Check out the new design

വിശുദ്ധ ഖുർആൻ പരിഭാഷ - അംഹാരിക് പരിഭാഷ - ആഫ്രിക്ക അക്കാദമി * - വിവർത്തനങ്ങളുടെ സൂചിക


പരിഭാഷ അദ്ധ്യായം: ഹുജുറാത്ത്   ആയത്ത്:
يَٰٓأَيُّهَا ٱلَّذِينَ ءَامَنُواْ ٱجۡتَنِبُواْ كَثِيرٗا مِّنَ ٱلظَّنِّ إِنَّ بَعۡضَ ٱلظَّنِّ إِثۡمٞۖ وَلَا تَجَسَّسُواْ وَلَا يَغۡتَب بَّعۡضُكُم بَعۡضًاۚ أَيُحِبُّ أَحَدُكُمۡ أَن يَأۡكُلَ لَحۡمَ أَخِيهِ مَيۡتٗا فَكَرِهۡتُمُوهُۚ وَٱتَّقُواْ ٱللَّهَۚ إِنَّ ٱللَّهَ تَوَّابٞ رَّحِيمٞ
12. እናንተ ያመናችሁ ሆይ! ከጥርጣሬ ብዙን ራቁ:: ከጥርጣሬ ከፊሉ ኃጢአት ነውና:: ነውርንም አትከታተሉ። ከፊላችሁም ከፊሉን አይማው። አንደኛችሁ የወንድሙን ስጋ የሞተ ሆኖ ሊበላ ይወዳልን? (መብላቱን) ጠላችሁት (ሀሜቱንም ጥሉት):: አላህንም ፍሩ:: አላህ ጸጸትን ተቀባይና አዛኝ ነውና::
അറബി ഖുർആൻ വിവരണങ്ങൾ:
يَٰٓأَيُّهَا ٱلنَّاسُ إِنَّا خَلَقۡنَٰكُم مِّن ذَكَرٖ وَأُنثَىٰ وَجَعَلۡنَٰكُمۡ شُعُوبٗا وَقَبَآئِلَ لِتَعَارَفُوٓاْۚ إِنَّ أَكۡرَمَكُمۡ عِندَ ٱللَّهِ أَتۡقَىٰكُمۡۚ إِنَّ ٱللَّهَ عَلِيمٌ خَبِيرٞ
13. እናንተ ሰዎች ሆይ! እኛ ከወንድና ከሴት ፈጠርናችሁ:: እንድትተዋወቁም ጎሳዎችና ነገዶች አደረግናችሁ:: አላህ ዘንድ በላጫችሁ በጣም አላህን ፈሪያችሁ ብቻ ነው:: አላህ ግልጽን አዋቂ ውስጥንም አዋቂ ነው::
അറബി ഖുർആൻ വിവരണങ്ങൾ:
۞ قَالَتِ ٱلۡأَعۡرَابُ ءَامَنَّاۖ قُل لَّمۡ تُؤۡمِنُواْ وَلَٰكِن قُولُوٓاْ أَسۡلَمۡنَا وَلَمَّا يَدۡخُلِ ٱلۡإِيمَٰنُ فِي قُلُوبِكُمۡۖ وَإِن تُطِيعُواْ ٱللَّهَ وَرَسُولَهُۥ لَا يَلِتۡكُم مِّنۡ أَعۡمَٰلِكُمۡ شَيۡـًٔاۚ إِنَّ ٱللَّهَ غَفُورٞ رَّحِيمٌ
14. (መልዕክተኛችን ሙሐመድ ሆይ!) የዐረብ ዘላኖች አምነናል አሉ:: «አላመናችሁም ግን ሰልመናል በሉ እምነቱም በልቦቻችሁ ውስጥ ገና ጠልቆ አልገባም:: አላህንና መልዕክተኛውን ብትታዘዙ ከስራዎቻችሁ ምንም አይጎድልባችሁም:: አላህ መሀሪና አዛኝ ነውና» በላቸው::
