Check out the new design

Kilniojo Korano reikšmių vertimas - Vertimas į amharų k. - Afrikos akademija * - Vertimų turinys

PDF XML CSV Excel API
Please review the Terms and Policies

Reikšmių vertimas Sūra: Aš-Šu’ara   Aja (Korano eilutė):
وَٱتَّقُواْ ٱلَّذِي خَلَقَكُمۡ وَٱلۡجِبِلَّةَ ٱلۡأَوَّلِينَ
184. «ያንንም የፈጠራችሁን የቀድሞዎቹንም ፍጡሮች የፈጠረውን ፍሩ።» (ባለ ጊዜ የሆነውን አስታውስ)
Tafsyrai arabų kalba:
قَالُوٓاْ إِنَّمَآ أَنتَ مِنَ ٱلۡمُسَحَّرِينَ
185. እነርሱም አሉ: «ሹዓይብ ሆይ! አንተ በብዛት ከተደገመባቸው ሰዎች አንዱ ነህ።
Tafsyrai arabų kalba:
وَمَآ أَنتَ إِلَّا بَشَرٞ مِّثۡلُنَا وَإِن نَّظُنُّكَ لَمِنَ ٱلۡكَٰذِبِينَ
186. «አንተም ብጤያችን ሰው እንጂ ሌላ አይደለህም:: እነሆ ከውሸታሞች ነህ ብለን እንጠረጥርሃለን፤
Tafsyrai arabų kalba:
فَأَسۡقِطۡ عَلَيۡنَا كِسَفٗا مِّنَ ٱلسَّمَآءِ إِن كُنتَ مِنَ ٱلصَّٰدِقِينَ
187. «ከእውነተኞችም እንደሆንክ በእኛ ላይ ከሰማይ ቁራጭን ጣልብን።» (አሉ)
Tafsyrai arabų kalba:
قَالَ رَبِّيٓ أَعۡلَمُ بِمَا تَعۡمَلُونَ
188. «ጌታዬ የምትሰሩትን ሁሉ አዋቂ ነው።» አላቸው።
Tafsyrai arabų kalba:
فَكَذَّبُوهُ فَأَخَذَهُمۡ عَذَابُ يَوۡمِ ٱلظُّلَّةِۚ إِنَّهُۥ كَانَ عَذَابَ يَوۡمٍ عَظِيمٍ
189. አስተባበሉትም የጥላይቱ ቀን ቅጣትም ያዛቸው፤ እርሱ የከባድ ቀን ቅጣት ነበርና::
Tafsyrai arabų kalba:
إِنَّ فِي ذَٰلِكَ لَأٓيَةٗۖ وَمَا كَانَ أَكۡثَرُهُم مُّؤۡمِنِينَ
190. በዚህ ውስጥ አስደናቂ ተዐምር አለበት:: አብዛዛቻቸዉም አማኞች አልነበሩም::
Tafsyrai arabų kalba:
وَإِنَّ رَبَّكَ لَهُوَ ٱلۡعَزِيزُ ٱلرَّحِيمُ
191. (መልዕክተኛችን ሙሐመድ ሆይ!) ጌታህም እርሱ በእርግጥ አሸናፊዉንና አዛኙ ነው::
Tafsyrai arabų kalba:
وَإِنَّهُۥ لَتَنزِيلُ رَبِّ ٱلۡعَٰلَمِينَ
192. (መልዕክተኛችን ሙሐመድ ሆይ!) እርሱም (ቁርኣን) በእርግጥ ከዓለማት ጌታ የተወረደ ነው::
Tafsyrai arabų kalba:
نَزَلَ بِهِ ٱلرُّوحُ ٱلۡأَمِينُ
193. እርሱን ታማኙ መንፈስ ጂብሪል አወረደው::
Tafsyrai arabų kalba:
عَلَىٰ قَلۡبِكَ لِتَكُونَ مِنَ ٱلۡمُنذِرِينَ
