Check out the new design

Kilniojo Korano reikšmių vertimas - Vertimas į amharų k. - Afrikos akademija * - Vertimų turinys


Reikšmių vertimas Sūra: Al-Ahzab   Aja (Korano eilutė):
تَحِيَّتُهُمۡ يَوۡمَ يَلۡقَوۡنَهُۥ سَلَٰمٞۚ وَأَعَدَّ لَهُمۡ أَجۡرٗا كَرِيمٗا
44. በሚገናኙበት ቀን መከባበሪያቸው ሰላም መባባል ነው:: ለእነርሱም የከበረን ምንዳ አዘጋጅቶላቸዋል::
Tafsyrai arabų kalba:
يَٰٓأَيُّهَا ٱلنَّبِيُّ إِنَّآ أَرۡسَلۡنَٰكَ شَٰهِدٗا وَمُبَشِّرٗا وَنَذِيرٗا
45. አንተ ነብይ ሆይ! እኛ መስካሪ አብሳሪና አስፈራሪ አድርገን ላክንህ::
Tafsyrai arabų kalba:
وَدَاعِيًا إِلَى ٱللَّهِ بِإِذۡنِهِۦ وَسِرَاجٗا مُّنِيرٗا
46. ወደ አላህም በፈቃዱ ጠሪ፣ አብሪና ብርሃን አድርገን ላክንህ::
Tafsyrai arabų kalba:
وَبَشِّرِ ٱلۡمُؤۡمِنِينَ بِأَنَّ لَهُم مِّنَ ٱللَّهِ فَضۡلٗا كَبِيرٗا
47. (መልዕክተኛችን ሙሐመድ ሆይ!) አማኞችንም ከአላህ ዘንድ ለእነርሱ ታላቅ ችሮታ ያላቸው መሆኑን አብስራቸው::
Tafsyrai arabų kalba:
وَلَا تُطِعِ ٱلۡكَٰفِرِينَ وَٱلۡمُنَٰفِقِينَ وَدَعۡ أَذَىٰهُمۡ وَتَوَكَّلۡ عَلَى ٱللَّهِۚ وَكَفَىٰ بِٱللَّهِ وَكِيلٗا
48. (መልዕክተኛችን ሙሐመድ ሆይ!) ከሓዲያንና አስመሳዮችንም አትታዘዛቸው ማሰቃየታቸውንም (ለአላህ) ተው:: በአላህም ላይ ተጠጋ:: በመጠጊያነትም አላህ በቃ::
Tafsyrai arabų kalba:
يَٰٓأَيُّهَا ٱلَّذِينَ ءَامَنُوٓاْ إِذَا نَكَحۡتُمُ ٱلۡمُؤۡمِنَٰتِ ثُمَّ طَلَّقۡتُمُوهُنَّ مِن قَبۡلِ أَن تَمَسُّوهُنَّ فَمَا لَكُمۡ عَلَيۡهِنَّ مِنۡ عِدَّةٖ تَعۡتَدُّونَهَاۖ فَمَتِّعُوهُنَّ وَسَرِّحُوهُنَّ سَرَاحٗا جَمِيلٗا
49. እናንተ ያመናችሁ ሆይ! ምዕመናትን ባገባችሁና ከዚያም ሳትነኳቸው በፊት በፈታችኋቸው ጊዜ ለናንተ በእነርሱ ላይ የምትቆጥሩዋት ዒዳ ምንም የላችሁም:: ሆኖም አጣቅሟቸው (ጉርሻ ስጧቸው):: መልካም ማሰናበትንም አሰናብቷቸው::
Tafsyrai arabų kalba:
يَٰٓأَيُّهَا ٱلنَّبِيُّ إِنَّآ أَحۡلَلۡنَا لَكَ أَزۡوَٰجَكَ ٱلَّٰتِيٓ ءَاتَيۡتَ أُجُورَهُنَّ وَمَا مَلَكَتۡ يَمِينُكَ مِمَّآ أَفَآءَ ٱللَّهُ عَلَيۡكَ وَبَنَاتِ عَمِّكَ وَبَنَاتِ عَمَّٰتِكَ وَبَنَاتِ خَالِكَ وَبَنَاتِ خَٰلَٰتِكَ ٱلَّٰتِي هَاجَرۡنَ مَعَكَ وَٱمۡرَأَةٗ مُّؤۡمِنَةً إِن وَهَبَتۡ نَفۡسَهَا لِلنَّبِيِّ إِنۡ أَرَادَ ٱلنَّبِيُّ أَن يَسۡتَنكِحَهَا خَالِصَةٗ لَّكَ مِن دُونِ ٱلۡمُؤۡمِنِينَۗ قَدۡ عَلِمۡنَا مَا فَرَضۡنَا عَلَيۡهِمۡ فِيٓ أَزۡوَٰجِهِمۡ وَمَا مَلَكَتۡ أَيۡمَٰنُهُمۡ لِكَيۡلَا يَكُونَ عَلَيۡكَ حَرَجٞۗ وَكَانَ ٱللَّهُ غَفُورٗا رَّحِيمٗا
50. አንተ ነብይ ሆይ! እነዚያን መህሮቻቸውን የሰጠሃቸውን ሚስቶችህን፤ አላህ ባንተ ላይ ከመለሰልህም ሴቶች መካከል እነዚያን እጅህ የጨበጠቻቸውን ምርኮኞች ሴቶች፤ እነዚያን ካንተ ጋር የተሰደዱትን የአጎቶችህንና፤ የአክስቶችህን ሴት ልጆች (እንደዚሁም) የእናትህ ወንድም ሴት ልጆችና የእናትህ እህት ሴት ልጆች ማግባትን ላንተ ፈቅደንልሃል:: ማንኛዋም በአላህ ያመነች ሴት ራሷን ለነብዩ ብትሰጥ ነብዩ ሊያገባት የፈለገ እንደ ሆነ ከአማኞች ሌላ ላንተ ብቻ የተሰጠ መብት ሲሆን ፈቀድንልህ:: በአማኞች ላይ በሚስቶቻቸውና እጆቻቸው በጨበጧቸው ባሮች ነገር ግዴታ ያደረግንባቸውን በእርግጥ አውቀናል:: ባንተ ላይ ችግር እንዳይኖር ያለፉትን ፈቀድንልህ:: አላህ መሃሪና አዛኝ ነውና::
Tafsyrai arabų kalba:
 
Reikšmių vertimas Sūra: Al-Ahzab
Sūrų turinys Puslapio numeris
 
Kilniojo Korano reikšmių vertimas - Vertimas į amharų k. - Afrikos akademija - Vertimų turinys

Išvertė Muchamed Zain Zahr Ad-Din. Išleido Afrikos akademija.

Uždaryti