Check out the new design

വിശുദ്ധ ഖുർആൻ പരിഭാഷ - അംഹാരിക് പരിഭാഷ - ആഫ്രിക്ക അക്കാദമി * - വിവർത്തനങ്ങളുടെ സൂചിക


പരിഭാഷ അദ്ധ്യായം: അൻഫാൽ   ആയത്ത്:
إِذۡ تَسۡتَغِيثُونَ رَبَّكُمۡ فَٱسۡتَجَابَ لَكُمۡ أَنِّي مُمِدُّكُم بِأَلۡفٖ مِّنَ ٱلۡمَلَٰٓئِكَةِ مُرۡدِفِينَ
9. (ሙስሊሞች ሆይ!) ከጌታችሁ እርዳታን በፈለጋችሁ ጊዜ «እኔ በሺህ መላዕክት ተከታታዮች ሲሆኑ እረዳችኋለሁ።» ሲል ለእናንተ የተቀበላችሁን አስታውሱ።
അറബി ഖുർആൻ വിവരണങ്ങൾ:
وَمَا جَعَلَهُ ٱللَّهُ إِلَّا بُشۡرَىٰ وَلِتَطۡمَئِنَّ بِهِۦ قُلُوبُكُمۡۚ وَمَا ٱلنَّصۡرُ إِلَّا مِنۡ عِندِ ٱللَّهِۚ إِنَّ ٱللَّهَ عَزِيزٌ حَكِيمٌ
10. አላህ ይህንን እርዳታ ለብስራትና ልቦቻችሁ በእርሱ ሊረኩበት እንጂ ለሌላ አላደረገዉም:: ድልም የሚገኘው ከአላህ ዘንድ ብቻ ነው:: አላህ ሁሉን አሸናፊና ጥበበኛ ነውና::
അറബി ഖുർആൻ വിവരണങ്ങൾ:
إِذۡ يُغَشِّيكُمُ ٱلنُّعَاسَ أَمَنَةٗ مِّنۡهُ وَيُنَزِّلُ عَلَيۡكُم مِّنَ ٱلسَّمَآءِ مَآءٗ لِّيُطَهِّرَكُم بِهِۦ وَيُذۡهِبَ عَنكُمۡ رِجۡزَ ٱلشَّيۡطَٰنِ وَلِيَرۡبِطَ عَلَىٰ قُلُوبِكُمۡ وَيُثَبِّتَ بِهِ ٱلۡأَقۡدَامَ
11. (መልዕክተኛችን ሙሐመድ ሆይ! ) ከእርሱ በሆነው ጸጥታ በጦር ግንባር በእንቅልፍ በሸፈናችሁና ውሃውንም በእርሱ ሊያጠራችሁ፤ የሰይጣንንም ጉትጎታ ከናንተ ላይ ሊያስወግድላችሁ፤ ልቦቻችሁንም በትዕግሥት ሊያጠነክርላችሁ፤ በእርሱም ጫማዎችን በአሸዋው ላይ ሊያደላድልላችሁ በእናንተ ላይ ከሰማይ ዝናብን ባወረደ ጊዜ የሆነውን አስታውስ::
അറബി ഖുർആൻ വിവരണങ്ങൾ:
إِذۡ يُوحِي رَبُّكَ إِلَى ٱلۡمَلَٰٓئِكَةِ أَنِّي مَعَكُمۡ فَثَبِّتُواْ ٱلَّذِينَ ءَامَنُواْۚ سَأُلۡقِي فِي قُلُوبِ ٱلَّذِينَ كَفَرُواْ ٱلرُّعۡبَ فَٱضۡرِبُواْ فَوۡقَ ٱلۡأَعۡنَاقِ وَٱضۡرِبُواْ مِنۡهُمۡ كُلَّ بَنَانٖ
