Check out the new design

وه‌رگێڕانی ماناكانی قورئانی پیرۆز - وەرگێڕاوی ئەمهەری - ئەکادیمیای ئەفریقا * - پێڕستی وه‌رگێڕاوه‌كان

PDF XML CSV Excel API
Please review the Terms and Policies

وه‌رگێڕانی ماناكان سوره‌تی: یونس   ئایه‌تی:
وَمِنۡهُم مَّن يَنظُرُ إِلَيۡكَۚ أَفَأَنتَ تَهۡدِي ٱلۡعُمۡيَ وَلَوۡ كَانُواْ لَا يُبۡصِرُونَ
43. ከእነርሱም መካከል ወደ አንተ የሚመለከቱ አሉ:: አንተ ልበ እውራንን የማያዩ ቢሆኑም ትመራለህን?
تەفسیرە عەرەبیەکان:
إِنَّ ٱللَّهَ لَا يَظۡلِمُ ٱلنَّاسَ شَيۡـٔٗا وَلَٰكِنَّ ٱلنَّاسَ أَنفُسَهُمۡ يَظۡلِمُونَ
44. አላህ ሰዎችን ምንም አይበድልም:: ግን ሰዎች ነፍሶቻቸውን ይበድላሉ::
تەفسیرە عەرەبیەکان:
وَيَوۡمَ يَحۡشُرُهُمۡ كَأَن لَّمۡ يَلۡبَثُوٓاْ إِلَّا سَاعَةٗ مِّنَ ٱلنَّهَارِ يَتَعَارَفُونَ بَيۡنَهُمۡۚ قَدۡ خَسِرَ ٱلَّذِينَ كَذَّبُواْ بِلِقَآءِ ٱللَّهِ وَمَا كَانُواْ مُهۡتَدِينَ
45. (መልዕክተኛችን ሙሐመድ ሆይ!) ከሓዲያንን ከቀን አንዲትን ሰዓት እንጂ አንዳልቆዩ መስለው በመካከላቸው የሚተዋወቁ ሲሆኑ በምንሰበስባቸው ቀን የሚከሰተውን አስታውስ:: እነዚያ በአላህ መገናኘት ያስተባበሉት ሁሉ በእርግጥ ከሰሩ:: የተመሩም አልነበሩምና::
تەفسیرە عەرەبیەکان:
وَإِمَّا نُرِيَنَّكَ بَعۡضَ ٱلَّذِي نَعِدُهُمۡ أَوۡ نَتَوَفَّيَنَّكَ فَإِلَيۡنَا مَرۡجِعُهُمۡ ثُمَّ ٱللَّهُ شَهِيدٌ عَلَىٰ مَا يَفۡعَلُونَ
46. (መልዕክተኛችን ሙሐመድ ሆይ!) የዚያንም የምናስፈራራባቸውን ነገር ውጤት ከፊሉን (በሕይወትህ ሳለህ) ብናሳይህ (መልካም ነው):: ወይም ሳናሳይህ ብንገድልህ (ጉዳዩ የእኔ ነው):: መመለሻቸው ወደ እኛ ነውና:: ከዚያ አላህ በሚሠሩት ሥራ ላይ ሁሉ አዋቂ ነው::
تەفسیرە عەرەبیەکان:
وَلِكُلِّ أُمَّةٖ رَّسُولٞۖ فَإِذَا جَآءَ رَسُولُهُمۡ قُضِيَ بَيۡنَهُم بِٱلۡقِسۡطِ وَهُمۡ لَا يُظۡلَمُونَ
47. ለሕዝቦችም ሁሉ መልዕክተኛ አላቸው:: መልዕክተኛቸው በመጣ ጊዜ (ሲያስተባብሉት) በመካከላቸው በትክክል ይፈረዳል:: እነርሱም ፍጹም አይበደሉም::
تەفسیرە عەرەبیەکان:
وَيَقُولُونَ مَتَىٰ هَٰذَا ٱلۡوَعۡدُ إِن كُنتُمۡ صَٰدِقِينَ
