Check out the new design

Kilniojo Korano reikšmių vertimas - Vertimas į amharų k. - Afrikos akademija * - Vertimų turinys


Reikšmių vertimas Sūra: An-Naml   Aja (Korano eilutė):

አን ነምል

طسٓۚ تِلۡكَ ءَايَٰتُ ٱلۡقُرۡءَانِ وَكِتَابٖ مُّبِينٍ
1. ጣ፤ ሲን፤ ይህ ከቁርኣኑና ከገላጩ መጽሐፍ አናቅጽ ነው።
Tafsyrai arabų kalba:
هُدٗى وَبُشۡرَىٰ لِلۡمُؤۡمِنِينَ
2. ለምዕምናን መሪና ብስራት ነው::
Tafsyrai arabų kalba:
ٱلَّذِينَ يُقِيمُونَ ٱلصَّلَوٰةَ وَيُؤۡتُونَ ٱلزَّكَوٰةَ وَهُم بِٱلۡأٓخِرَةِ هُمۡ يُوقِنُونَ
3. ለእነዚያ ሶላትን ለሚሰግዱት፤ ዘካንም ለሚሰጡ፤ እነርሱም በመጨረሻይቱ ሕይወት እነርሱ የሚያረጋግጡ ለሆኑት::
Tafsyrai arabų kalba:
إِنَّ ٱلَّذِينَ لَا يُؤۡمِنُونَ بِٱلۡأٓخِرَةِ زَيَّنَّا لَهُمۡ أَعۡمَٰلَهُمۡ فَهُمۡ يَعۡمَهُونَ
4. እነዚያ በመጨረሻይቱ ዓለም የማያምኑት ለእነርሱ ክፉ ሥራዎቻቸውን ሸለምንላቸው:: ስለዚህ እነርሱ ይዋልላሉ::
Tafsyrai arabų kalba:
أُوْلَٰٓئِكَ ٱلَّذِينَ لَهُمۡ سُوٓءُ ٱلۡعَذَابِ وَهُمۡ فِي ٱلۡأٓخِرَةِ هُمُ ٱلۡأَخۡسَرُونَ
5. እነርሱ እነዚያ ክፉ ቅጣት ያላባቸው ናቸው:: እነርሱም በመጨረሻይቱ ዓለም እነርሱ በጣም ከከሳሪዎቹ ናቸው::
Tafsyrai arabų kalba:
وَإِنَّكَ لَتُلَقَّى ٱلۡقُرۡءَانَ مِن لَّدُنۡ حَكِيمٍ عَلِيمٍ
6. (መልዕክተኛችን ሙሐመድ ሆይ!) አንተም ቁርኣንን ጥበበኛና አዋቂ ከሆነው ጌታህ ዘንድ በእርግጥ ትስሰጣለህ::
Tafsyrai arabų kalba:
إِذۡ قَالَ مُوسَىٰ لِأَهۡلِهِۦٓ إِنِّيٓ ءَانَسۡتُ نَارٗا سَـَٔاتِيكُم مِّنۡهَا بِخَبَرٍ أَوۡ ءَاتِيكُم بِشِهَابٖ قَبَسٖ لَّعَلَّكُمۡ تَصۡطَلُونَ
7. (መልዕክተኛችን ሙሐመድ ሆይ!) ሙሳ ለቤተሰቦቹ «እኔ እሳትን አየሁ ከእርሷ ወሬን አመጣላችኋለሁ፤ ወይም ትሞቁ ዘንድ የተለኮሰ ችቦን አመጣላችኋለሁ» ባለ ጊዜ የሆነውን አውሳላቸው።
Tafsyrai arabų kalba:
فَلَمَّا جَآءَهَا نُودِيَ أَنۢ بُورِكَ مَن فِي ٱلنَّارِ وَمَنۡ حَوۡلَهَا وَسُبۡحَٰنَ ٱللَّهِ رَبِّ ٱلۡعَٰلَمِينَ
8. በመጣትም ጊዜ እንዲህ በማለት ተጠራ፡- «በእሳቲቱ ያለው ሰውና በዙሪያዋ ያሉም ሰዎች ሁሉ ተባረኩ:: የዓለማትም ጌታ አላህ ጥራት ይገባው።
Tafsyrai arabų kalba:
يَٰمُوسَىٰٓ إِنَّهُۥٓ أَنَا ٱللَّهُ ٱلۡعَزِيزُ ٱلۡحَكِيمُ
9. «ሙሳ ሆይ! እነሆ እኔ አሸናፊዉና ጥበበኛው (አምላክህ) አላህ ነኝ።
Tafsyrai arabų kalba:
وَأَلۡقِ عَصَاكَۚ فَلَمَّا رَءَاهَا تَهۡتَزُّ كَأَنَّهَا جَآنّٞ وَلَّىٰ مُدۡبِرٗا وَلَمۡ يُعَقِّبۡۚ يَٰمُوسَىٰ لَا تَخَفۡ إِنِّي لَا يَخَافُ لَدَيَّ ٱلۡمُرۡسَلُونَ
10. «በትርህንም ጣል» (ተባለና ጣለም):: እርሷ እንደ ትንሽ እባብ በፍጥነት ስትስለከለክ ባያትም ጊዜ ፊቱን አዙሮ ሸሸ:: አልተመለሰምም:: «ሙሳ ሆይ! አትፍራ:: መልዕክተኞች እኔ ዘንድ ፈጽሞ አይፈሩምና።
Tafsyrai arabų kalba:
إِلَّا مَن ظَلَمَ ثُمَّ بَدَّلَ حُسۡنَۢا بَعۡدَ سُوٓءٖ فَإِنِّي غَفُورٞ رَّحِيمٞ
11. «ግን የበደለ ሰው ከዚያም ከመጥፎ ሥራው በኋላ መልካምን የለወጠ እኔ መሓሪ፤ አዛኝ ነኝ።
Tafsyrai arabų kalba:
وَأَدۡخِلۡ يَدَكَ فِي جَيۡبِكَ تَخۡرُجۡ بَيۡضَآءَ مِنۡ غَيۡرِ سُوٓءٖۖ فِي تِسۡعِ ءَايَٰتٍ إِلَىٰ فِرۡعَوۡنَ وَقَوۡمِهِۦٓۚ إِنَّهُمۡ كَانُواْ قَوۡمٗا فَٰسِقِينَ
12. «እጅህንም በአንገትየህ ውስጥ አስገባ ያለ ነውር (ወይም ያለ ለምጽ) ነጭ ሆና ትወጣለችና በዘጠኝ ታዐምራት ወደ ፈርዖንና ወደ ሕዝቦቹ ሂድ እነርሱ አመጸኞች ህዝቦች ናቸውና።»
Tafsyrai arabų kalba:
فَلَمَّا جَآءَتۡهُمۡ ءَايَٰتُنَا مُبۡصِرَةٗ قَالُواْ هَٰذَا سِحۡرٞ مُّبِينٞ
13. ተዓምራታችንም ግልጽ ሆና በመጣቻቸው ጊዜ «ይህ ግልጽ ድግምት ነው።» አሉ።
Tafsyrai arabų kalba:
 
Reikšmių vertimas Sūra: An-Naml
Sūrų turinys Puslapio numeris
 
Kilniojo Korano reikšmių vertimas - Vertimas į amharų k. - Afrikos akademija - Vertimų turinys

Išvertė Muchamed Zain Zahr Ad-Din. Išleido Afrikos akademija.

Uždaryti