12. (መልዕክተኛችን ሙሐመድ ሆይ!) ጌታህ ወደ መላዕክቱ «እኔ በእርዳታዬ ከናንተ ጋር ነኝና እነዚያን በእኔ ያመኑትን ሰዎች አጽናኑ:: በእነዚያ በአላህ በካዱት ልቦች ውስጥ ደግሞ ፍርሀትን እጥላለሁ:: ከአንገቶችም በላይ እራሶችን ምቱ:: ከእነርሱም የቅርንጫፎችን መለያ ( አትቆች) ሁሉ ምቱ።» ሲል ያወረደውን አስታውስ።
അറബി ഖുർആൻ വിവരണങ്ങൾ:
ذَٰلِكَ بِأَنَّهُمۡ شَآقُّواْ ٱللَّهَ وَرَسُولَهُۥۚ وَمَن يُشَاقِقِ ٱللَّهَ وَرَسُولَهُۥ فَإِنَّ ٱللَّهَ شَدِيدُ ٱلۡعِقَابِ
13. ይህ የሆነው በአላህና በመልዕክተኛው ስለካዱ ነው:: አላህንና መልዕክተኛውን ለሚቃወም ሁሉ አላህም ቅጣቱ ብርቱ ነው::
അറബി ഖുർആൻ വിവരണങ്ങൾ:
ذَٰلِكُمۡ فَذُوقُوهُ وَأَنَّ لِلۡكَٰفِرِينَ عَذَابَ ٱلنَّارِ
14. (ከሓዲያን ሆይ!) ይህ ቅጣታችሁ ነው:: እናም ቅመሱት:: ለከሓዲያን የገሀነም እሳት ቅጣት በእርግጥ አለባቸው::
അറബി ഖുർആൻ വിവരണങ്ങൾ:
يَٰٓأَيُّهَا ٱلَّذِينَ ءَامَنُوٓاْ إِذَا لَقِيتُمُ ٱلَّذِينَ كَفَرُواْ زَحۡفٗا فَلَا تُوَلُّوهُمُ ٱلۡأَدۡبَارَ
15. እናንተ ያመናችሁ ሆይ! እነዚያን በአላህ የካዱትን ለጦር ሲጓዙ ባገኛቹኋቸው ጊዜ ጀርባዎችን አታዙሩላቸው::
അറബി ഖുർആൻ വിവരണങ്ങൾ:
وَمَن يُوَلِّهِمۡ يَوۡمَئِذٖ دُبُرَهُۥٓ إِلَّا مُتَحَرِّفٗا لِّقِتَالٍ أَوۡ مُتَحَيِّزًا إِلَىٰ فِئَةٖ فَقَدۡ بَآءَ بِغَضَبٖ مِّنَ ٱللَّهِ وَمَأۡوَىٰهُ جَهَنَّمُۖ وَبِئۡسَ ٱلۡمَصِيرُ
16. ያን ጊዜ ለግድያ ለመዘዋወር ወይም ወደ ሰራዊት ለመቀላቀል ሳይሆን ጀርባውን የሚያዞርላቸው ሰው ሁሉ ከአላህ የሆነን ቁጣ አትርፏል። መኖሪያዉም ገሀነም ናት:: የገሀነም መመለሻነትም ከፋ!
അറബി ഖുർആൻ വിവരണങ്ങൾ:
 
പരിഭാഷ അദ്ധ്യായം: അൻഫാൽ
സൂറത്തുകളുടെ സൂചിക പേജ് നമ്പർ
 
വിശുദ്ധ ഖുർആൻ പരിഭാഷ - അംഹാരിക് പരിഭാഷ - ആഫ്രിക്ക അക്കാദമി - വിവർത്തനങ്ങളുടെ സൂചിക

മൊഴിമാറ്റം മുഹമ്മദ് സെയിൻ സഹ്റുദ്ദീൻ. ആഫ്രിക്ക അക്കാദമി പ്രസിദ്ധീകരണം.

അടക്കുക