Check out the new design

Kilniojo Korano reikšmių vertimas - Vertimas į amharų k. - Afrikos akademija * - Vertimų turinys

PDF XML CSV Excel API
Please review the Terms and Policies

Reikšmių vertimas Sūra: Al-Anbija   Aja (Korano eilutė):
وَكَمۡ قَصَمۡنَا مِن قَرۡيَةٖ كَانَتۡ ظَالِمَةٗ وَأَنشَأۡنَا بَعۡدَهَا قَوۡمًا ءَاخَرِينَ
11. በዳይም ከነበረች ከተማ ያጠፋናትና ከኋላዋም ሌሎችን ህዝቦች ያስገኘነው ብዙ ናት::
Tafsyrai arabų kalba:
فَلَمَّآ أَحَسُّواْ بَأۡسَنَآ إِذَا هُم مِّنۡهَا يَرۡكُضُونَ
12. ቅጣታችንም በተሰማቸው ጊዜ እነርሱ ወዲያውኑ ከርሷ ለመሸሽ ይገሰግሳሉ።
Tafsyrai arabų kalba:
لَا تَرۡكُضُواْ وَٱرۡجِعُوٓاْ إِلَىٰ مَآ أُتۡرِفۡتُمۡ فِيهِ وَمَسَٰكِنِكُمۡ لَعَلَّكُمۡ تُسۡـَٔلُونَ
13. «አትገስግሱ፤ ትጠየቁም ይሆናልና በእርሱ ወደ ተቀማጠላችሁበት ጸጋ ወደ መኖሪያዎቻችሁም ተመለሱ።» ይባላሉ።
Tafsyrai arabų kalba:
قَالُواْ يَٰوَيۡلَنَآ إِنَّا كُنَّا ظَٰلِمِينَ
14. «ዋ ጥፋታችን! እኛ በእርግጥ በዳዮች ነበርን።» ይላሉ።
Tafsyrai arabų kalba:
فَمَا زَالَت تِّلۡكَ دَعۡوَىٰهُمۡ حَتَّىٰ جَعَلۡنَٰهُمۡ حَصِيدًا خَٰمِدِينَ
15.የታጨዱ ሬሳዎችም እስካደረግናቸው ድረስ ይህቺ ጥሪያቸው ከመሆን አልተወገደችም::
Tafsyrai arabų kalba:
وَمَا خَلَقۡنَا ٱلسَّمَآءَ وَٱلۡأَرۡضَ وَمَا بَيۡنَهُمَا لَٰعِبِينَ
16. ሰማይንና ምድርን በመካከላቸው ያለውንም ሁሉ ቀላጆች ሆነን አልፈጠርንም::
Tafsyrai arabų kalba:
لَوۡ أَرَدۡنَآ أَن نَّتَّخِذَ لَهۡوٗا لَّٱتَّخَذۡنَٰهُ مِن لَّدُنَّآ إِن كُنَّا فَٰعِلِينَ
17.መጫዎቻን (ሚስትንና ልጅን) ልንይዝ በሻን ኖሮ ከኛ ዘንድ በያዝነው ነበር፤ ግን ሰሪዎች አይደለንም።
Tafsyrai arabų kalba:
بَلۡ نَقۡذِفُ بِٱلۡحَقِّ عَلَى ٱلۡبَٰطِلِ فَيَدۡمَغُهُۥ فَإِذَا هُوَ زَاهِقٞۚ وَلَكُمُ ٱلۡوَيۡلُ مِمَّا تَصِفُونَ
18. በእርግጥ እውነትን በውሸት ላይ እንጥላለን:: አንጎሉን ያፈርሰዋልም:: ወዲያዉም እርሱ ጠፊ ነው:: ለእናንተም ከዚያ (ሚስትና ልጅ) አለው በማለት ከምትመጥኑት ነገር ብርቱ ቅጣት አላችሁ:: (ወዮላችሁ)።
Tafsyrai arabų kalba:
وَلَهُۥ مَن فِي ٱلسَّمَٰوَٰتِ وَٱلۡأَرۡضِۚ وَمَنۡ عِندَهُۥ لَا يَسۡتَكۡبِرُونَ عَنۡ عِبَادَتِهِۦ وَلَا يَسۡتَحۡسِرُونَ
19. በሰማያትና በምድር ዉስጥ ያለው ሁሉም የእርሱ ብቻ ነው:: እርሱ ዘንድ ያሉትም መላእክት እርሱን ከመገዛት አይኮሩም:: አይሰለቹምም።
Tafsyrai arabų kalba:
يُسَبِّحُونَ ٱلَّيۡلَ وَٱلنَّهَارَ لَا يَفۡتُرُونَ
20. በበሌሊትና በቀንም ያጠሩታል:: አይታክቱም።
Tafsyrai arabų kalba:
أَمِ ٱتَّخَذُوٓاْ ءَالِهَةٗ مِّنَ ٱلۡأَرۡضِ هُمۡ يُنشِرُونَ
21. ይልቁንም ከምድር የሆኑን ሙታንን የሚያስነሱ አማልክትን ያዙን? የለም።
Tafsyrai arabų kalba:
لَوۡ كَانَ فِيهِمَآ ءَالِهَةٌ إِلَّا ٱللَّهُ لَفَسَدَتَاۚ فَسُبۡحَٰنَ ٱللَّهِ رَبِّ ٱلۡعَرۡشِ عَمَّا يَصِفُونَ
22.በሰማያትና በምድር ውስጥ ከአላህ ሌላ አማልክት በነበሩ ኖሮ ሁለቱም በተበላሹ ነበር:: የዐርሹ ጌታ አላህም ከሚሉት ሁሉ ጠራ::
Tafsyrai arabų kalba:
لَا يُسۡـَٔلُ عَمَّا يَفۡعَلُ وَهُمۡ يُسۡـَٔلُونَ
23. አላህ ከሚሰራው ሁሉ አይጠየቅም:: እነርሱ (ፍጥረቶቹ) ግን ይጠየቃሉ::
Tafsyrai arabų kalba:
أَمِ ٱتَّخَذُواْ مِن دُونِهِۦٓ ءَالِهَةٗۖ قُلۡ هَاتُواْ بُرۡهَٰنَكُمۡۖ هَٰذَا ذِكۡرُ مَن مَّعِيَ وَذِكۡرُ مَن قَبۡلِيۚ بَلۡ أَكۡثَرُهُمۡ لَا يَعۡلَمُونَ ٱلۡحَقَّۖ فَهُم مُّعۡرِضُونَ
24. (መልዕክተኛችን ሙሐመድ ሆይ!) ይልቁንም ከርሱ ሌላ አማልክትን ያዙን? «አስረጃችሁን አምጡ:: ይህ ቁርኣን እኔ ዘንድ ያለው ህዝብ መገሰጫ፤ ከኔ በፊትም የነበሩት ህዝቦች መገሠጫ ነው።» በላቸው:: እንዲያዉም አብዛኞቻቸው እውነቱን አያውቁም:: ስለዚህ እነርሱ እንቢተኞች ናቸው::
Tafsyrai arabų kalba:
 
Reikšmių vertimas Sūra: Al-Anbija
Sūrų turinys Puslapio numeris
 
Kilniojo Korano reikšmių vertimas - Vertimas į amharų k. - Afrikos akademija - Vertimų turinys

Išvertė Muchamed Zain Zahr Ad-Din. Išleido Afrikos akademija.

Uždaryti