അറബി ഖുർആൻ വിവരണങ്ങൾ:
إِنَّمَا ٱلۡمُؤۡمِنُونَ ٱلَّذِينَ ءَامَنُواْ بِٱللَّهِ وَرَسُولِهِۦ ثُمَّ لَمۡ يَرۡتَابُواْ وَجَٰهَدُواْ بِأَمۡوَٰلِهِمۡ وَأَنفُسِهِمۡ فِي سَبِيلِ ٱللَّهِۚ أُوْلَٰٓئِكَ هُمُ ٱلصَّٰدِقُونَ
15. አማኞች እነዚያ በአላህና በመልዕክተኛው ያመኑትና ከዚያም ያልተጠራጠሩት በገንዘቦቻቸውና በነፍሶቻቸዉም በአላህ መንገድ ላይ የታገሉት ሰዎች ብቻ ናቸው:: እነዚያ እነርሱ እውነተኞቹ ናቸው::
അറബി ഖുർആൻ വിവരണങ്ങൾ:
قُلۡ أَتُعَلِّمُونَ ٱللَّهَ بِدِينِكُمۡ وَٱللَّهُ يَعۡلَمُ مَا فِي ٱلسَّمَٰوَٰتِ وَمَا فِي ٱلۡأَرۡضِۚ وَٱللَّهُ بِكُلِّ شَيۡءٍ عَلِيمٞ
16. (መልዕክተኛችን ሙሐመድ ሆይ!) «አላህ በሰማያት ውስጥ ያለውንና በምድር ውስጥ ያለውን ሁሉ የሚያውቅ ሲሆን አላህን በሃይማኖታችሁ ታስታውቁታላችሁን?» በላቸው:: አላህም በነገሩ ሁሉ አዋቂ ነው::
അറബി ഖുർആൻ വിവരണങ്ങൾ:
يَمُنُّونَ عَلَيۡكَ أَنۡ أَسۡلَمُواْۖ قُل لَّا تَمُنُّواْ عَلَيَّ إِسۡلَٰمَكُمۖ بَلِ ٱللَّهُ يَمُنُّ عَلَيۡكُمۡ أَنۡ هَدَىٰكُمۡ لِلۡإِيمَٰنِ إِن كُنتُمۡ صَٰدِقِينَ
17. (መልዕክተኛችን ሙሐመድ ሆይ!) በመስለማቸው ባንተ ላይ ይመፃደቃሉ። «በእስልምናችሁ በእኔ ላይ አትመጻደቁ:: ይልቁንም አላህ ወደ ትክክለኛው እምነት ስለመራችሁ ፀጋውን ውሎላችኋል:: እውነተኞች ብትሆኑ (መመፃደቅ የሚገባው ለአላህ) ብቻ ነው» በላቸው።
അറബി ഖുർആൻ വിവരണങ്ങൾ:
إِنَّ ٱللَّهَ يَعۡلَمُ غَيۡبَ ٱلسَّمَٰوَٰتِ وَٱلۡأَرۡضِۚ وَٱللَّهُ بَصِيرُۢ بِمَا تَعۡمَلُونَ
18. አላህ የሰማያትንና የምድርን ሩቅ ሚስጥር ሁሉ ያውቃል:: አላህ የምትሰሩትን ሁሉ ተመልካችም ነው::
അറബി ഖുർആൻ വിവരണങ്ങൾ:
 
പരിഭാഷ അദ്ധ്യായം: ഹുജുറാത്ത്
സൂറത്തുകളുടെ സൂചിക പേജ് നമ്പർ
 
വിശുദ്ധ ഖുർആൻ പരിഭാഷ - അംഹാരിക് പരിഭാഷ - ആഫ്രിക്ക അക്കാദമി - വിവർത്തനങ്ങളുടെ സൂചിക

മൊഴിമാറ്റം മുഹമ്മദ് സെയിൻ സഹ്റുദ്ദീൻ. ആഫ്രിക്ക അക്കാദമി പ്രസിദ്ധീകരണം.

അടക്കുക