Check out the new design

വിശുദ്ധ ഖുർആൻ പരിഭാഷ - അംഹാരിക് പരിഭാഷ - ആഫ്രിക്ക അക്കാദമി * - വിവർത്തനങ്ങളുടെ സൂചിക


പരിഭാഷ അദ്ധ്യായം: യൂനുസ്   ആയത്ത്:
۞ لِّلَّذِينَ أَحۡسَنُواْ ٱلۡحُسۡنَىٰ وَزِيَادَةٞۖ وَلَا يَرۡهَقُ وُجُوهَهُمۡ قَتَرٞ وَلَا ذِلَّةٌۚ أُوْلَٰٓئِكَ أَصۡحَٰبُ ٱلۡجَنَّةِۖ هُمۡ فِيهَا خَٰلِدُونَ
26. ለእነዚያ መልካም ለሠሩት ሰዎች መልካም ነገርና (ገነት) ሌላ ተጨማሪም አላቸው:: ፊቶቻቸውንም ጥቁረትና ውርደት አይሸፍናቸዉም:: እነዚያ የገነት ሰዎች ናቸው:: እነርሱ በውስጧ ዘውታሪዎች ናቸው::
അറബി ഖുർആൻ വിവരണങ്ങൾ:
وَٱلَّذِينَ كَسَبُواْ ٱلسَّيِّـَٔاتِ جَزَآءُ سَيِّئَةِۭ بِمِثۡلِهَا وَتَرۡهَقُهُمۡ ذِلَّةٞۖ مَّا لَهُم مِّنَ ٱللَّهِ مِنۡ عَاصِمٖۖ كَأَنَّمَآ أُغۡشِيَتۡ وُجُوهُهُمۡ قِطَعٗا مِّنَ ٱلَّيۡلِ مُظۡلِمًاۚ أُوْلَٰٓئِكَ أَصۡحَٰبُ ٱلنَّارِۖ هُمۡ فِيهَا خَٰلِدُونَ
27. እነዚያ ኃጢአቶችን የሠሩት ደግሞ ኃጢአቲቱን የሚመጥን ቅጣት አለባቸው:: ውርደትም ትሸፍናቸዋለች :: እነርሱ ከአላህ ቅጣት ጠባቂ የላቸዉም:: ፊቶቻቸው በድቅድቅ ጨለማ ቁራጮች እንደ ተሸፈኑ ይሆናሉ:: እነዚያ የእሳት ሰዎች ናቸው:: እነርሱ በውስጧ ዘለዓለም ነዋሪዎች ናቸው::
അറബി ഖുർആൻ വിവരണങ്ങൾ:
وَيَوۡمَ نَحۡشُرُهُمۡ جَمِيعٗا ثُمَّ نَقُولُ لِلَّذِينَ أَشۡرَكُواْ مَكَانَكُمۡ أَنتُمۡ وَشُرَكَآؤُكُمۡۚ فَزَيَّلۡنَا بَيۡنَهُمۡۖ وَقَالَ شُرَكَآؤُهُم مَّا كُنتُمۡ إِيَّانَا تَعۡبُدُونَ
28. (መልዕክተኛችን ሙሐመድ ሆይ!) አማልክትንና አምላኪዎቻቸውን ሁሉ በአንድ የምንሰበስባቸውንና ከዚያም ለእነዚያ ላጋሩት «እናንተም ተጋሪዎቻችሁም ቦታችሁን ያዙ።» የምንልበትን ተጋሪዎቻቸዉም (እንዲህ) የሚሏቸው ሲሆኑ በመካከላቸው የምንለይበትን ቀን አስታውስ «ትገዙ የነበረው እኛን አልነበረም።
അറബി ഖുർആൻ വിവരണങ്ങൾ:
فَكَفَىٰ بِٱللَّهِ شَهِيدَۢا بَيۡنَنَا وَبَيۡنَكُمۡ إِن كُنَّا عَنۡ عِبَادَتِكُمۡ لَغَٰفِلِينَ
