Check out the new design

Kilniojo Korano reikšmių vertimas - Vertimas į amharų k. - Afrikos akademija * - Vertimų turinys

PDF XML CSV Excel API
Please review the Terms and Policies

Reikšmių vertimas Sūra: Al-Ma’idah’   Aja (Korano eilutė):
إِنَّمَا يُرِيدُ ٱلشَّيۡطَٰنُ أَن يُوقِعَ بَيۡنَكُمُ ٱلۡعَدَٰوَةَ وَٱلۡبَغۡضَآءَ فِي ٱلۡخَمۡرِ وَٱلۡمَيۡسِرِ وَيَصُدَّكُمۡ عَن ذِكۡرِ ٱللَّهِ وَعَنِ ٱلصَّلَوٰةِۖ فَهَلۡ أَنتُم مُّنتَهُونَ
91. ሰይጣን የሚፈልገው በሚያሰክር መጠጥና በቁማር አማካኝነት በመካከላችሁ ጠብንና ጥላቻን ሊጭርና አላህን ከማውሳትና ከስግደት ሊያግዳችሁ ብቻ ነው:: ታዲያ እናንተ ከእነዚህ ነገሮች ተከልካዩች ናችሁን?
Tafsyrai arabų kalba:
وَأَطِيعُواْ ٱللَّهَ وَأَطِيعُواْ ٱلرَّسُولَ وَٱحۡذَرُواْۚ فَإِن تَوَلَّيۡتُمۡ فَٱعۡلَمُوٓاْ أَنَّمَا عَلَىٰ رَسُولِنَا ٱلۡبَلَٰغُ ٱلۡمُبِينُ
92. (ሙስሊሞች ሆይ!) አላህን ብቻ ታዘዙ:: መልዕክተኛውንም ታዘዙ:: ተጠንቀቁ:: ብትሸሹም በመልዕክተኛችን ላይ ያለበት በግልጽ መልዕክቱን ማድረስ ብቻ መሆኑን እወቁ::
Tafsyrai arabų kalba:
لَيۡسَ عَلَى ٱلَّذِينَ ءَامَنُواْ وَعَمِلُواْ ٱلصَّٰلِحَٰتِ جُنَاحٞ فِيمَا طَعِمُوٓاْ إِذَا مَا ٱتَّقَواْ وَّءَامَنُواْ وَعَمِلُواْ ٱلصَّٰلِحَٰتِ ثُمَّ ٱتَّقَواْ وَّءَامَنُواْ ثُمَّ ٱتَّقَواْ وَّأَحۡسَنُواْۚ وَٱللَّهُ يُحِبُّ ٱلۡمُحۡسِنِينَ
93. በእነዚያ በአላህ ባመኑትና በጎ ስራዎችን በሰሩት ላይ ከተጠነቀቁና ካመኑ መልካምን ከሰሩ፤ ከዚያም ከተጠነቀቁና ካመኑ፤ ከዚያም ከተጠነቀቁና ስራንም ካሳመሩ ከመከልከሉ በፊት በተመገቡት ነገር ኃጢአት የለባቸዉም። አላህ ስራቸውን አሳማሪዎቹን ሁሉ ይወዳልና።
Tafsyrai arabų kalba:
يَٰٓأَيُّهَا ٱلَّذِينَ ءَامَنُواْ لَيَبۡلُوَنَّكُمُ ٱللَّهُ بِشَيۡءٖ مِّنَ ٱلصَّيۡدِ تَنَالُهُۥٓ أَيۡدِيكُمۡ وَرِمَاحُكُمۡ لِيَعۡلَمَ ٱللَّهُ مَن يَخَافُهُۥ بِٱلۡغَيۡبِۚ فَمَنِ ٱعۡتَدَىٰ بَعۡدَ ذَٰلِكَ فَلَهُۥ عَذَابٌ أَلِيمٞ
94. እናንተ ያመናችሁ ሆይ! አላህ በሐጅ ጊዜ እጆቻችሁና ጦሮቻችሁ (በሚያገኙት) በሚያድኑት ታዳኝ አውሬ አላህን በሩቁ ሆኖ የሚፈራውን ሰው ሊገልጽ ይሞክራችኋል:: ከዚያ በኋላ ወሰንን ያለፈና ያደነ ሰው ሁሉ አሳማሚ ቅጣት አለበት::
Tafsyrai arabų kalba:
يَٰٓأَيُّهَا ٱلَّذِينَ ءَامَنُواْ لَا تَقۡتُلُواْ ٱلصَّيۡدَ وَأَنتُمۡ حُرُمٞۚ وَمَن قَتَلَهُۥ مِنكُم مُّتَعَمِّدٗا فَجَزَآءٞ مِّثۡلُ مَا قَتَلَ مِنَ ٱلنَّعَمِ يَحۡكُمُ بِهِۦ ذَوَا عَدۡلٖ مِّنكُمۡ هَدۡيَۢا بَٰلِغَ ٱلۡكَعۡبَةِ أَوۡ كَفَّٰرَةٞ طَعَامُ مَسَٰكِينَ أَوۡ عَدۡلُ ذَٰلِكَ صِيَامٗا لِّيَذُوقَ وَبَالَ أَمۡرِهِۦۗ عَفَا ٱللَّهُ عَمَّا سَلَفَۚ وَمَنۡ عَادَ فَيَنتَقِمُ ٱللَّهُ مِنۡهُۚ وَٱللَّهُ عَزِيزٞ ذُو ٱنتِقَامٍ
95. እናንተ ያመናችሁ ሆይ! እናንተ በሐጅ ስራ ውስጥ ስትሆኑ አውሬን አትግደሉ:: ከናንተም እያወቀ አውሬን የገደለ ሰው ቅጣቱ ከናንተ መካከል ሁለት የፍትሀዊነት ባለቤቶች የሚፈርዱበትና ወደ ካዕባ ደራሽ መስዋዕት ሲሆን ከቤት እንሰሳዎች የገደለውን ነገር ብጤ መስጠት ወይም ሚስኪኖችን ማብላት ወይም የዚህን ልክ መፆም ማሰረዣው ነው:: ይህም የስራውን ከባድ ቅጣት እንዲቀምስ ነው:: ሳይከለከል በፊት ላለፈው ነገር አላህ ይቅርታ አደረገ:: ወደ ጥፋቱ የተመለሰን ሁሉ አላህ ይበቀለዋል:: አላህ አሸናፊና የብቀላ ባለቤት ነው::
Tafsyrai arabų kalba:
 
Reikšmių vertimas Sūra: Al-Ma’idah’
Sūrų turinys Puslapio numeris
 
Kilniojo Korano reikšmių vertimas - Vertimas į amharų k. - Afrikos akademija - Vertimų turinys

Išvertė Muchamed Zain Zahr Ad-Din. Išleido Afrikos akademija.

Uždaryti