Check out the new design

Fassarar Ma'anonin Alqura'ni - Fassarar Amhariyanci - Akadamar Afirka * - Teburin Bayani kan wasu Fassarori


Fassarar Ma'anoni Sura: Al'bakara   Aya:
فِي ٱلدُّنۡيَا وَٱلۡأٓخِرَةِۗ وَيَسۡـَٔلُونَكَ عَنِ ٱلۡيَتَٰمَىٰۖ قُلۡ إِصۡلَاحٞ لَّهُمۡ خَيۡرٞۖ وَإِن تُخَالِطُوهُمۡ فَإِخۡوَٰنُكُمۡۚ وَٱللَّهُ يَعۡلَمُ ٱلۡمُفۡسِدَ مِنَ ٱلۡمُصۡلِحِۚ وَلَوۡ شَآءَ ٱللَّهُ لَأَعۡنَتَكُمۡۚ إِنَّ ٱللَّهَ عَزِيزٌ حَكِيمٞ
220. በዱኒያም በአኼራም ታስተነትኑ ዘንድ ይገልፅላችኃል። (መልዕክተኛችን ሙሐመድ ሆይ!) ስለየቲሞችም ይጠይቁሀል:: «የእነርሱን ሁኔታ ማሻሻል በላጭ ነው:: የእነርሱ ጉዳይ ከናንተ ጋር ብትቀላቅሉም ወንድሞቻችሁ ናቸው:: አላህም አጥፊውን ከአልሚው ለይቶ ያውቃል:: አላህም በፈለገ ኖሮ መፈናፈኛ ያሳጣችሁ (ባስቸገራችሁ) ነበር:: አላህ በሁሉም ነገር አሸናፊና ጥበበኛ ነው በላቸው::
Tafsiran larabci:
وَلَا تَنكِحُواْ ٱلۡمُشۡرِكَٰتِ حَتَّىٰ يُؤۡمِنَّۚ وَلَأَمَةٞ مُّؤۡمِنَةٌ خَيۡرٞ مِّن مُّشۡرِكَةٖ وَلَوۡ أَعۡجَبَتۡكُمۡۗ وَلَا تُنكِحُواْ ٱلۡمُشۡرِكِينَ حَتَّىٰ يُؤۡمِنُواْۚ وَلَعَبۡدٞ مُّؤۡمِنٌ خَيۡرٞ مِّن مُّشۡرِكٖ وَلَوۡ أَعۡجَبَكُمۡۗ أُوْلَٰٓئِكَ يَدۡعُونَ إِلَى ٱلنَّارِۖ وَٱللَّهُ يَدۡعُوٓاْ إِلَى ٱلۡجَنَّةِ وَٱلۡمَغۡفِرَةِ بِإِذۡنِهِۦۖ وَيُبَيِّنُ ءَايَٰتِهِۦ لِلنَّاسِ لَعَلَّهُمۡ يَتَذَكَّرُونَ
221. (ሙስሊሞች ሆይ!) አጋሪዎችን ሴቶችን በአላህ እስከሚያምኑ ድረስ አታግቧቸው:: አጋሪይቱ ነፃ ሴት ምንም ብትስባችሁ እንኳ ያመነችው ባሪያ ሴት በእርግጥ ለእናንተ በላጭ ናት:: ለአጋሪዎቹ እስከሚያምኑ ድረስ አትዳሩላቸው:: ከአጋሪ ወንድ ምንም ቢስባችሁ አማኝ ባሪያዎች ለእናንተ በላጭ ናቸው:: እነዚያ አጋሪዎች ወደ እሳት ይጠራሉ:: አላህ ደግሞ ወደ ገነትና ወደ ምህረት ይጠራል:: ህግጋቱንም ለሰዎች ሊገሰጹ ዘንድ ይገልፅላቸዋል፡፡
Tafsiran larabci:
وَيَسۡـَٔلُونَكَ عَنِ ٱلۡمَحِيضِۖ قُلۡ هُوَ أَذٗى فَٱعۡتَزِلُواْ ٱلنِّسَآءَ فِي ٱلۡمَحِيضِ وَلَا تَقۡرَبُوهُنَّ حَتَّىٰ يَطۡهُرۡنَۖ فَإِذَا تَطَهَّرۡنَ فَأۡتُوهُنَّ مِنۡ حَيۡثُ أَمَرَكُمُ ٱللَّهُۚ إِنَّ ٱللَّهَ يُحِبُّ ٱلتَّوَّٰبِينَ وَيُحِبُّ ٱلۡمُتَطَهِّرِينَ
222. (መልዕክተኛችን ሙሐመድ ሆይ!) ስለ ሴቶች የወር አበባ ይጠይቁሃል:: «እርሱ ጎጂ (አጸያፊ) ነው። እናም ሚስቶቻችሁን በወር አበባቸው ጊዜ ራቁዋቸው፤ ደሙ ቆሞ ንጹህ እስከሚሆኑ ድረስ ለግንኙነት በፍጹም አትቅረቧቸው:: ንጹህ በሆኑ ጊዜም አላህ ባዘዛችሁ ቦታ ተገናኟቸው:: አላህ ከኃጢአት ተመላሾችንና ንጽህናን የሚጠብቁትን ይወዳልና።» በላቸው::
Tafsiran larabci:
نِسَآؤُكُمۡ حَرۡثٞ لَّكُمۡ فَأۡتُواْ حَرۡثَكُمۡ أَنَّىٰ شِئۡتُمۡۖ وَقَدِّمُواْ لِأَنفُسِكُمۡۚ وَٱتَّقُواْ ٱللَّهَ وَٱعۡلَمُوٓاْ أَنَّكُم مُّلَٰقُوهُۗ وَبَشِّرِ ٱلۡمُؤۡمِنِينَ
223. ሚስቶቻችሁ ለእናንተ እርሻ ናቸው:: እናም እርሻዎቻችሁን በፈለጋችሁት ሁኔታ ግንኙነት ፈጽሙ:: ለነፍሶቻችሁ መልካም ስራን አስቀድሙ:: አላህንም ፍሩ:: እናንተም ከእርሱ ጋር የምትገናኙ መሆናችሁን እውቁ:: (መልዕክተኛችን ሙሐመድ ሆይ!) አማኞችንም በገነት አብስራቸው::
Tafsiran larabci:
وَلَا تَجۡعَلُواْ ٱللَّهَ عُرۡضَةٗ لِّأَيۡمَٰنِكُمۡ أَن تَبَرُّواْ وَتَتَّقُواْ وَتُصۡلِحُواْ بَيۡنَ ٱلنَّاسِۚ وَٱللَّهُ سَمِيعٌ عَلِيمٞ
224. (ሙስሊሞች ሆይ!) በአላህ ስም የፈጸማችሁት መሀላ በጎ ከመዋል አላህን ከመፍራትም ወይም በሰዎች መካከል እርቀ ሰላም ከማውረድ ግርዶ አታድርጉ:: አላህ ሁሉን ሰሚና ሁሉንም አዋቂ ነውና::
Tafsiran larabci:
 
Fassarar Ma'anoni Sura: Al'bakara
Teburin Jerin Sunayen Surori Lambar shafi
 
Fassarar Ma'anonin Alqura'ni - Fassarar Amhariyanci - Akadamar Afirka - Teburin Bayani kan wasu Fassarori

Fassararta Muhammad Zain Zahruddin. Fitowa daga Akademiyar Afirka.

Rufewa