29. (ጣኦታቶቹ) «እኛን ለመገዛታችሁ ዘንጊዎች ለመሆናችን በኛና በእናንተ መካከል የአላህ መስካሪነት በቃ።» ይሏቸዋል::
അറബി ഖുർആൻ വിവരണങ്ങൾ:
هُنَالِكَ تَبۡلُواْ كُلُّ نَفۡسٖ مَّآ أَسۡلَفَتۡۚ وَرُدُّوٓاْ إِلَى ٱللَّهِ مَوۡلَىٰهُمُ ٱلۡحَقِّۖ وَضَلَّ عَنۡهُم مَّا كَانُواْ يَفۡتَرُونَ
30. በዚያ ቀን ነፍስ ሁሉ ያሳለፈችውን ሥራ ታውቃለች:: አጋሪዎች ወደ አላህ እውነተኛ ወደሆነው ጌታቸው ይመለሳሉ:: ያ በአላህ ላይ ይቀጣጥፋት የነበሩት ሁሉ ነገርም ይጠፋባቸዋል::
അറബി ഖുർആൻ വിവരണങ്ങൾ:
قُلۡ مَن يَرۡزُقُكُم مِّنَ ٱلسَّمَآءِ وَٱلۡأَرۡضِ أَمَّن يَمۡلِكُ ٱلسَّمۡعَ وَٱلۡأَبۡصَٰرَ وَمَن يُخۡرِجُ ٱلۡحَيَّ مِنَ ٱلۡمَيِّتِ وَيُخۡرِجُ ٱلۡمَيِّتَ مِنَ ٱلۡحَيِّ وَمَن يُدَبِّرُ ٱلۡأَمۡرَۚ فَسَيَقُولُونَ ٱللَّهُۚ فَقُلۡ أَفَلَا تَتَّقُونَ
31. (መልዕክተኛችን ሙሐመድ ሆይ!) «ከሰማይና ከምድር ሲሳይን የሚሰጣችሁ ማን ነው? መስሚያዎችንና ማያዎችንስ የፈጠረላችሁ ማን ነው? ከሙትም ህያውን የሚያወጣ፤ ከህያዉም ሙትን የሚያወጣስ ማን ነው? ነገሩን ሁሉ የሚያስተናብርስ ማን ነው?» በላቸው:: «በእርግጥ አላህ ነው።» ይሉሃል:: «ታዲያ ለምን ታጋራላችሁ? ታዲያ አትፈሩትምን?» በላቸው።
അറബി ഖുർആൻ വിവരണങ്ങൾ:
فَذَٰلِكُمُ ٱللَّهُ رَبُّكُمُ ٱلۡحَقُّۖ فَمَاذَا بَعۡدَ ٱلۡحَقِّ إِلَّا ٱلضَّلَٰلُۖ فَأَنَّىٰ تُصۡرَفُونَ
32. እውነተኛው ጌታችሁ አላህ ብቻ ነው:: ከእውነት በኋላ ጥመት እንጂ ሌላ ምን አለ? ከእውነት እንዴት ትዞራላችሁ?
അറബി ഖുർആൻ വിവരണങ്ങൾ:
كَذَٰلِكَ حَقَّتۡ كَلِمَتُ رَبِّكَ عَلَى ٱلَّذِينَ فَسَقُوٓاْ أَنَّهُمۡ لَا يُؤۡمِنُونَ
33. ልክ እንደዚሁ የጌታህ ቃል በእነዚያ ባመጹት ሰዎች ላይ ፈጽሞ የማያምኑ መሆናቸው ተረጋገጠ::
അറബി ഖുർആൻ വിവരണങ്ങൾ:
 
പരിഭാഷ അദ്ധ്യായം: യൂനുസ്
സൂറത്തുകളുടെ സൂചിക പേജ് നമ്പർ
 
വിശുദ്ധ ഖുർആൻ പരിഭാഷ - അംഹാരിക് പരിഭാഷ - ആഫ്രിക്ക അക്കാദമി - വിവർത്തനങ്ങളുടെ സൂചിക

മൊഴിമാറ്റം മുഹമ്മദ് സെയിൻ സഹ്റുദ്ദീൻ. ആഫ്രിക്ക അക്കാദമി പ്രസിദ്ധീകരണം.

അടക്കുക