194. ከአስፈራሪዎች ነብያት ትሆን ዘንድ በልብህ ላይ አወረደው፤
Tafsyrai arabų kalba:
بِلِسَانٍ عَرَبِيّٖ مُّبِينٖ
195. ግልጽ በሆነ ዐረብኛ ቋንቋ፤ (አወረደው)
Tafsyrai arabų kalba:
وَإِنَّهُۥ لَفِي زُبُرِ ٱلۡأَوَّلِينَ
196. እርሱም (ቁርኣን) በቀድሞዎቹ መጽሐፍት ውስጥ የተወሳ ነው::
Tafsyrai arabų kalba:
أَوَلَمۡ يَكُن لَّهُمۡ ءَايَةً أَن يَعۡلَمَهُۥ عُلَمَٰٓؤُاْ بَنِيٓ إِسۡرَٰٓءِيلَ
197. የኢስራኢል ልጆች ሊቃውንት የሚያውቁት መሆኑ ለእነርሱ (ለመካ ከሓዲያን) ምልክት አይሆናቸዉም?
Tafsyrai arabų kalba:
وَلَوۡ نَزَّلۡنَٰهُ عَلَىٰ بَعۡضِ ٱلۡأَعۡجَمِينَ
198. ከአዕጀሞች ባንዱ ላይ ባወረድነዉም ኖሮ
Tafsyrai arabų kalba:
فَقَرَأَهُۥ عَلَيۡهِم مَّا كَانُواْ بِهِۦ مُؤۡمِنِينَ
199. በእነርሱ ላይ ቢያነበዉም በእርሱ አማኞች አይሆኑም ነበር::
Tafsyrai arabų kalba:
كَذَٰلِكَ سَلَكۡنَٰهُ فِي قُلُوبِ ٱلۡمُجۡرِمِينَ
200. እንድዚሁ ማስተባበልን በተንኮለኞች ልቦች ውስጥ አስገባነው::
Tafsyrai arabų kalba:
لَا يُؤۡمِنُونَ بِهِۦ حَتَّىٰ يَرَوُاْ ٱلۡعَذَابَ ٱلۡأَلِيمَ
201. አሳማሚ ቅጣትን እስከሚያዩ ድረስ በእርሱ አያምኑም::
Tafsyrai arabų kalba:
فَيَأۡتِيَهُم بَغۡتَةٗ وَهُمۡ لَا يَشۡعُرُونَ
202. እነርሱ የማያውቁ ሲሆኑ ቅጣቱ ድንገት እስከሚመጣባቸዉም ድረስ (አያምኑም)::
Tafsyrai arabų kalba:
فَيَقُولُواْ هَلۡ نَحۡنُ مُنظَرُونَ
203. በመጣባቸው ጊዜ: «እኛ የምንቆይ ነን?» እስከሚሉም (አያምኑም)።
Tafsyrai arabų kalba:
أَفَبِعَذَابِنَا يَسۡتَعۡجِلُونَ
204. በቅጣታችን ያቻኩላሉን?
Tafsyrai arabų kalba:
أَفَرَءَيۡتَ إِن مَّتَّعۡنَٰهُمۡ سِنِينَ
205. (መልዕክተኛችን ሙሐመድ ሆይ! ) አየህን? ብዙ ዓመታትን ብናጣቅማቸው::
Tafsyrai arabų kalba:
ثُمَّ جَآءَهُم مَّا كَانُواْ يُوعَدُونَ
206. ከዚያም ያ ይስፈራሩበት የነበሩት ቢመጣባቸው
Tafsyrai arabų kalba:
 
Reikšmių vertimas Sūra: Aš-Šu’ara
Sūrų turinys Puslapio numeris
 
Kilniojo Korano reikšmių vertimas - Vertimas į amharų k. - Afrikos akademija - Vertimų turinys

Išvertė Muchamed Zain Zahr Ad-Din. Išleido Afrikos akademija.

Uždaryti