُۥ جَهَنَّمُۖ وَلَبِئۡسَ ٱلۡمِهَادُ
206. ለእርሱ “አላህን ፍራ” በተባለም ጊዜ ትዕቢት (በኃጢአት ስራ ላይ) ይገፋፋዋል። ገሀነምም ለእሱ በቂው ናት:: እርሷም በእርግጥ የከፋች ምንጣፍ ናት::
Tafsiran larabci:
وَمِنَ ٱلنَّاسِ مَن يَشۡرِي نَفۡسَهُ ٱبۡتِغَآءَ مَرۡضَاتِ ٱللَّهِۚ وَٱللَّهُ رَءُوفُۢ بِٱلۡعِبَادِ
207. ከሰዎችም ውስጥ የአላህን ውዴታ ለመፈለግ ሲል ነፍሱን የሚሸጥም ሰው አለ:: አላህም ለባሮቹ በጣም ሩህሩህ ነው።
Tafsiran larabci:
يَٰٓأَيُّهَا ٱلَّذِينَ ءَامَنُواْ ٱدۡخُلُواْ فِي ٱلسِّلۡمِ كَآفَّةٗ وَلَا تَتَّبِعُواْ خُطُوَٰتِ ٱلشَّيۡطَٰنِۚ إِنَّهُۥ لَكُمۡ عَدُوّٞ مُّبِينٞ
208. እናንተ ያመናችሁ ሆይ! ሁላችሁም ወደ አላህ መንገድ እስልምና ጠቅልላችሁ ግቡ:: የሰይጣንን እርምጃዎችም አትከተሉ፤ እርሱም ለእናንተ ግልጽ ጠላት ነውና።
Tafsiran larabci:
فَإِن زَلَلۡتُم مِّنۢ بَعۡدِ مَا جَآءَتۡكُمُ ٱلۡبَيِّنَٰتُ فَٱعۡلَمُوٓاْ أَنَّ ٱللَّهَ عَزِيزٌ حَكِيمٌ
209. ግልጽ ማስረጃዎች ከመጡላችሁ በኋላ እውነትን ከመቀበል ብታፈገፍጉ አላህ ሁሉን አሸናፊና ጥበበኛ መሆኑን እወቁ።
Tafsiran larabci:
هَلۡ يَنظُرُونَ إِلَّآ أَن يَأۡتِيَهُمُ ٱللَّهُ فِي ظُلَلٖ مِّنَ ٱلۡغَمَامِ وَٱلۡمَلَٰٓئِكَةُ وَقُضِيَ ٱلۡأَمۡرُۚ وَإِلَى ٱللَّهِ تُرۡجَعُ ٱلۡأُمُورُ
210. አላህ በዳመና ጥላዎች ዉሥጥ ሆኖ እና መላዕክቱ ከያቅጣጫው ወደ እነርሱ እንዲመጡና ጉዳዩ እንዲወሰን እንጂ ሌላ ምንን ይጠባበቃሉ:: ነገሮች ሁሉ ወደ አላህ ብቻ ይመለሳሉ።
Tafsiran larabci:
 
Fassarar Ma'anoni Sura: Al'bakara
Teburin Jerin Sunayen Surori Lambar shafi
 
Fassarar Ma'anonin Alqura'ni - Fassarar Amhariyanci - Akadamar Afirka - Teburin Bayani kan wasu Fassarori

Fassararta Muhammad Zain Zahruddin. Fitowa daga Akademiyar Afirka.

Rufewa