លេខ​ទំព័រ:close

external-link copy
45 : 21

قُلۡ إِنَّمَآ أُنذِرُكُم بِٱلۡوَحۡيِۚ وَلَا يَسۡمَعُ ٱلصُّمُّ ٱلدُّعَآءَ إِذَا مَا يُنذَرُونَ

«የማስፈራራችሁ በተወረደልኝ ብቻ ነው፡፡ ግን ደንቆሮዎች በሚስፈራሩ ጊዜ ጥሪን አይሰሙም» በላቸው፡፡ info
التفاسير: |

external-link copy
46 : 21

وَلَئِن مَّسَّتۡهُمۡ نَفۡحَةٞ مِّنۡ عَذَابِ رَبِّكَ لَيَقُولُنَّ يَٰوَيۡلَنَآ إِنَّا كُنَّا ظَٰلِمِينَ

ከጌታህ ቅጣትም ወላፈን ብትነካቸው «ዋ ጥፋታችን! እኛ በዳዮች ነበርን» ይላሉ፡፡ info
التفاسير: |

external-link copy
47 : 21

وَنَضَعُ ٱلۡمَوَٰزِينَ ٱلۡقِسۡطَ لِيَوۡمِ ٱلۡقِيَٰمَةِ فَلَا تُظۡلَمُ نَفۡسٞ شَيۡـٔٗاۖ وَإِن كَانَ مِثۡقَالَ حَبَّةٖ مِّنۡ خَرۡدَلٍ أَتَيۡنَا بِهَاۗ وَكَفَىٰ بِنَا حَٰسِبِينَ

በትንሣኤም ቀን ትክክለኛ ሚዛኖችን እናቆማለን፡፡ ማንኛይቱም ነፍስ ምንንም አትበደልም፡፡ (ሥራው) የሰናፍጭ ቅንጣት ያክል ቢኾንም እርሷን እናመጣታለን፡፡ ተቆጣጣሪዎችም በኛ በቃ፡፡ info
التفاسير: |

external-link copy
48 : 21

وَلَقَدۡ ءَاتَيۡنَا مُوسَىٰ وَهَٰرُونَ ٱلۡفُرۡقَانَ وَضِيَآءٗ وَذِكۡرٗا لِّلۡمُتَّقِينَ

ለሙሳና ለሃሩንም እውነትንና ውሸትን የሚለይን ብርሃንንም ለጥንቁቆችም መገሰጫን በእርግጥ ሰጠናቸው፡፡ info
التفاسير: |

external-link copy
49 : 21

ٱلَّذِينَ يَخۡشَوۡنَ رَبَّهُم بِٱلۡغَيۡبِ وَهُم مِّنَ ٱلسَّاعَةِ مُشۡفِقُونَ

ለእነዚያ ጌታቸውን በሩቅ ለሚፈሩት እነሱም ከሰዓቲቱ ተጨናቂዎች ለኾኑ (መገሰጫን ሰጠን)፡፡ info
التفاسير: |

external-link copy
50 : 21

وَهَٰذَا ذِكۡرٞ مُّبَارَكٌ أَنزَلۡنَٰهُۚ أَفَأَنتُمۡ لَهُۥ مُنكِرُونَ

ይህም (ቁርኣን) ያወረድነው የኾነ ብሩክ መገሰጫ ነው፡፡ ታዲያ እናንተ ለእርሱ ከሓዲዎች ናችሁን? info
التفاسير: |

external-link copy
51 : 21

۞ وَلَقَدۡ ءَاتَيۡنَآ إِبۡرَٰهِيمَ رُشۡدَهُۥ مِن قَبۡلُ وَكُنَّا بِهِۦ عَٰلِمِينَ

ለኢብራሂምም ከዚያ በፊት ቅን መንገዱን በእርግጥ ሰጠነው፡፡ እኛም በእርሱ (ተገቢነት) ዐዋቂዎች ነበርን፡፡ info
التفاسير: |

external-link copy
52 : 21

إِذۡ قَالَ لِأَبِيهِ وَقَوۡمِهِۦ مَا هَٰذِهِ ٱلتَّمَاثِيلُ ٱلَّتِيٓ أَنتُمۡ لَهَا عَٰكِفُونَ

ለአባቱና ለሕዝቦቹ «ይህቺ ቅርጻ ቅርጽ ያቺ እናንተ ለእርሷ ተገዢዎች የኾናችሁት ምንድን ናት» ባለ ጊዜ (መራነው)፡፡ info
التفاسير: |

external-link copy
53 : 21

قَالُواْ وَجَدۡنَآ ءَابَآءَنَا لَهَا عَٰبِدِينَ

«አባቶቻችንን ለእርሷ ተገዢዎች ኾነው አገኘን» አሉት፡፡ info
التفاسير: |

external-link copy
54 : 21

قَالَ لَقَدۡ كُنتُمۡ أَنتُمۡ وَءَابَآؤُكُمۡ فِي ضَلَٰلٖ مُّبِينٖ

«እናንተም አባቶቻችሁም በእርግጥ በግልጽ ስህተት ውስጥ ነበራችሁ» አላቸው፡፡ info
التفاسير: |

external-link copy
55 : 21

قَالُوٓاْ أَجِئۡتَنَا بِٱلۡحَقِّ أَمۡ أَنتَ مِنَ ٱللَّٰعِبِينَ

«በምሩ መጣህልን ወይንስ አንተ ከሚቀልዱት ነህ?» አሉት፡፡ info
التفاسير: |

external-link copy
56 : 21

قَالَ بَل رَّبُّكُمۡ رَبُّ ٱلسَّمَٰوَٰتِ وَٱلۡأَرۡضِ ٱلَّذِي فَطَرَهُنَّ وَأَنَا۠ عَلَىٰ ذَٰلِكُم مِّنَ ٱلشَّٰهِدِينَ

«አይደለም ጌታችሁ የሰማያትና የምድር ጌታ ያ የፈጠራቸው ነው፡፡ እኔም በዚህ ላይ ከመስካሪዎቹ ነኝ» አለ፡፡ info
التفاسير: |

external-link copy
57 : 21

وَتَٱللَّهِ لَأَكِيدَنَّ أَصۡنَٰمَكُم بَعۡدَ أَن تُوَلُّواْ مُدۡبِرِينَ

«በአላህም እምላለሁ ዟሪዎች ኾናችሁ ከሄዳችሁ በኋላ ጣዖቶቻችሁን ተንኮል እሠራባቸዋለሁ» (አለ)፡፡ info
التفاسير: |

አል አንቢያ