Check out the new design

Traduzione dei Significati del Sacro Corano - Traduzione Amarica - Accademia d'Africa * - Indice Traduzioni


Traduzione dei significati Sura: Al-Baqarah   Versetto:
فَمَنۡ خَافَ مِن مُّوصٖ جَنَفًا أَوۡ إِثۡمٗا فَأَصۡلَحَ بَيۡنَهُمۡ فَلَآ إِثۡمَ عَلَيۡهِۚ إِنَّ ٱللَّهَ غَفُورٞ رَّحِيمٞ
182. ከተናዛዥም በኩል (ከእውነት) መዘንበልን ወይም (ከሲሶ የመጨመር) ኃጢአትን የፈራ (ያወቀ) ከዚያም በመካከላቸው ያስታረቀ በእርሱ ላይ ምንም ኃጢአት የለበትም:: አላህ በጣም መሀሪና በጣም አዛኝ ነውና።
Esegesi in lingua araba:
يَٰٓأَيُّهَا ٱلَّذِينَ ءَامَنُواْ كُتِبَ عَلَيۡكُمُ ٱلصِّيَامُ كَمَا كُتِبَ عَلَى ٱلَّذِينَ مِن قَبۡلِكُمۡ لَعَلَّكُمۡ تَتَّقُونَ
183. እናንተ ያመናችሁ ሆይ! ፆም በእነዚያ ከናንተ በፊት በነበሩት (ሕዝቦች) ላይ ግዴታነቱ እንደተፃፈ ሁሉ በእናንተም ላይ ተደነገገ:: ልትጠነቀቁ ይከጀላልና።
Esegesi in lingua araba:
أَيَّامٗا مَّعۡدُودَٰتٖۚ فَمَن كَانَ مِنكُم مَّرِيضًا أَوۡ عَلَىٰ سَفَرٖ فَعِدَّةٞ مِّنۡ أَيَّامٍ أُخَرَۚ وَعَلَى ٱلَّذِينَ يُطِيقُونَهُۥ فِدۡيَةٞ طَعَامُ مِسۡكِينٖۖ فَمَن تَطَوَّعَ خَيۡرٗا فَهُوَ خَيۡرٞ لَّهُۥۚ وَأَن تَصُومُواْ خَيۡرٞ لَّكُمۡ إِن كُنتُمۡ تَعۡلَمُونَ
184. ውስን ቀናትን ጹሙ። ከናንተም ውስጥ በሽተኛ ወይም በጉዞ ላይ የሆነ ሰው ባልፆማቸው ቀናት ልክ ተመሳሳይ ቁጥር ያላቸውን ቀናት መፆም አለበት:: እነዚያ ለመፆም ከአቅም በላይ ችግር የገጠማቸው ሰዎች ደግሞ አፍጥረው ለየቀኑ እንድ ድሃን የአንድ ጊዜ ምግብ ማብላት ይኖርባቸዋል:: ከዚህ በላይ ቤዛን በመጨመር መልካምንም ስራ የፈቀደ ሰው (እርሱ ፈቅዶ መጨመሩ ለራሱ) በላጭ ተግባር ነው:: ግና በመንገድ ላይ ሆናችሁ መፆማቸሁ ለእናንተ የበለጠ ነው:: የምታውቁ ብትሆኑ ትመርጡታላችሁ::
Esegesi in lingua araba:
شَهۡرُ رَمَضَانَ ٱلَّذِيٓ أُنزِلَ فِيهِ ٱلۡقُرۡءَانُ هُدٗى لِّلنَّاسِ وَبَيِّنَٰتٖ مِّنَ ٱلۡهُدَىٰ وَٱلۡفُرۡقَانِۚ فَمَن شَهِدَ مِنكُمُ ٱلشَّهۡرَ فَلۡيَصُمۡهُۖ وَمَن كَانَ مَرِيضًا أَوۡ عَلَىٰ سَفَرٖ فَعِدَّةٞ مِّنۡ أَيَّامٍ أُخَرَۗ يُرِيدُ ٱللَّهُ بِكُمُ ٱلۡيُسۡرَ وَلَا يُرِيدُ بِكُمُ ٱلۡعُسۡرَ وَلِتُكۡمِلُواْ ٱلۡعِدَّةَ وَلِتُكَبِّرُواْ ٱللَّهَ عَلَىٰ مَا هَدَىٰكُمۡ وَلَعَلَّكُمۡ تَشۡكُرُونَ
185. (ያ እንድትጾሙት የተደነገገላችሁ ወር) በእርሱ ዉስጥ ለሰዎች መሪ ሐቅን መንገድና እውነትን ከዉሸት የሚለየው ገላጭ ቁርአን የተወረደበት የረመዷን ወር ነው:: ከናንተ መካከል ወሩን ያገኘ ሁሉ ይጹመው:: በሽተኛ ወይም በጉዞ ላይ የሆነ ሰው ካፈጠረ ከሌሎች ቀናት ባልፆማቸው ቀናት ቁጥሮች ልክ መፆም አለበት:: አላህ ሁልጊዜም ለእናንተ ገሩን ነገር ይሻል እንጂ በእናንተ ላይ ጫናን መፍጠርን አይሻምና ነው። ለፆም የተወሰኑትን ቀናት ልትሞሉና አላህን ቅንኑ መንገድ ስለመራችሁ ልታከብሩትና ልታመሰግኑት ዘንድ (ይህን ደነገገላችሁ)
Esegesi in lingua araba:
وَإِذَا سَأَلَكَ عِبَادِي عَنِّي فَإِنِّي قَرِيبٌۖ أُجِيبُ دَعۡوَةَ ٱلدَّاعِ إِذَا دَعَانِۖ فَلۡيَسۡتَجِيبُواْ لِي وَلۡيُؤۡمِنُواْ بِي لَعَلَّهُمۡ يَرۡشُدُونَ
186. (መልዕክተኛችን ሙሐመድ ሆይ!) ባሮቼ ስለ እኔ በጠየቁህ ጊዜ እኔ ቅርብ ነኝ:: የለማኝን ጸሎትም በለመነኝ ጊዜ እቀበለዋለሁ:: ስለዚህ ወደ ቀናው መንገድ ይመሩ ዘንድ ለእኔ ብቻ ይታዘዙ:: በእኔም ብቻ ይመኑ። (በላቸው።)
Esegesi in lingua araba:
 
Traduzione dei significati Sura: Al-Baqarah
Indice delle Sure Numero di pagina
 
Traduzione dei Significati del Sacro Corano - Traduzione Amarica - Accademia d'Africa - Indice Traduzioni

Tradotta da Muhammad Zain Zaher al-Din. Pubblicata dall'Accademia d'Africa.

Chiudi