Check out the new design

Vertaling van de betekenissen Edele Qur'an - De Amhaarse vertaling - Afrika Academie * - Index van vertaling


Vertaling van de betekenissen Surah: el-Anfaal   Vers:
وَأَطِيعُواْ ٱللَّهَ وَرَسُولَهُۥ وَلَا تَنَٰزَعُواْ فَتَفۡشَلُواْ وَتَذۡهَبَ رِيحُكُمۡۖ وَٱصۡبِرُوٓاْۚ إِنَّ ٱللَّهَ مَعَ ٱلصَّٰبِرِينَ
46. (ሙስሊሞች ሆይ!) አላህንና መልዕክተኛውን ታዘዙ :: አትጨቃጨቁም ትፈራላችሁና ኃይላችሁም ትሄዳለችና:: ታገሡም አላህ በእርዳታው ከትዕግሥተኞች ጋር ነውና::
Arabische uitleg van de Qur'an:
وَلَا تَكُونُواْ كَٱلَّذِينَ خَرَجُواْ مِن دِيَٰرِهِم بَطَرٗا وَرِئَآءَ ٱلنَّاسِ وَيَصُدُّونَ عَن سَبِيلِ ٱللَّهِۚ وَٱللَّهُ بِمَا يَعۡمَلُونَ مُحِيطٞ
47. እንደ እነዚያ ለትዕቢትና ለሰዎች ይዩልኝ ሲሉ ከአላህም መንገድ ለማገድ ከሀገራቸው እንደወጡት ሰዎች አትሁኑ:: አላህ በሚሠሩት ሁሉ በእውቀቱ ከባቢ ነውና::
Arabische uitleg van de Qur'an:
وَإِذۡ زَيَّنَ لَهُمُ ٱلشَّيۡطَٰنُ أَعۡمَٰلَهُمۡ وَقَالَ لَا غَالِبَ لَكُمُ ٱلۡيَوۡمَ مِنَ ٱلنَّاسِ وَإِنِّي جَارٞ لَّكُمۡۖ فَلَمَّا تَرَآءَتِ ٱلۡفِئَتَانِ نَكَصَ عَلَىٰ عَقِبَيۡهِ وَقَالَ إِنِّي بَرِيٓءٞ مِّنكُمۡ إِنِّيٓ أَرَىٰ مَا لَا تَرَوۡنَ إِنِّيٓ أَخَافُ ٱللَّهَۚ وَٱللَّهُ شَدِيدُ ٱلۡعِقَابِ
48. ሰይጣንም ሥራዎቻቸውን ለእነርሱ ባሳመረላቸውና «ዛሬ ለእናንተ ከሰዎች አሸናፊ የላችሁም:: እኔም ለእናንተ ረዳት ነኝ።» ባለ ጊዜም (የሆነውን አስታውስ):: ሁለቱ ቡድኖችም በተያዩ ጊዜ ወደኋላው አፈገፈገ:: «እኔ ከናንተ ንጹህ ነኝ:: እኔ እናንተ የማታዩትን አያለሁ:: እኔ አላህን እፈራለሁ:: አላህም ቅጣተ ብርቱ ነው።» አላቸው::
Arabische uitleg van de Qur'an:
إِذۡ يَقُولُ ٱلۡمُنَٰفِقُونَ وَٱلَّذِينَ فِي قُلُوبِهِم مَّرَضٌ غَرَّ هَٰٓؤُلَآءِ دِينُهُمۡۗ وَمَن يَتَوَكَّلۡ عَلَى ٱللَّهِ فَإِنَّ ٱللَّهَ عَزِيزٌ حَكِيمٞ
49. (መልዕክተኛችን ሙሐመድ ሆይ!) አስመሳዮችና እነዚያ በልቦቻቸው ውስጥ በሽታ ያለባቸው ሰዎች «እነዚህን ሙስሊሞች ሃይማኖታቸው አታለላቸው።» ባሉ ጊዜ (የነበረውን አስታውስ):: በአላህ ላይ የሚጠጋ (ሁልጊዜም ያሸንፋል):: አላህ ሁሉንም አሸናፊና ጥበበኛ ነውና::
Arabische uitleg van de Qur'an:
وَلَوۡ تَرَىٰٓ إِذۡ يَتَوَفَّى ٱلَّذِينَ كَفَرُواْ ٱلۡمَلَٰٓئِكَةُ يَضۡرِبُونَ وُجُوهَهُمۡ وَأَدۡبَٰرَهُمۡ وَذُوقُواْ عَذَابَ ٱلۡحَرِيقِ
50. (መልዕክተኛችን ሙሐመድ ሆይ!) እነዚያንም በአላህ የካዱትን ሰዎች መላዕክት ፊቶቻቸውንና ጀርቦቻቸውን እየመቱ «የቃጠሎን ስቃይ ቅመሱ።» እያሉ በሚገድሏቸው ጊዜ ብታይ ኖሮ (አስደንጋጭን ነገር ታይ ነበር)::
Arabische uitleg van de Qur'an:
ذَٰلِكَ بِمَا قَدَّمَتۡ أَيۡدِيكُمۡ وَأَنَّ ٱللَّهَ لَيۡسَ بِظَلَّٰمٖ لِّلۡعَبِيدِ
51. «ይህ እጆቻችሁ ባስቀደሙት ምክንያት አላህ ለባሮቹ በዳይ ባለመሆኑ ነው።» ይባላሉ።
Arabische uitleg van de Qur'an:
كَدَأۡبِ ءَالِ فِرۡعَوۡنَ وَٱلَّذِينَ مِن قَبۡلِهِمۡۚ كَفَرُواْ بِـَٔايَٰتِ ٱللَّهِ فَأَخَذَهُمُ ٱللَّهُ بِذُنُوبِهِمۡۚ إِنَّ ٱللَّهَ قَوِيّٞ شَدِيدُ ٱلۡعِقَابِ
52. የእነዚያ ሰዎች ልማድ እንደ ፈርዖን ቤተሰብና እንደነዚያም ከእነርሱ በፊት እንደ ነበሩት ህዝቦች ልማድ ነው:: በአላህ አናቅጽ ካዱ:: አላህም በኃጢአቶቻቸው ያዛቸው:: አላህ ሀይለኛና ቅጣተ ብርቱ ነውና::
Arabische uitleg van de Qur'an:
 
Vertaling van de betekenissen Surah: el-Anfaal
Surah's Index Pagina nummer
 
Vertaling van de betekenissen Edele Qur'an - De Amhaarse vertaling - Afrika Academie - Index van vertaling

Vertaald door Mohammed Zayn Zaher Ad-Din. Uitgegeven door de Afrika Academie.

Sluit