Check out the new design

Terjemahan makna Alquran Alkarim - Terjemahan Berbahasa Amhar - Akademi Afrika * - Daftar isi terjemahan


Terjemahan makna Surah: Al-A'rāf   Ayah:
قَالَ يَٰمُوسَىٰٓ إِنِّي ٱصۡطَفَيۡتُكَ عَلَى ٱلنَّاسِ بِرِسَٰلَٰتِي وَبِكَلَٰمِي فَخُذۡ مَآ ءَاتَيۡتُكَ وَكُن مِّنَ ٱلشَّٰكِرِينَ
144. አላህም አለ፡- «ሙሳ ሆይ! እኔ በመልዕክቶቼና በማናገሬ በሰዎች ላይ መረጥኩህ:: የሰጠሁህንም ያዝ። ከአመስጋኞችም ሁን።» አለው።
Tafsir berbahasa Arab:
وَكَتَبۡنَا لَهُۥ فِي ٱلۡأَلۡوَاحِ مِن كُلِّ شَيۡءٖ مَّوۡعِظَةٗ وَتَفۡصِيلٗا لِّكُلِّ شَيۡءٖ فَخُذۡهَا بِقُوَّةٖ وَأۡمُرۡ قَوۡمَكَ يَأۡخُذُواْ بِأَحۡسَنِهَاۚ سَأُوْرِيكُمۡ دَارَ ٱلۡفَٰسِقِينَ
145. ለእርሱም በሰሌዳዎቹ ላይ ከሁሉ ነገር ግሳጼንና ለሁሉ ነገር ማብራራትን ጻፍንለትና አልንም: «በብርታትም ያዛት። ሕዝቦችህንም በመልካሟ እንዲይዙ እዘዛቸው። የአመጸኞቹን አገር በእርግጥ አሳያችኋለሁ።»
Tafsir berbahasa Arab:
سَأَصۡرِفُ عَنۡ ءَايَٰتِيَ ٱلَّذِينَ يَتَكَبَّرُونَ فِي ٱلۡأَرۡضِ بِغَيۡرِ ٱلۡحَقِّ وَإِن يَرَوۡاْ كُلَّ ءَايَةٖ لَّا يُؤۡمِنُواْ بِهَا وَإِن يَرَوۡاْ سَبِيلَ ٱلرُّشۡدِ لَا يَتَّخِذُوهُ سَبِيلٗا وَإِن يَرَوۡاْ سَبِيلَ ٱلۡغَيِّ يَتَّخِذُوهُ سَبِيلٗاۚ ذَٰلِكَ بِأَنَّهُمۡ كَذَّبُواْ بِـَٔايَٰتِنَا وَكَانُواْ عَنۡهَا غَٰفِلِينَ
146. እነዚያን ያለ አግባብ በምድር ላይ የሚኮሩትን ከአንቀፆቼ በእርግጥ አዞራቸዋለሁ:: ተዓምርንም ሁሉ ቢያዩ እንኳን አያምኑም:: ቅንንም መንገድ ቢያዩ መንገድ አድርገው አይዙትም:: ግን የጥመትን መንገድ ቢያዩ መንገድ አድርገው ይይዙታል:: ይህ እነርሱ በአንቀፆቻችን ስለ አስተባበሉና ከእርሷም ዘንጊዎች ስለሆኑ ነው::
Tafsir berbahasa Arab:
وَٱلَّذِينَ كَذَّبُواْ بِـَٔايَٰتِنَا وَلِقَآءِ ٱلۡأٓخِرَةِ حَبِطَتۡ أَعۡمَٰلُهُمۡۚ هَلۡ يُجۡزَوۡنَ إِلَّا مَا كَانُواْ يَعۡمَلُونَ
147. እነዚያም በአናቅጻችንና መጨረሻይቱን ዓለም በመገናኘት ያስተባበሉት ሥራዎቻቸው ተበላሹ:: ይሰሩት የነበረውን እንጂ ይመነዳሉን?
Tafsir berbahasa Arab:
وَٱتَّخَذَ قَوۡمُ مُوسَىٰ مِنۢ بَعۡدِهِۦ مِنۡ حُلِيِّهِمۡ عِجۡلٗا جَسَدٗا لَّهُۥ خُوَارٌۚ أَلَمۡ يَرَوۡاْ أَنَّهُۥ لَا يُكَلِّمُهُمۡ وَلَا يَهۡدِيهِمۡ سَبِيلًاۘ ٱتَّخَذُوهُ وَكَانُواْ ظَٰلِمِينَ
148. የሙሳም ህዝቦች ከእርሱ መሄድ በኋላ ከጌጦቻቸው በወይፈን ቅርጽ የተቀረጸውን እና የራሱ የሆነ ድምጽ የነበረውን አካል አምላክ አድርገው ያዙት:: እርሱ የማያናግራቸው መንገድን የማይመራቸው መሆኑን አይመለከቱምን? አምላክ አደረጉት:: በዳዮችም ሆኑ::
Tafsir berbahasa Arab:
وَلَمَّا سُقِطَ فِيٓ أَيۡدِيهِمۡ وَرَأَوۡاْ أَنَّهُمۡ قَدۡ ضَلُّواْ قَالُواْ لَئِن لَّمۡ يَرۡحَمۡنَا رَبُّنَا وَيَغۡفِرۡ لَنَا لَنَكُونَنَّ مِنَ ٱلۡخَٰسِرِينَ
149. በተጸጸቱና እነርሱም በእርግጥ የተሳሳቱ መሆናቸውን ባዩ ጊዜ «ጌታችን ካላዘነልንና ካልማረን በእርግጥ ከከሳሪዎቹ እንሆናለን።» አሉ::
Tafsir berbahasa Arab:
 
Terjemahan makna Surah: Al-A'rāf
Daftar surah Nomor Halaman
 
Terjemahan makna Alquran Alkarim - Terjemahan Berbahasa Amhar - Akademi Afrika - Daftar isi terjemahan

Terjemahan oleh Muhammad Zain Zahreddin. Diterbitkan oleh Akademi Afrika.

Tutup