Check out the new design

Kilniojo Korano reikšmių vertimas - Vertimas į amharų k. - Afrikos akademija * - Vertimų turinys

PDF XML CSV Excel API
Please review the Terms and Policies

Reikšmių vertimas Sūra: Al-’Imran   Aja (Korano eilutė):
وَلَئِن مُّتُّمۡ أَوۡ قُتِلۡتُمۡ لَإِلَى ٱللَّهِ تُحۡشَرُونَ
158. በጂሃድ ብትሞቱ ወይም ብትገደሉ ወደ አላህ ብቻ ትሰበሰባላችሁ::
Tafsyrai arabų kalba:
فَبِمَا رَحۡمَةٖ مِّنَ ٱللَّهِ لِنتَ لَهُمۡۖ وَلَوۡ كُنتَ فَظًّا غَلِيظَ ٱلۡقَلۡبِ لَٱنفَضُّواْ مِنۡ حَوۡلِكَۖ فَٱعۡفُ عَنۡهُمۡ وَٱسۡتَغۡفِرۡ لَهُمۡ وَشَاوِرۡهُمۡ فِي ٱلۡأَمۡرِۖ فَإِذَا عَزَمۡتَ فَتَوَكَّلۡ عَلَى ٱللَّهِۚ إِنَّ ٱللَّهَ يُحِبُّ ٱلۡمُتَوَكِّلِينَ
159. (መልዕክተኛችን ሙሐመድ ሆይ!) በአላህ ችሮታ ለዘብክላቸው:: አመለ መጥፎና ልበ ደረቅ በሆንክ ኖሮ ከአጠገብህ በተበተኑ ነበር:: ከእነርሱም ጥፋት ይቅር በል:: ለእነርሱም ከአላህ ምህረትን ለምንላቸው:: በሁሉም ነገር ላይ አማክራቸው:: ከዚያ ቁርጥ ሀሳብ ባደረገክ ጊዜ በአላህ ላይ ብቻ ተመካ:: አላህ በእርሱ ላይ ብቻ ተመኪዎችን ይወዳልና::
Tafsyrai arabų kalba:
إِن يَنصُرۡكُمُ ٱللَّهُ فَلَا غَالِبَ لَكُمۡۖ وَإِن يَخۡذُلۡكُمۡ فَمَن ذَا ٱلَّذِي يَنصُرُكُم مِّنۢ بَعۡدِهِۦۗ وَعَلَى ٱللَّهِ فَلۡيَتَوَكَّلِ ٱلۡمُؤۡمِنُونَ
160. (ሙስሊሞች ሆይ!) አላህ ከረዳችሁ እናንተን የሚያሸንፍ የለም:: እርሱ ካዋረዳቸሁ ደግሞ ከእርሱ ማዋረድ በኋላ የሚረዳችሁ ያ ማን ነው? አማኞች በአላህ ላይ ብቻ ይመኩ።
Tafsyrai arabų kalba:
وَمَا كَانَ لِنَبِيٍّ أَن يَغُلَّۚ وَمَن يَغۡلُلۡ يَأۡتِ بِمَا غَلَّ يَوۡمَ ٱلۡقِيَٰمَةِۚ ثُمَّ تُوَفَّىٰ كُلُّ نَفۡسٖ مَّا كَسَبَتۡ وَهُمۡ لَا يُظۡلَمُونَ
161. የምርኮን ገንዘብ መደበቅ ከነብይ የሚሆን አይደለም። የምርኮን ገንዘብ የሚደብቅም በትንሳኤ ቀን የደበቀውን ነገር ተሸክሞ ይመጣል:: ከዚያ ነፍስ ሁሉ የስራዋን ዋጋ ትመነዳለች:: እነርሱም አይበደሉም።
Tafsyrai arabų kalba:
أَفَمَنِ ٱتَّبَعَ رِضۡوَٰنَ ٱللَّهِ كَمَنۢ بَآءَ بِسَخَطٖ مِّنَ ٱللَّهِ وَمَأۡوَىٰهُ جَهَنَّمُۖ وَبِئۡسَ ٱلۡمَصِيرُ
162. የአላህን ውዴታ የተከተለ ሁሉ የአላህን ቁጣ እንዳተረፈና መኖሪያውም ገሀነም እንደሆነው ነውን? ገሀነም ማረፊያነቱ እጅግ ከፋ!
Tafsyrai arabų kalba:
هُمۡ دَرَجَٰتٌ عِندَ ٱللَّهِۗ وَٱللَّهُ بَصِيرُۢ بِمَا يَعۡمَلُونَ
163. ሁሉም በአላህ ዘንድ ባለ ልዩ ልዩ ደረጃዎች ናቸው:: አላህ የሚሰሩትን ሁሉ ተመልካች ነውና::
Tafsyrai arabų kalba:
لَقَدۡ مَنَّ ٱللَّهُ عَلَى ٱلۡمُؤۡمِنِينَ إِذۡ بَعَثَ فِيهِمۡ رَسُولٗا مِّنۡ أَنفُسِهِمۡ يَتۡلُواْ عَلَيۡهِمۡ ءَايَٰتِهِۦ وَيُزَكِّيهِمۡ وَيُعَلِّمُهُمُ ٱلۡكِتَٰبَ وَٱلۡحِكۡمَةَ وَإِن كَانُواْ مِن قَبۡلُ لَفِي ضَلَٰلٖ مُّبِينٍ
164. አላህ በአማኞች ላይ ከመካከላቸው የሆነን፤ በእነርሱም ላይ አናቅጽን የሚያነብ፤ ከርክሰት የሚያጠራቸው፤ መጽሐፍንና ጥበብንም የሚያስተምራቸውን መልዕክተኛ በላከላቸው ጊዜ በእርግጥ ለገሰላቸው:: እነርሱም ከዚያ በፊት ግልጽ ስህተት ውስጥ ነበሩ::
Tafsyrai arabų kalba:
أَوَلَمَّآ أَصَٰبَتۡكُم مُّصِيبَةٞ قَدۡ أَصَبۡتُم مِّثۡلَيۡهَا قُلۡتُمۡ أَنَّىٰ هَٰذَاۖ قُلۡ هُوَ مِنۡ عِندِ أَنفُسِكُمۡۗ إِنَّ ٱللَّهَ عَلَىٰ كُلِّ شَيۡءٖ قَدِيرٞ
165. (መልዕክተኛችን ሙሐመድ ሆይ!) «እናንተ ያደረሳችሁትን ጥቃት ግማሽ በአገኛችሁ (በደረሰባችሁ) ጊዜ ይህ ከየት ነው የመጣብን አላችሁን? እርሱ ከነፍሶቻችሁ ዘንድ ነው:: አላህም በነገሩ ሁሉ ላይ ቻይ ነው።» በላቸው።
Tafsyrai arabų kalba:
 
Reikšmių vertimas Sūra: Al-’Imran
Sūrų turinys Puslapio numeris
 
Kilniojo Korano reikšmių vertimas - Vertimas į amharų k. - Afrikos akademija - Vertimų turinys

Išvertė Muchamed Zain Zahr Ad-Din. Išleido Afrikos akademija.

Uždaryti