Check out the new design

Vertaling van de betekenissen Edele Qur'an - De Amhaarse vertaling - Afrika Academie * - Index van vertaling

PDF XML CSV Excel API
Please review the Terms and Policies

Vertaling van de betekenissen Surah: An-nisa   Vers:
وَإِنِ ٱمۡرَأَةٌ خَافَتۡ مِنۢ بَعۡلِهَا نُشُوزًا أَوۡ إِعۡرَاضٗا فَلَا جُنَاحَ عَلَيۡهِمَآ أَن يُصۡلِحَا بَيۡنَهُمَا صُلۡحٗاۚ وَٱلصُّلۡحُ خَيۡرٞۗ وَأُحۡضِرَتِ ٱلۡأَنفُسُ ٱلشُّحَّۚ وَإِن تُحۡسِنُواْ وَتَتَّقُواْ فَإِنَّ ٱللَّهَ كَانَ بِمَا تَعۡمَلُونَ خَبِيرٗا
128. ሴት ልጅ ከባሏ ጥላቻን ወይም ከእርሷ ፊቱን ማዞሩን ብታውቅ እና ከዚያ በመካከላቸው እንደገና ቢስማሙ በሁለቱ ላይ ኃጢአት የለባቸዉም:: መታረቅ መልካም ነውና:: ነፍሶች ሁሉ ንፍገት ተጣለባቸው:: (ባሎች ሆይ!) መልካም ነገር ብትሰሩና ብትጠነቀቁ ግን አላህ በምትሰሩት ነገር ሁሉ ውስጠ አዋቂ ነው::
Arabische uitleg van de Qur'an:
وَلَن تَسۡتَطِيعُوٓاْ أَن تَعۡدِلُواْ بَيۡنَ ٱلنِّسَآءِ وَلَوۡ حَرَصۡتُمۡۖ فَلَا تَمِيلُواْ كُلَّ ٱلۡمَيۡلِ فَتَذَرُوهَا كَٱلۡمُعَلَّقَةِۚ وَإِن تُصۡلِحُواْ وَتَتَّقُواْ فَإِنَّ ٱللَّهَ كَانَ غَفُورٗا رَّحِيمٗا
129. (ባሎች ሆይ! ) በሁለትና ከዚያ በላይ በሆኑ ሴቶች መካከል ምንም እንኳን ብትጓጉ በፍቅር ለማስተካከል አትችሉም። ሆኖም እንደተንጠለጠለች (ገመድ) አድርጋችሁ ትተዋት ዘንድ ወደምትወዷት ሴት ሙሉ መዘንበልን አትንዘንበሉ:: ብታበጁና ብትጠነቀቁ አላህ መሀሪና አዛኝ ነው::
Arabische uitleg van de Qur'an:
وَإِن يَتَفَرَّقَا يُغۡنِ ٱللَّهُ كُلّٗا مِّن سَعَتِهِۦۚ وَكَانَ ٱللَّهُ وَٰسِعًا حَكِيمٗا
130. ባልና ሚስት በመሀከላቸው በተፈጠረው ችግር ቢለያዩ አላህ ሁሉንም በችሮታው ያብቃቃቸዋል:: አላህ ችሮታው ሰፊና ጥበበኛ ነውና::
Arabische uitleg van de Qur'an:
وَلِلَّهِ مَا فِي ٱلسَّمَٰوَٰتِ وَمَا فِي ٱلۡأَرۡضِۗ وَلَقَدۡ وَصَّيۡنَا ٱلَّذِينَ أُوتُواْ ٱلۡكِتَٰبَ مِن قَبۡلِكُمۡ وَإِيَّاكُمۡ أَنِ ٱتَّقُواْ ٱللَّهَۚ وَإِن تَكۡفُرُواْ فَإِنَّ لِلَّهِ مَا فِي ٱلسَّمَٰوَٰتِ وَمَا فِي ٱلۡأَرۡضِۚ وَكَانَ ٱللَّهُ غَنِيًّا حَمِيدٗا
131. በሰማያትና በምድር ያለው ሁሉ የአላህ ነው:: እነዚያንም ከበፊታችሁ መጽሐፍ የተሰጡትን እናንተንም አላህን ፍሩ በማለት በእርግጥ አዘዝን:: ብትክዱም በሰማያትና በምድር ያለው ሁሉ የአላህ ነው አትጎዱትም:: አላህ በራሱ ተብቃቂና ምስጉን ነውና::
Arabische uitleg van de Qur'an:
وَلِلَّهِ مَا فِي ٱلسَّمَٰوَٰتِ وَمَا فِي ٱلۡأَرۡضِۚ وَكَفَىٰ بِٱللَّهِ وَكِيلًا
132. በሰማያትና በምድር ያለው ሁሉ የአላህ ብቻ ነው:: መመኪያነትም በአላህ በቃ::
Arabische uitleg van de Qur'an:
إِن يَشَأۡ يُذۡهِبۡكُمۡ أَيُّهَا ٱلنَّاسُ وَيَأۡتِ بِـَٔاخَرِينَۚ وَكَانَ ٱللَّهُ عَلَىٰ ذَٰلِكَ قَدِيرٗا
133. (እናንተ ሰዎች ሆይ!) አላህ ቢሻ ያስወግዳችሁና ሌሎችን በቦታችሁ ላይ ይተካል:: አላህም በዚህ ላይ ቻይ ነው::
Arabische uitleg van de Qur'an:
مَّن كَانَ يُرِيدُ ثَوَابَ ٱلدُّنۡيَا فَعِندَ ٱللَّهِ ثَوَابُ ٱلدُّنۡيَا وَٱلۡأٓخِرَةِۚ وَكَانَ ٱللَّهُ سَمِيعَۢا بَصِيرٗا
134. የቅርቢቱን አለም ምንዳ የሚፈልግ ሁሉ አላህ ዘንድ የቅርቢቱና የመጨረሻይቱ ምንዳ አለ:: አላህ ሁሉን ሰሚ እና ሁሉን ተመልካች ነውና::
Arabische uitleg van de Qur'an:
 
Vertaling van de betekenissen Surah: An-nisa
Surah's Index Pagina nummer
 
Vertaling van de betekenissen Edele Qur'an - De Amhaarse vertaling - Afrika Academie - Index van vertaling

Vertaald door Mohammed Zayn Zaher Ad-Din. Uitgegeven door de Afrika Academie.

Sluit