Check out the new design

Traduzione dei Significati del Sacro Corano - Traduzione Amarica - Accademia d'Africa * - Indice Traduzioni


Traduzione dei significati Sura: Yûsuf   Versetto:
وَرَٰوَدَتۡهُ ٱلَّتِي هُوَ فِي بَيۡتِهَا عَن نَّفۡسِهِۦ وَغَلَّقَتِ ٱلۡأَبۡوَٰبَ وَقَالَتۡ هَيۡتَ لَكَۚ قَالَ مَعَاذَ ٱللَّهِۖ إِنَّهُۥ رَبِّيٓ أَحۡسَنَ مَثۡوَايَۖ إِنَّهُۥ لَا يُفۡلِحُ ٱلظَّٰلِمُونَ
23. ያችም እርሱ በቤትዋ የነበረባት ሴት ከነፍሱ አባበለችው:: ደጃፎቹንም ዘጋችና «ይኸው ላንተ ተዘጋጂቼልሃለሁና ቶሎ በል» አለችው:: እሱም «ከዚህ ጸያፍ ተግባር በአላህ እጠበቃለሁ:: እርሱ የገዘኝ ጌታዬ ኑሮዬን ያሳመረልኝ ነውና አልከዳዉም:: እነሆ በደለኞች ሁሉ አይድኑምና» አላት።
Esegesi in lingua araba:
وَلَقَدۡ هَمَّتۡ بِهِۦۖ وَهَمَّ بِهَا لَوۡلَآ أَن رَّءَا بُرۡهَٰنَ رَبِّهِۦۚ كَذَٰلِكَ لِنَصۡرِفَ عَنۡهُ ٱلسُّوٓءَ وَٱلۡفَحۡشَآءَۚ إِنَّهُۥ مِنۡ عِبَادِنَا ٱلۡمُخۡلَصِينَ
24. በእርሱም በእርግጥ አሰበች፡፡ በእርሷም አሰበ ፡፡የጌታውን ማስረጃ ባላዬ ኖሮ (በእርሷም ባሰበ ነበር) ፡፡ልክ እንደዚሁ መጥፎ ነገርንና ኃጢአትን ከእርሱ ላይ ልንመልስለት አስረጃችንን አሳየነው ፡፡እርሱ ከተጠበቁት ባሮቻችን አንዱ ነዉና ፡፡
Esegesi in lingua araba:
وَٱسۡتَبَقَا ٱلۡبَابَ وَقَدَّتۡ قَمِيصَهُۥ مِن دُبُرٖ وَأَلۡفَيَا سَيِّدَهَا لَدَا ٱلۡبَابِۚ قَالَتۡ مَا جَزَآءُ مَنۡ أَرَادَ بِأَهۡلِكَ سُوٓءًا إِلَّآ أَن يُسۡجَنَ أَوۡ عَذَابٌ أَلِيمٞ
25. እርሱና እርሷ በሩን ተሸቀዳደሙና ቀሚሱን ከኋላው ቀደደችው። ባለቤትዋን እበሩ አጠገብ አገኙት:: እርሷም ቀደም ብላ «በባለቤትህ መጥፎን ያሰበ ሰው ቅጣቱ መታሰር ወይም አሳማሚ ስቃይ እንጂ ሌላ አይደለም።» አለችው።
Esegesi in lingua araba:
قَالَ هِيَ رَٰوَدَتۡنِي عَن نَّفۡسِيۚ وَشَهِدَ شَاهِدٞ مِّنۡ أَهۡلِهَآ إِن كَانَ قَمِيصُهُۥ قُدَّ مِن قُبُلٖ فَصَدَقَتۡ وَهُوَ مِنَ ٱلۡكَٰذِبِينَ
26. ዩሱፍም «እርሷ ናት ከነፍሴ ያባበለችኝ።» አለ:: ከቤተሰቦቿም አንድ መስካሪ (እንዲህ) መሰከረ: «ቀሚሱ ከበስተፊት ተቀዶ ከሆነ እርሷ እውነት ተናገረች:: እርሱ ከውሸታሞቹ አንዱ ነው።
Esegesi in lingua araba:
وَإِن كَانَ قَمِيصُهُۥ قُدَّ مِن دُبُرٖ فَكَذَبَتۡ وَهُوَ مِنَ ٱلصَّٰدِقِينَ
27. «ቀሚሱም ከበስተኋላው ተቀዶ እንደሆነ ዋሸች:: እርሱም ከእውነተኞቹ ነው።»
Esegesi in lingua araba:
فَلَمَّا رَءَا قَمِيصَهُۥ قُدَّ مِن دُبُرٖ قَالَ إِنَّهُۥ مِن كَيۡدِكُنَّۖ إِنَّ كَيۡدَكُنَّ عَظِيمٞ
28. ቀሚሱንም ከበስተኋላ ተቀዶ ባየ ጊዜ አለ: «እርሱ የተናገርሽው ከተንኮላችሁ ነው። የእንናንተ የሴቶች ተንኮል በእርግጥ ብርቱ ነው።
Esegesi in lingua araba:
يُوسُفُ أَعۡرِضۡ عَنۡ هَٰذَاۚ وَٱسۡتَغۡفِرِي لِذَنۢبِكِۖ إِنَّكِ كُنتِ مِنَ ٱلۡخَاطِـِٔينَ
29. «ዩሱፍ ሆይ! አንተም ከዚህ ወሬ ተከልከል:: አንቺም ለኃጢአትሽ ማርታን ለምኝ። አንቺ ከስሕተተኞቹ ሆነሻልና።» አለ::
Esegesi in lingua araba:
۞ وَقَالَ نِسۡوَةٞ فِي ٱلۡمَدِينَةِ ٱمۡرَأَتُ ٱلۡعَزِيزِ تُرَٰوِدُ فَتَىٰهَا عَن نَّفۡسِهِۦۖ قَدۡ شَغَفَهَا حُبًّاۖ إِنَّا لَنَرَىٰهَا فِي ضَلَٰلٖ مُّبِينٖ
30. በከተማው ያሉ ሴቶችም «የዐዚዝ ሚስት ሰራተኛዋን ከነፍሱ ታባብለዋለች:: በእውነቱ ፍቅሩ ልቧን መቷታል:: እኛ በግልጽ ስሕተት ውስጥ ሆና በእርግጥ እናያታለን።» አሉ።
Esegesi in lingua araba:
 
Traduzione dei significati Sura: Yûsuf
Indice delle Sure Numero di pagina
 
Traduzione dei Significati del Sacro Corano - Traduzione Amarica - Accademia d'Africa - Indice Traduzioni

Tradotta da Muhammad Zain Zaher al-Din. Pubblicata dall'Accademia d'Africa.

Chiudi