Check out the new design

ߞߎ߬ߙߣߊ߬ ߞߟߊߒߞߋ ߞߘߐ ߟߎ߬ ߘߟߊߡߌߘߊ - ߊߡߎߤߊߙߌߞߊ߲ ߘߟߊߡߌߘߊ - ߊߞߊ߬ߘߌߡߌߘߌ ߊߝߙߌߞߌߟߊ * - ߘߟߊߡߌߘߊ ߟߎ߫ ߦߌ߬ߘߊ߬ߥߟߊ


ߞߘߐ ߟߎ߬ ߘߟߊߡߌ߬ߘߊ߬ߟߌ ߝߐߘߊ ߘߏ߫: ߌߓߎ߬ߙߊ߬ߤߌߡߊ߫   ߟߝߊߙߌ ߘߏ߫:
وَإِذۡ قَالَ مُوسَىٰ لِقَوۡمِهِ ٱذۡكُرُواْ نِعۡمَةَ ٱللَّهِ عَلَيۡكُمۡ إِذۡ أَنجَىٰكُم مِّنۡ ءَالِ فِرۡعَوۡنَ يَسُومُونَكُمۡ سُوٓءَ ٱلۡعَذَابِ وَيُذَبِّحُونَ أَبۡنَآءَكُمۡ وَيَسۡتَحۡيُونَ نِسَآءَكُمۡۚ وَفِي ذَٰلِكُم بَلَآءٞ مِّن رَّبِّكُمۡ عَظِيمٞ
6. (መልዕክተኛችን ሙሐመድ ሆይ!) ሙሳም ለህዝቦቹ «ከፈርዖን ቤተሰቦች መጥፎን ቅጣት የሚያቀምሷችሁ፤ ወንዶች ልጆቻችሁን የሚያርዱና ሴቶቻችሁንም የሚተው ሲሆን በአዳናችሁ ጊዜ በእናንተ ላይ የዋለላችሁን የአላህን ጸጋ አስታውሱ:: በዚሃችሁ ከጌታችሁ የሆነ ታላቅ ፈተና አለበት።» ባለ ጊዜ የሆነውን አስታውስ::
ߊߙߊߓߎߞߊ߲ߡߊ ߞߘߐߦߌߘߊ ߟߎ߬:
وَإِذۡ تَأَذَّنَ رَبُّكُمۡ لَئِن شَكَرۡتُمۡ لَأَزِيدَنَّكُمۡۖ وَلَئِن كَفَرۡتُمۡ إِنَّ عَذَابِي لَشَدِيدٞ
7. ጌታችሁም፦ «ብታመሰግኑ በእርግጥ እጨምርላችኋለሁ:: ብትክዱም እቀጣችኋለሁ:: ቅጣቴ በእርግጥ ብርቱ ነው።» በማለት ባስታወቀ ጊዜ (የሆነዉን አስታውሱ)::
ߊߙߊߓߎߞߊ߲ߡߊ ߞߘߐߦߌߘߊ ߟߎ߬:
وَقَالَ مُوسَىٰٓ إِن تَكۡفُرُوٓاْ أَنتُمۡ وَمَن فِي ٱلۡأَرۡضِ جَمِيعٗا فَإِنَّ ٱللَّهَ لَغَنِيٌّ حَمِيدٌ
8. ሙሳ፡- «እናንተም በምድር ያለዉም ሁሉ በመላ ብትክዱ አላህ ተብቃቂና ምስጉን ነው።» አለ።
ߊߙߊߓߎߞߊ߲ߡߊ ߞߘߐߦߌߘߊ ߟߎ߬:
أَلَمۡ يَأۡتِكُمۡ نَبَؤُاْ ٱلَّذِينَ مِن قَبۡلِكُمۡ قَوۡمِ نُوحٖ وَعَادٖ وَثَمُودَ وَٱلَّذِينَ مِنۢ بَعۡدِهِمۡ لَا يَعۡلَمُهُمۡ إِلَّا ٱللَّهُۚ جَآءَتۡهُمۡ رُسُلُهُم بِٱلۡبَيِّنَٰتِ فَرَدُّوٓاْ أَيۡدِيَهُمۡ فِيٓ أَفۡوَٰهِهِمۡ وَقَالُوٓاْ إِنَّا كَفَرۡنَا بِمَآ أُرۡسِلۡتُم بِهِۦ وَإِنَّا لَفِي شَكّٖ مِّمَّا تَدۡعُونَنَآ إِلَيۡهِ مُرِيبٖ
9. (ሙስሊሞች ሆይ!) የእነዚያ ከእናንተ በፊት የነበሩት የኑህ ህዝቦች፤ የዓድ፣ የሠሙድም የእነዚያም ከእነርሱ በኋላ የነበሩት ከአላህ በስተቀር ሌላ የማያውቃቸው ህዝቦች ወሬ (ታሪክ) አልመጣላችሁምን? መልዕክተኞቻቸው በማስረጃዎች መጡላቸውና እጆቻቸውን በቁጭት ሊነክሱ ወደ አፎቻቸው መለሱ: «በተላካችሁበት ነገር ካድን እኛም ወደ እርሱ ከምትጠሩን ነገር አወላዋይ በሆነ ጥርጣሬ ውስጥ ነን።» አሉ።
ߊߙߊߓߎߞߊ߲ߡߊ ߞߘߐߦߌߘߊ ߟߎ߬:
۞ قَالَتۡ رُسُلُهُمۡ أَفِي ٱللَّهِ شَكّٞ فَاطِرِ ٱلسَّمَٰوَٰتِ وَٱلۡأَرۡضِۖ يَدۡعُوكُمۡ لِيَغۡفِرَ لَكُم مِّن ذُنُوبِكُمۡ وَيُؤَخِّرَكُمۡ إِلَىٰٓ أَجَلٖ مُّسَمّٗىۚ قَالُوٓاْ إِنۡ أَنتُمۡ إِلَّا بَشَرٞ مِّثۡلُنَا تُرِيدُونَ أَن تَصُدُّونَا عَمَّا كَانَ يَعۡبُدُ ءَابَآؤُنَا فَأۡتُونَا بِسُلۡطَٰنٖ مُّبِينٖ
10. መልዕክተኞቻቸው «ከኃጢአቶቻችሁ እንዲሚራችሁ ወደ ተወሰነ ጊዜም ያለ ቅጣት እንዲያቆያችሁ የሚጠራችሁ ሲሆን ሰማያትንና ምድርን ፈጣሪ በሆነው አላህ በመኖሩ ጥርጣሬ አለን?» አሏቸው:: ህዝቦቹም፡ «እናንተ ብጤያችን ሰው እንጂ (ሌላ ፍጡር) አይደላችሁም:: አባቶቻችን ይገዙት ከነበሩት ልትከለክሉን ትሻላችሁን? ግልጽን አስረጅ ካመጣችሁት ሌላ እስቲ አምጡልን።» አሉ::
ߊߙߊߓߎߞߊ߲ߡߊ ߞߘߐߦߌߘߊ ߟߎ߬:
 
