Check out the new design

വിശുദ്ധ ഖുർആൻ പരിഭാഷ - അംഹാരിക് പരിഭാഷ - ആഫ്രിക്ക അക്കാദമി * - വിവർത്തനങ്ങളുടെ സൂചിക

PDF XML CSV Excel API
Please review the Terms and Policies

പരിഭാഷ അദ്ധ്യായം: ബഖറഃ   ആയത്ത്:
وَإِذَا قِيلَ لَهُمُ ٱتَّبِعُواْ مَآ أَنزَلَ ٱللَّهُ قَالُواْ بَلۡ نَتَّبِعُ مَآ أَلۡفَيۡنَا عَلَيۡهِ ءَابَآءَنَآۚ أَوَلَوۡ كَانَ ءَابَآؤُهُمۡ لَا يَعۡقِلُونَ شَيۡـٔٗا وَلَا يَهۡتَدُونَ
170. ለእነርሱም «አላህ ያወረደውን ተከተሉ በተባሉ ጊዜ የለም አባቶቻችንን በእርሱ ላይ ያገኘንበትን ነገር ብቻ እንከተላለን» ይላሉ:: አባቶቻቸው ምንም የማያውቁና ወደ እውነት የማይመሩም ቢሆኑ ይከተሏቸዋልን?
അറബി ഖുർആൻ വിവരണങ്ങൾ:
وَمَثَلُ ٱلَّذِينَ كَفَرُواْ كَمَثَلِ ٱلَّذِي يَنۡعِقُ بِمَا لَا يَسۡمَعُ إِلَّا دُعَآءٗ وَنِدَآءٗۚ صُمُّۢ بُكۡمٌ عُمۡيٞ فَهُمۡ لَا يَعۡقِلُونَ
171. የእነዚያም በአላህ የካዱት ምሳሌ ልክ እንደዚያ ድምጽንና ጥሪን እንጂ ሌላን በማይሰማ እንሰሳ ላይ እንደሚጮህ (እረኛ) ብጤ ነው:: እነርሱ (እውነትን የማይሰሙ) ደንቆሮዎች፤ (ሐቅን የማይናገሩ) ዲዳዎች፤ (ትክክለኛውን መንገድ የማያዩ) እውሮች ናቸው:: ምንንም ነገር የሚገነዘቡ አይደሉም::
അറബി ഖുർആൻ വിവരണങ്ങൾ:
يَٰٓأَيُّهَا ٱلَّذِينَ ءَامَنُواْ كُلُواْ مِن طَيِّبَٰتِ مَا رَزَقۡنَٰكُمۡ وَٱشۡكُرُواْ لِلَّهِ إِن كُنتُمۡ إِيَّاهُ تَعۡبُدُونَ
172. እናንተ ያመናችሁ ሆይ! ከሰጠናችሁ ሲሳዮች መካከል ጥሩውን ተመገቡ:: አላህንም በብቸኝነት የምታመልኩት ከሆናችሁ እሱኑ ብቻ አመስግኑት::
അറബി ഖുർആൻ വിവരണങ്ങൾ:
إِنَّمَا حَرَّمَ عَلَيۡكُمُ ٱلۡمَيۡتَةَ وَٱلدَّمَ وَلَحۡمَ ٱلۡخِنزِيرِ وَمَآ أُهِلَّ بِهِۦ لِغَيۡرِ ٱللَّهِۖ فَمَنِ ٱضۡطُرَّ غَيۡرَ بَاغٖ وَلَا عَادٖ فَلَآ إِثۡمَ عَلَيۡهِۚ إِنَّ ٱللَّهَ غَفُورٞ رَّحِيمٌ
173. (አላህ) በእናንተ ላይ እርም ያደረገባችሁ በክትን፣ ደምን፣ የአሳማ ስጋንና ከአላህ ሌላ በሆነ ስም የታረደን ስጋ ብቻ ነው:: ተገዶ ችግሩን ለማስወገድ ያክል ብቻ ሽፍታና ወሰን አላፊ ሳይሆን (ቢመገብ) በእርሱ ላይ ምንም ሀጢአት የለበትም:: አላህ መሐሪና አዛኝ ነውና::
അറബി ഖുർആൻ വിവരണങ്ങൾ:
إِنَّ ٱلَّذِينَ يَكۡتُمُونَ مَآ أَنزَلَ ٱللَّهُ مِنَ ٱلۡكِتَٰبِ وَيَشۡتَرُونَ بِهِۦ ثَمَنٗا قَلِيلًا أُوْلَٰٓئِكَ مَا يَأۡكُلُونَ فِي بُطُونِهِمۡ إِلَّا ٱلنَّارَ وَلَا يُكَلِّمُهُمُ ٱللَّهُ يَوۡمَ ٱلۡقِيَٰمَةِ وَلَا يُزَكِّيهِمۡ وَلَهُمۡ عَذَابٌ أَلِيمٌ
174. እነዚያ አላህ ካወረደው መጽሐፍ (የትኛውንም ክፍል) የሚደብቁ፤ በሱ (በደበቁትም) ጥቂትን ዋጋ የሚለውጡ፤ በሆዶቻቸው ውስጥ እሳትን እንጂ አይበሉም:: አላህም በትንሳኤ ቀን አያናግራቸዉም:: ከኃጢአትም አያጠራቸዉምም:: ለእነርሱም አሳማሚ ቅጣት አለባቸው::
അറബി ഖുർആൻ വിവരണങ്ങൾ:
أُوْلَٰٓئِكَ ٱلَّذِينَ ٱشۡتَرَوُاْ ٱلضَّلَٰلَةَ بِٱلۡهُدَىٰ وَٱلۡعَذَابَ بِٱلۡمَغۡفِرَةِۚ فَمَآ أَصۡبَرَهُمۡ عَلَى ٱلنَّارِ
175. እነዚህ እነዚያ ስህተትን በቅንነት ቅጣትንም በምህረት የለወጡ ናቸው:: በእሳት ላይ ምን ታጋሽ አደረጋቸው?!
അറബി ഖുർആൻ വിവരണങ്ങൾ:
ذَٰلِكَ بِأَنَّ ٱللَّهَ نَزَّلَ ٱلۡكِتَٰبَ بِٱلۡحَقِّۗ وَإِنَّ ٱلَّذِينَ ٱخۡتَلَفُواْ فِي ٱلۡكِتَٰبِ لَفِي شِقَاقِۭ بَعِيدٖ
176. ይህም አላህ መጽሐፍን በእውነት ያወረደ በመሆኑና (በእርሱም በመካዳቸው ነው):: እነዚያም በመጽሐፉ የተለያዩት ከእውነት በራቀ ውዝግብ ውስጥ ናቸው::
അറബി ഖുർആൻ വിവരണങ്ങൾ:
 
പരിഭാഷ അദ്ധ്യായം: ബഖറഃ
സൂറത്തുകളുടെ സൂചിക പേജ് നമ്പർ
 
വിശുദ്ധ ഖുർആൻ പരിഭാഷ - അംഹാരിക് പരിഭാഷ - ആഫ്രിക്ക അക്കാദമി - വിവർത്തനങ്ങളുടെ സൂചിക

മൊഴിമാറ്റം മുഹമ്മദ് സെയിൻ സഹ്റുദ്ദീൻ. ആഫ്രിക്ക അക്കാദമി പ്രസിദ്ധീകരണം.

അടക്കുക