Check out the new design

Kilniojo Korano reikšmių vertimas - Vertimas į amharų k. - Afrikos akademija * - Vertimų turinys


Reikšmių vertimas Sūra: As-Saffat   Aja (Korano eilutė):
يَقُولُ أَءِنَّكَ لَمِنَ ٱلۡمُصَدِّقِينَ
52. (እንዲህ) የሚል: ‹በእርግጥ አንተ ከሚያምኑት ነህን?
Tafsyrai arabų kalba:
أَءِذَا مِتۡنَا وَكُنَّا تُرَابٗا وَعِظَٰمًا أَءِنَّا لَمَدِينُونَ
53. ‹በሞትንና ዐፈር አጥንቶችም በሆነ ጊዜ እኛ በእርግጥ እኛ እንመረመራለን?› የሚልም።
Tafsyrai arabų kalba:
قَالَ هَلۡ أَنتُم مُّطَّلِعُونَ
54. እናንተ ተመልካቾች ናችሁን? ይላል::
Tafsyrai arabų kalba:
فَٱطَّلَعَ فَرَءَاهُ فِي سَوَآءِ ٱلۡجَحِيمِ
55. ይመለከታልም በገሀነም መካከልም ጓደኛውን ያየዋል::
Tafsyrai arabų kalba:
قَالَ تَٱللَّهِ إِن كِدتَّ لَتُرۡدِينِ
56. ይላል «በአላህ እምላለሁ በእርግጥ ልታጠፋኝ ቀርበህ ነበር።
Tafsyrai arabų kalba:
وَلَوۡلَا نِعۡمَةُ رَبِّي لَكُنتُ مِنَ ٱلۡمُحۡضَرِينَ
57. «የጌታየም ጸጋ ባልነበረ ኖሮ ወደ እሳት ከሚቀርቡት እሆን ነበር።» (ይላል)
Tafsyrai arabų kalba:
أَفَمَا نَحۡنُ بِمَيِّتِينَ
58. (የገነት ሰዎች ይላሉ)፡ «እኛ የምንሞት ሰዎች አይደለንምን?»
Tafsyrai arabų kalba:
إِلَّا مَوۡتَتَنَا ٱلۡأُولَىٰ وَمَا نَحۡنُ بِمُعَذَّبِينَ
59. «የመጀመሪያይቱ መሞታችን ብቻ ስትቀር እኛም የምንቀጣ አይደለንም» ይላሉ።
Tafsyrai arabų kalba:
إِنَّ هَٰذَا لَهُوَ ٱلۡفَوۡزُ ٱلۡعَظِيمُ
60.ይህ ለገነት ሰዎች የተወሳው እርሱ በእርግጥ ታላቅ እድል ነው::
Tafsyrai arabų kalba:
لِمِثۡلِ هَٰذَا فَلۡيَعۡمَلِ ٱلۡعَٰمِلُونَ
61. ለዚህ ብጤ ሰሪዎች ሁሉ ይስሩ::
Tafsyrai arabų kalba:
أَذَٰلِكَ خَيۡرٞ نُّزُلًا أَمۡ شَجَرَةُ ٱلزَّقُّومِ
62. በመስተንግዶነት ይህ ይበልጣልን? ወይስ የዘቁም ዛፍ?
Tafsyrai arabų kalba:
إِنَّا جَعَلۡنَٰهَا فِتۡنَةٗ لِّلظَّٰلِمِينَ
63. እኛ ለበዳዮች ፈተና አድርገናታል።
Tafsyrai arabų kalba:
إِنَّهَا شَجَرَةٞ تَخۡرُجُ فِيٓ أَصۡلِ ٱلۡجَحِيمِ
64. እርሷ ከገሀነም አዘቅት ውስጥ የምትወጣ ዛፍ ናት፤
Tafsyrai arabų kalba:
طَلۡعُهَا كَأَنَّهُۥ رُءُوسُ ٱلشَّيَٰطِينِ
65. እንቡጧ ልክ የሰይጣናት ራሶች ይመስላል::
Tafsyrai arabų kalba:
فَإِنَّهُمۡ لَأٓكِلُونَ مِنۡهَا فَمَالِـُٔونَ مِنۡهَا ٱلۡبُطُونَ
66. እነርሱ ከእርሷ በይዎች ናቸው:: ሆዶችንም ከእርሷ ሞይዎች ናቸው::
Tafsyrai arabų kalba:
ثُمَّ إِنَّ لَهُمۡ عَلَيۡهَا لَشَوۡبٗا مِّنۡ حَمِيمٖ
67. ከዚያ ለእነርሱ በእርሷ ላይ ከተኳሳ ውሃ ቅልቅልን መጠጥ አላቸው።
Tafsyrai arabų kalba:
ثُمَّ إِنَّ مَرۡجِعَهُمۡ لَإِلَى ٱلۡجَحِيمِ
68. ከዚያም መመለሻቸው ወደ ተጋጋመች እሳት ነው::
Tafsyrai arabų kalba:
إِنَّهُمۡ أَلۡفَوۡاْ ءَابَآءَهُمۡ ضَآلِّينَ
69. እነርሱ አባቶቻቸውን የተሳሳቱ ሆነው አግኝተዋል።
Tafsyrai arabų kalba:
فَهُمۡ عَلَىٰٓ ءَاثَٰرِهِمۡ يُهۡرَعُونَ
70. እነርሱም በፈለጎቻቸው ላይ ይገሰግሳሉና።
Tafsyrai arabų kalba:
وَلَقَدۡ ضَلَّ قَبۡلَهُمۡ أَكۡثَرُ ٱلۡأَوَّلِينَ
71. ከእነርሱም በፊት የነበሩት የቀድሞዎቹ ህዝቦች አብዛሀኞቻቸው በእርግጥ ተሳስተዋል::
Tafsyrai arabų kalba:
وَلَقَدۡ أَرۡسَلۡنَا فِيهِم مُّنذِرِينَ
72. በውስጣቸዉም አስፈራሪዎችን በእርግጥ ልከናል::
Tafsyrai arabų kalba:
فَٱنظُرۡ كَيۡفَ كَانَ عَٰقِبَةُ ٱلۡمُنذَرِينَ
73. (መልዕክተኛችን ሙሐመድ ሆይ!) የተስፈራሪዎቹም መጨረሻ እንዴት እንደነበረ ተመልከት!
Tafsyrai arabų kalba:
إِلَّا عِبَادَ ٱللَّهِ ٱلۡمُخۡلَصِينَ
74. ምርጥ የሆኑት የአላህ ባሮች ብቻ ሲቀሩ::
Tafsyrai arabų kalba:
وَلَقَدۡ نَادَىٰنَا نُوحٞ فَلَنِعۡمَ ٱلۡمُجِيبُونَ
75. ኑህም በእርግጥ ጠራን:: ምንኛ ያማርን ምላሽ ሰጪ ነን?
Tafsyrai arabų kalba:
وَنَجَّيۡنَٰهُ وَأَهۡلَهُۥ مِنَ ٱلۡكَرۡبِ ٱلۡعَظِيمِ
76. እርሱንም ቤተሰቦቹንም ከከባድ ጭንቅ አዳንን::
Tafsyrai arabų kalba:
 
Reikšmių vertimas Sūra: As-Saffat
Sūrų turinys Puslapio numeris
 
Kilniojo Korano reikšmių vertimas - Vertimas į amharų k. - Afrikos akademija - Vertimų turinys

Išvertė Muchamed Zain Zahr Ad-Din. Išleido Afrikos akademija.

Uždaryti