Check out the new design

Terjemahan makna Alquran Alkarim - Terjemahan Berbahasa Amhar - Akademi Afrika * - Daftar isi terjemahan


Terjemahan makna Surah: Al-Baqarah   Ayah:
ٱلَّذِينَ ءَاتَيۡنَٰهُمُ ٱلۡكِتَٰبَ يَعۡرِفُونَهُۥ كَمَا يَعۡرِفُونَ أَبۡنَآءَهُمۡۖ وَإِنَّ فَرِيقٗا مِّنۡهُمۡ لَيَكۡتُمُونَ ٱلۡحَقَّ وَهُمۡ يَعۡلَمُونَ
146. እነዚያ መጽሐፍን የሰጠናቸው ሰዎች ወንዶች ልጆቻቸውን እንደሚያውቁ ሁሉ (ሙሐመድን) ያውቁታል:: ከእነርሱም የተለዩ ክፍሎች እነርሱ የሚያውቁ ሲሆኑ እውነቱን በእርግጥ ይደብቃሉ::
Tafsir berbahasa Arab:
ٱلۡحَقُّ مِن رَّبِّكَ فَلَا تَكُونَنَّ مِنَ ٱلۡمُمۡتَرِينَ
147. (መልዕክተኛችን ሙሐመድ ሆይ!) ይህ ከጌታህ የሆነ እውነት ነው:: እናም ከተጠራጣሪዎችም አትሁን::
Tafsir berbahasa Arab:
وَلِكُلّٖ وِجۡهَةٌ هُوَ مُوَلِّيهَاۖ فَٱسۡتَبِقُواْ ٱلۡخَيۡرَٰتِۚ أَيۡنَ مَا تَكُونُواْ يَأۡتِ بِكُمُ ٱللَّهُ جَمِيعًاۚ إِنَّ ٱللَّهَ عَلَىٰ كُلِّ شَيۡءٖ قَدِيرٞ
148. ለሁሉም ለስግደት ፊታቸዉን የሚያዞሩባት አቅጣጫ አላቸው:: ወደ መልካም ስራዎችም ተሽቀዳደሙ:: የትም ስፍራ ብትሆኑ አላህ ሁላችሁንም ያመጣችኋል:: አላህ በነገሩ ሁሉ ላይ ቻይ ነውና::
Tafsir berbahasa Arab:
وَمِنۡ حَيۡثُ خَرَجۡتَ فَوَلِّ وَجۡهَكَ شَطۡرَ ٱلۡمَسۡجِدِ ٱلۡحَرَامِۖ وَإِنَّهُۥ لَلۡحَقُّ مِن رَّبِّكَۗ وَمَا ٱللَّهُ بِغَٰفِلٍ عَمَّا تَعۡمَلُونَ
149. (መልዕክተኛችን ሙሐመድ ሆይ!) ከየትም ለጉዞ ከወጣህበት ስፍራ ሁነህ ፊትህን ወደ ተከበረው መስጊድ አቅጣጫ አዙር:: እርሱም ከጌታህ የሆነ እርግጠኛ እውነት ነው:: አላህም ከምትሰሩት ስራ ሁሉ ዘንጊ አይደለም::
Tafsir berbahasa Arab:
وَمِنۡ حَيۡثُ خَرَجۡتَ فَوَلِّ وَجۡهَكَ شَطۡرَ ٱلۡمَسۡجِدِ ٱلۡحَرَامِۚ وَحَيۡثُ مَا كُنتُمۡ فَوَلُّواْ وُجُوهَكُمۡ شَطۡرَهُۥ لِئَلَّا يَكُونَ لِلنَّاسِ عَلَيۡكُمۡ حُجَّةٌ إِلَّا ٱلَّذِينَ ظَلَمُواْ مِنۡهُمۡ فَلَا تَخۡشَوۡهُمۡ وَٱخۡشَوۡنِي وَلِأُتِمَّ نِعۡمَتِي عَلَيۡكُمۡ وَلَعَلَّكُمۡ تَهۡتَدُونَ
150.ከየትም ከወጣህበት ስፍራ ፊትህን ወደ ተከለለው መስጊድ አግጣጫ አዙር፡፡ በየትም ስፍራ ብትኾኑ ለሰዎቹ እነዚያ ከነሱ የበደሉት ሲቀሩ (ሃይማኖታችንን ይክዳሉ ቂብላችንን ይከተላሉ በማለት) በናንተ ላይ መከራከሪያ እንዳይኖራቸው ፊቶቻችሁን ወደ አግጣጫው አዙሩ፡፡ አትፍሩዋቸውም፤ ፍሩኝም፤ (በዚህም ያዘዝኳችሁ መከራከሪያ እንዳይኖራቸው) በናንተም ላይ ጸጋየን እንድሞላላችሁና (ወደ እውነትም) እንድትመሩ ነው፡፡
Tafsir berbahasa Arab:
كَمَآ أَرۡسَلۡنَا فِيكُمۡ رَسُولٗا مِّنكُمۡ يَتۡلُواْ عَلَيۡكُمۡ ءَايَٰتِنَا وَيُزَكِّيكُمۡ وَيُعَلِّمُكُمُ ٱلۡكِتَٰبَ وَٱلۡحِكۡمَةَ وَيُعَلِّمُكُم مَّا لَمۡ تَكُونُواْ تَعۡلَمُونَ
151. ከመካከላችሁ ከናንተ የሆነን በእናንተ ላይ አናቅጻችንን የሚያነብላችሁ እና የሚያጠራችሁ መጽሐፉንና ጥበብንም የሚያስተምራችሁ ታውቁት ያልነበራችሁትንም ነገር የሚያሳውቃችሁን መልእክተኛ እንደላክን ሁሉ ጸጋን ሞላንላችሁ።
Tafsir berbahasa Arab:
فَٱذۡكُرُونِيٓ أَذۡكُرۡكُمۡ وَٱشۡكُرُواْ لِي وَلَا تَكۡفُرُونِ
152. አስታውሱኝ አስታውሳችኋለሁና:: አመስግኑኝ አትካዱኝም::
Tafsir berbahasa Arab:
يَٰٓأَيُّهَا ٱلَّذِينَ ءَامَنُواْ ٱسۡتَعِينُواْ بِٱلصَّبۡرِ وَٱلصَّلَوٰةِۚ إِنَّ ٱللَّهَ مَعَ ٱلصَّٰبِرِينَ
153. እናንተ ያመናችሁ ሆይ! በመታገስና በሶላት ታጋዙ (ጥንካሬን ፈልጉ):: አላህም ከታጋሾች ጋር ነውና::
Tafsir berbahasa Arab:
 
Terjemahan makna Surah: Al-Baqarah
Daftar surah Nomor Halaman
 
Terjemahan makna Alquran Alkarim - Terjemahan Berbahasa Amhar - Akademi Afrika - Daftar isi terjemahan

Terjemahan oleh Muhammad Zain Zahreddin. Diterbitkan oleh Akademi Afrika.

Tutup