Check out the new design

Vertaling van de betekenissen Edele Qur'an - De Amhaarse vertaling - Afrika Academie * - Index van vertaling

PDF XML CSV Excel API
Please review the Terms and Policies

Vertaling van de betekenissen Surah: Al-Ani'jaa   Vers:
لَا يَسۡمَعُونَ حَسِيسَهَاۖ وَهُمۡ فِي مَا ٱشۡتَهَتۡ أَنفُسُهُمۡ خَٰلِدُونَ
102. ድምጿንም አይሰሙም:: እነርሱም ነፍሶቻቸው በሚሹት ነገር ውስጥ ዘውታሪዎች ናቸው::
Arabische uitleg van de Qur'an:
لَا يَحۡزُنُهُمُ ٱلۡفَزَعُ ٱلۡأَكۡبَرُ وَتَتَلَقَّىٰهُمُ ٱلۡمَلَٰٓئِكَةُ هَٰذَا يَوۡمُكُمُ ٱلَّذِي كُنتُمۡ تُوعَدُونَ
103. ታላቁ ድንጋጤ አያስተክዛቸዉም:: መላእክትም «ይህ ያ ! ትቀጠሩት የነበራችሁት ቀናችሁ ነው።» እያሉ ይቀበሏቸዋል።
Arabische uitleg van de Qur'an:
يَوۡمَ نَطۡوِي ٱلسَّمَآءَ كَطَيِّ ٱلسِّجِلِّ لِلۡكُتُبِۚ كَمَا بَدَأۡنَآ أَوَّلَ خَلۡقٖ نُّعِيدُهُۥۚ وَعۡدًا عَلَيۡنَآۚ إِنَّا كُنَّا فَٰعِلِينَ
104. (መልዕክተኛችን ሙሐመድ ሆይ!) ለመጽሐፎች ገፆች እንደሚጠቀለሉ ሁሉ ሰማይን የምንጠቀልልበትን ቀን አስታውስ:: የመጀመሪያን ፍጥረት እንደ ጀመርን እንመልሰዋለን:: ይህን መፈጸሙ የማይቀር ቀጠሮን ቀጠርን:: እኛ የቀጠርነውን ሰሪዎች ነን::
Arabische uitleg van de Qur'an:
وَلَقَدۡ كَتَبۡنَا فِي ٱلزَّبُورِ مِنۢ بَعۡدِ ٱلذِّكۡرِ أَنَّ ٱلۡأَرۡضَ يَرِثُهَا عِبَادِيَ ٱلصَّٰلِحُونَ
105. ምድርንም መልካሞቹ ባሮቼ ይወርሷታል ማለትን ከመጽሐፉ (ከተጠበቀው ሰሌዳ) በኋላ በመጽሐፎች በእርግጥ ጽፈናል::
Arabische uitleg van de Qur'an:
إِنَّ فِي هَٰذَا لَبَلَٰغٗا لِّقَوۡمٍ عَٰبِدِينَ
106.በዚህ ቁርኣን ውስጥ ያሉት ህግጋት ለአላህ ተገዢ ህዝቦች ሁሉ በቂ ናቸው።
Arabische uitleg van de Qur'an:
وَمَآ أَرۡسَلۡنَٰكَ إِلَّا رَحۡمَةٗ لِّلۡعَٰلَمِينَ
107. (መልዕክተኛችን ሙሐመድ ሆይ!) ለዓለማት እዝነት አድርገን እንጂ አልላክንህም::
Arabische uitleg van de Qur'an:
قُلۡ إِنَّمَا يُوحَىٰٓ إِلَيَّ أَنَّمَآ إِلَٰهُكُمۡ إِلَٰهٞ وَٰحِدٞۖ فَهَلۡ أَنتُم مُّسۡلِمُونَ
108. (መልዕክተኛችን ሙሐመድ ሆይ!) «ያ ወደ እኔ የሚወርደው መልዕክት ‹አምላካችሁ አንድ አምላክ ብቻ ነው።› የሚል ነው:: ታዲያ እናንተ ፍጹም ታዛዦች ናችሁን?» በላቸው።
Arabische uitleg van de Qur'an:
فَإِن تَوَلَّوۡاْ فَقُلۡ ءَاذَنتُكُمۡ عَلَىٰ سَوَآءٖۖ وَإِنۡ أَدۡرِيٓ أَقَرِيبٌ أَم بَعِيدٞ مَّا تُوعَدُونَ
109. (መልዕክተኛችን ሙሐመድ ሆይ!) እምቢ ቢሉም (እንዲህ) በላቸው: «የታዘዝኩትን በእኩልነት አሳውቂያችኋለሁ:: የምትስፈራሩበትም ነገር ቅርብ ወይም ሩቅ መሆኑን አላውቅም።
Arabische uitleg van de Qur'an:
إِنَّهُۥ يَعۡلَمُ ٱلۡجَهۡرَ مِنَ ٱلۡقَوۡلِ وَيَعۡلَمُ مَا تَكۡتُمُونَ
110. «እርሱ ከንግግር ጩኸቱን ያውቃል:: የምትደብቁትንም ሁሉ ያውቃል::
Arabische uitleg van de Qur'an:
وَإِنۡ أَدۡرِي لَعَلَّهُۥ فِتۡنَةٞ لَّكُمۡ وَمَتَٰعٌ إِلَىٰ حِينٖ
111. (መልዕክተኛችን ሙሐመድ ሆይ!) «እርሱም ቅጣትን ማቆየት ምናልባት ለእናንተ ፈተናና እስከ ጊዜው መጣቀሚያ እንደ ሆነም አላውቅም።» በላቸው::
Arabische uitleg van de Qur'an:
قَٰلَ رَبِّ ٱحۡكُم بِٱلۡحَقِّۗ وَرَبُّنَا ٱلرَّحۡمَٰنُ ٱلۡمُسۡتَعَانُ عَلَىٰ مَا تَصِفُونَ
112. «ጌታዬ ሆይ! በእውነት ፍረድ:: ጌታችንም እጅግ በጣም ሩህሩህን በምትሉት ነገር ላይ መታገዣ ነው።» አለ::
Arabische uitleg van de Qur'an:
 
Vertaling van de betekenissen Surah: Al-Ani'jaa
Surah's Index Pagina nummer
 
Vertaling van de betekenissen Edele Qur'an - De Amhaarse vertaling - Afrika Academie - Index van vertaling

Vertaald door Mohammed Zayn Zaher Ad-Din. Uitgegeven door de Afrika Academie.

Sluit