ߞߘߐ ߟߎ߬ ߘߟߊߡߌ߬ߘߊ߬ߟߌ ߝߐߘߊ ߘߏ߫: ߌߓߎ߬ߙߊ߬ߤߌߡߊ߫
ߝߐߘߊ ߟߎ߫ ߦߌ߬ߘߊ߬ߥߟߊ ߞߐߜߍ ߝߙߍߕߍ
 
ߞߎ߬ߙߣߊ߬ ߞߟߊߒߞߋ ߞߘߐ ߟߎ߬ ߘߟߊߡߌߘߊ - ߊߡߎߤߊߙߌߞߊ߲ ߘߟߊߡߌߘߊ - ߊߞߊ߬ߘߌߡߌߘߌ ߊߝߙߌߞߌߟߊ - ߘߟߊߡߌߘߊ ߟߎ߫ ߦߌ߬ߘߊ߬ߥߟߊ

ߡߎ߬ߤ߭ߊߡߡߊߘߎ߫ ߛߌ߲ߣߌ߲ ߛߌߙߘߌ߲ߘߌ߲߫ ߓߟߏ߫. ߛߊ߬ߘߊ߬ߙߌ߫ ߊ߲ߞߊ߬ߘߌ߬ߡߌ߫ ߊߝߙߌߞߌ߫.

ߘߊߕߎ߲߯ߠߌ߲