48. (መልዕክተኛችን ሙሐመድ ሆይ!) «እውነተኞች ከሆናችሁ የቅጣቱ ቀጠሮ መቼ ነው?» ይላሉ::
تەفسیرە عەرەبیەکان:
قُل لَّآ أَمۡلِكُ لِنَفۡسِي ضَرّٗا وَلَا نَفۡعًا إِلَّا مَا شَآءَ ٱللَّهُۗ لِكُلِّ أُمَّةٍ أَجَلٌۚ إِذَا جَآءَ أَجَلُهُمۡ فَلَا يَسۡتَـٔۡخِرُونَ سَاعَةٗ وَلَا يَسۡتَقۡدِمُونَ
49. (መልዕክተኛችን ሙሐመድ ሆይ!) «ለራሴ ጉዳትን ማድረስም ሆነ ጥቅምን ማስከበር አላህ ከሻው በስተቀር አልችልም:: ለህዝቦች ሁሉ የተወሰነ ጊዜ አላቸው:: ጊዜያቸው በደረሰ ወቅት አንዲትን ሰዓት እንኳን አይቆዩም:: አይቀደሙምም።» በላቸው::
تەفسیرە عەرەبیەکان:
قُلۡ أَرَءَيۡتُمۡ إِنۡ أَتَىٰكُمۡ عَذَابُهُۥ بَيَٰتًا أَوۡ نَهَارٗا مَّاذَا يَسۡتَعۡجِلُ مِنۡهُ ٱلۡمُجۡرِمُونَ
50. (መልዕክተኛችን ሙሐመድ ሆይ!) «እስቲ ንገሩኝ ቅጣቱ በሌሊት ወይም በቀን ቢመጣባችሁ አጋሪዎቹ የሚያስቸኩላቸው ነገር ምንድን ነው?» በላቸው::
تەفسیرە عەرەبیەکان:
أَثُمَّ إِذَا مَا وَقَعَ ءَامَنتُم بِهِۦٓۚ ءَآلۡـَٰٔنَ وَقَدۡ كُنتُم بِهِۦ تَسۡتَعۡجِلُونَ
51. «ከዚያም ቅጣቱ በወደቀ ጊዜ በእርሱ አመናችሁበትን? በእርግጥ በእርሱ የምትቻኮሉ የነበራችሁ ስትሆኑ አሁን ነው የምታምኑትን?» ይባላሉ።
تەفسیرە عەرەبیەکان:
ثُمَّ قِيلَ لِلَّذِينَ ظَلَمُواْ ذُوقُواْ عَذَابَ ٱلۡخُلۡدِ هَلۡ تُجۡزَوۡنَ إِلَّا بِمَا كُنتُمۡ تَكۡسِبُونَ
52. ከዚያ ለእነዚያ ለበደሉት ሰዎች «ዘውታሪውን ቅጣት ቅመሱ። ትሠሩ የነበራችሁትን እኩይ ተግባር ዋጋ እንጂ ትመነዳላችሁን? (አትመነዱም)።» ይባላሉ::
تەفسیرە عەرەبیەکان:
۞ وَيَسۡتَنۢبِـُٔونَكَ أَحَقٌّ هُوَۖ قُلۡ إِي وَرَبِّيٓ إِنَّهُۥ لَحَقّٞۖ وَمَآ أَنتُم بِمُعۡجِزِينَ
53. (መልዕክተኛችን ሙሐመድ ሆይ!) «(ከሞት በኋላ መቀስቀስ) እውነት ነውን?» ሲሉ ይጠይቁሃል:: «አዎን! በጌታዬ እምላለሁ እርሱ እውነት ነው:: እናንተም የምታቅቱ አይደላችሁም።» በላቸው።
تەفسیرە عەرەبیەکان:
 
وه‌رگێڕانی ماناكان سوره‌تی: یونس
پێڕستی سوره‌ته‌كان ژمارەی پەڕە
 
وه‌رگێڕانی ماناكانی قورئانی پیرۆز - وەرگێڕاوی ئەمهەری - ئەکادیمیای ئەفریقا - پێڕستی وه‌رگێڕاوه‌كان

وەرگێڕاوی محمد زەین زەهرەدین. بڵاوکراوەتەوە لە لایەن ئەکادیمیای ئەفریقا.

داخستن