Check out the new design

വിശുദ്ധ ഖുർആൻ പരിഭാഷ - അംഹാരിക് പരിഭാഷ - ആഫ്രിക്ക അക്കാദമി * - വിവർത്തനങ്ങളുടെ സൂചിക


പരിഭാഷ അദ്ധ്യായം: ന്നൂർ   ആയത്ത്:
إِنَّ ٱلَّذِينَ جَآءُو بِٱلۡإِفۡكِ عُصۡبَةٞ مِّنكُمۡۚ لَا تَحۡسَبُوهُ شَرّٗا لَّكُمۖ بَلۡ هُوَ خَيۡرٞ لَّكُمۡۚ لِكُلِّ ٱمۡرِيٕٖ مِّنۡهُم مَّا ٱكۡتَسَبَ مِنَ ٱلۡإِثۡمِۚ وَٱلَّذِي تَوَلَّىٰ كِبۡرَهُۥ مِنۡهُمۡ لَهُۥ عَذَابٌ عَظِيمٞ
11. እነዚያ መጥፎን ውሸት ያመጡ ከናንተው የሆኑ ቡድኖች ናቸው:: ለእናንተ ክፉ ነገር እንደሆነ አታስቡት፤ በእውነቱ እርሱ ለእናንተ መልካም ነገር ነው:: ከጭፍሮቹ ለእያንዳንዱ ሰው ከኃጢአት የሠራው ሥራ ዋጋ አለው:: ያም ከእነርሱ ትልቁን ኃጢአት የተሸከመው ለእርሱ ከባድ ቅጣት አለው::
അറബി ഖുർആൻ വിവരണങ്ങൾ:
لَّوۡلَآ إِذۡ سَمِعۡتُمُوهُ ظَنَّ ٱلۡمُؤۡمِنُونَ وَٱلۡمُؤۡمِنَٰتُ بِأَنفُسِهِمۡ خَيۡرٗا وَقَالُواْ هَٰذَآ إِفۡكٞ مُّبِينٞ
12. (ውሸቱን) በሰማችሁት ጊዜ አማኞችና ምዕመናት በነፍሶቻቸው ለምን ደግን ነገር አልጠረጠሩም? ለምንስ «ይህ ግልጽ ቅጥፈት ነው።» አላሉም?
അറബി ഖുർആൻ വിവരണങ്ങൾ:
لَّوۡلَا جَآءُو عَلَيۡهِ بِأَرۡبَعَةِ شُهَدَآءَۚ فَإِذۡ لَمۡ يَأۡتُواْ بِٱلشُّهَدَآءِ فَأُوْلَٰٓئِكَ عِندَ ٱللَّهِ هُمُ ٱلۡكَٰذِبُونَ
13. በእርሱ ላይ ለምን አራትን ምስክሮች አላመጡም? ምስክሮቹንም ካላመጡ እነዚያ አላህ ዘንድ ውሸታሞቹ እነርሱ ብቻ ናቸው::
അറബി ഖുർആൻ വിവരണങ്ങൾ:
وَلَوۡلَا فَضۡلُ ٱللَّهِ عَلَيۡكُمۡ وَرَحۡمَتُهُۥ فِي ٱلدُّنۡيَا وَٱلۡأٓخِرَةِ لَمَسَّكُمۡ فِي مَآ أَفَضۡتُمۡ فِيهِ عَذَابٌ عَظِيمٌ
14. በቅርቢቱም ሆነ በመጨረሻይቱ ዓለም በእናንተ ላይ የአላህ ችሮታና እዝነቱ ባልነበረ ኖሮ በውስጡ በገባችሁበት ወሬ ምክንያት ታላቅ ቅጣት በእርግጥ በደረሰባችሁ ነበር::
അറബി ഖുർആൻ വിവരണങ്ങൾ:
إِذۡ تَلَقَّوۡنَهُۥ بِأَلۡسِنَتِكُمۡ وَتَقُولُونَ بِأَفۡوَاهِكُم مَّا لَيۡسَ لَكُم بِهِۦ عِلۡمٞ وَتَحۡسَبُونَهُۥ هَيِّنٗا وَهُوَ عِندَ ٱللَّهِ عَظِيمٞ
15. በምላሶቻችሁም በምትቀባበሉት ጊዜ ለእናንተም በእርሱ እውቀት በሌላችሁ ነገር በአፎቻችሁ በተናገራችሁና አላህ ዘንድ ከባድ ኃጢአት ሆኖ ሳለ ቀላል አድርጋችሁ ባሰባችሁት ጊዜ ከባድ ቅጣት በነካችሁ ነበር::
അറബി ഖുർആൻ വിവരണങ്ങൾ:
وَلَوۡلَآ إِذۡ سَمِعۡتُمُوهُ قُلۡتُم مَّا يَكُونُ لَنَآ أَن نَّتَكَلَّمَ بِهَٰذَا سُبۡحَٰنَكَ هَٰذَا بُهۡتَٰنٌ عَظِيمٞ
16. በሰማችሁትም ጊዜ: «በዚህ ጉዳይ ልንናገር ለእኛ አይገባንም:: አላህ ጥራት ይገባህ:: ይህ ከባድ ቅጥፈት ነው።» አትሉም ነበርን?
അറബി ഖുർആൻ വിവരണങ്ങൾ:
يَعِظُكُمُ ٱللَّهُ أَن تَعُودُواْ لِمِثۡلِهِۦٓ أَبَدًا إِن كُنتُم مُّؤۡمِنِينَ
17. አማኞች እንደሆናችሁ ወደ ዚህ መሰል ተግባር ብጤው በፍጹም እንዳትመለሱ አላህ ይገስጻችኋል::
അറബി ഖുർആൻ വിവരണങ്ങൾ:
وَيُبَيِّنُ ٱللَّهُ لَكُمُ ٱلۡأٓيَٰتِۚ وَٱللَّهُ عَلِيمٌ حَكِيمٌ
18. ለእናንተም አላህ አናቅጽን ይገልጽላችኋል:: አላህ ሁሉን አዋቂና ጥበበኛ ነው::
അറബി ഖുർആൻ വിവരണങ്ങൾ:
إِنَّ ٱلَّذِينَ يُحِبُّونَ أَن تَشِيعَ ٱلۡفَٰحِشَةُ فِي ٱلَّذِينَ ءَامَنُواْ لَهُمۡ عَذَابٌ أَلِيمٞ فِي ٱلدُّنۡيَا وَٱلۡأٓخِرَةِۚ وَٱللَّهُ يَعۡلَمُ وَأَنتُمۡ لَا تَعۡلَمُونَ
19. እነዚያ በነዚያ በትክክል በአላህ ባመኑት ሰዎች መካከል መጥፎ ወሬ እንድትስፋፋ የሚወዱ ለእነርሱ በቅርቢቱም ሆነ በመጨረሻይቱ ዓለም አሳማሚ ቅጣት አላቸው:: አላህ ሁሉን ነገር ያውቃል እናንተ ግን አታውቁም::
അറബി ഖുർആൻ വിവരണങ്ങൾ:
وَلَوۡلَا فَضۡلُ ٱللَّهِ عَلَيۡكُمۡ وَرَحۡمَتُهُۥ وَأَنَّ ٱللَّهَ رَءُوفٞ رَّحِيمٞ
20. በእናንተም ላይ የአላህ ችሮታውና እዝነቱ ባልነበረ አላህም ሩህሩህና አዛኝ ባልሆነ ኖሮ (ቶሎ ባጠፋችሁ ነበር)::
അറബി ഖുർആൻ വിവരണങ്ങൾ:
 
പരിഭാഷ അദ്ധ്യായം: ന്നൂർ
സൂറത്തുകളുടെ സൂചിക പേജ് നമ്പർ
 
വിശുദ്ധ ഖുർആൻ പരിഭാഷ - അംഹാരിക് പരിഭാഷ - ആഫ്രിക്ക അക്കാദമി - വിവർത്തനങ്ങളുടെ സൂചിക

മൊഴിമാറ്റം മുഹമ്മദ് സെയിൻ സഹ്റുദ്ദീൻ. ആഫ്രിക്ക അക്കാദമി പ്രസിദ്ധീകരണം.

അടക്കുക