Check out the new design

ߞߎ߬ߙߣߊ߬ ߞߟߊߒߞߋ ߞߘߐ ߟߎ߬ ߘߟߊߡߌߘߊ - ߊߡߎߤߊߙߌߞߊ߲ ߘߟߊߡߌߘߊ - ߊߞߊ߬ߘߌߡߌߘߌ ߊߝߙߌߞߌߟߊ * - ߘߟߊߡߌߘߊ ߟߎ߫ ߦߌ߬ߘߊ߬ߥߟߊ


ߞߘߐ ߟߎ߬ ߘߟߊߡߌ߬ߘߊ߬ߟߌ ߝߐߘߊ ߘߏ߫: ߌߓߎ߬ߙߊ߬ߤߌߡߊ߫   ߟߝߊߙߌ ߘߏ߫:
مُهۡطِعِينَ مُقۡنِعِي رُءُوسِهِمۡ لَا يَرۡتَدُّ إِلَيۡهِمۡ طَرۡفُهُمۡۖ وَأَفۡـِٔدَتُهُمۡ هَوَآءٞ
43. ወደ ጠሪው መልአክ ቸኳዮች ራሶቻቸውንም አንጋጣጮች ሆነው ዓይኖቻቸው ይፈጣሉ። ዓይኖቻቸው ወደ እነርሱ አይመለሱም:: ልቦቻቸው ባዶዎች ናቸው::
ߊߙߊߓߎߞߊ߲ߡߊ ߞߘߐߦߌߘߊ ߟߎ߬:
وَأَنذِرِ ٱلنَّاسَ يَوۡمَ يَأۡتِيهِمُ ٱلۡعَذَابُ فَيَقُولُ ٱلَّذِينَ ظَلَمُواْ رَبَّنَآ أَخِّرۡنَآ إِلَىٰٓ أَجَلٖ قَرِيبٖ نُّجِبۡ دَعۡوَتَكَ وَنَتَّبِعِ ٱلرُّسُلَۗ أَوَلَمۡ تَكُونُوٓاْ أَقۡسَمۡتُم مِّن قَبۡلُ مَا لَكُم مِّن زَوَالٖ
44. (መልዕክተኛችን ሙሐመድ ሆይ!) ሰዎችንም ቅጣቱ የሚመጣባቸውን ቀን አስፈራራቸው:: እነዚያም የበደሉትማ «ጌታችን ሆይ! እስከ ቅርብ ጊዜ ድረስ አቆየን:: ጥሪህንም እንቀበላለንና መልዕክተኞቹንም እንከተላለንና።» ይላሉ። ይባላሉም: «ከአሁን በፊት በምድረ ዓለም ለእናንተ ምንም መወገድ የላችሁም በማለት የማላችሁ አልነበራችሁምን?
ߊߙߊߓߎߞߊ߲ߡߊ ߞߘߐߦߌߘߊ ߟߎ߬:
وَسَكَنتُمۡ فِي مَسَٰكِنِ ٱلَّذِينَ ظَلَمُوٓاْ أَنفُسَهُمۡ وَتَبَيَّنَ لَكُمۡ كَيۡفَ فَعَلۡنَا بِهِمۡ وَضَرَبۡنَا لَكُمُ ٱلۡأَمۡثَالَ
45. «በእነዚያም ነፍሶቻቸውን በበደሉት ሰዎች መኖሪያ ውስጥ ተቀመጣችሁ:: በእነርሱም እንዴት እንደሠራንባቸው ለእናንተም ተገለጸላችሁ፤ ለእናንተ ምሳሌዎችንም ገለጽንላችሁ።»
ߊߙߊߓߎߞߊ߲ߡߊ ߞߘߐߦߌߘߊ ߟߎ߬:
وَقَدۡ مَكَرُواْ مَكۡرَهُمۡ وَعِندَ ٱللَّهِ مَكۡرُهُمۡ وَإِن كَانَ مَكۡرُهُمۡ لِتَزُولَ مِنۡهُ ٱلۡجِبَالُ
46. በነብዩ ላይ ሴራቸውንም በእርግጥ አሴሩ:: ሴራቸዉም ቅጣቱ አላህ ዘንድ ነው:: ሴራቸዉም ኮረብታዎች በእርሱ የሚወገዱበት አልነበረም::
ߊߙߊߓߎߞߊ߲ߡߊ ߞߘߐߦߌߘߊ ߟߎ߬:
فَلَا تَحۡسَبَنَّ ٱللَّهَ مُخۡلِفَ وَعۡدِهِۦ رُسُلَهُۥٓۚ إِنَّ ٱللَّهَ عَزِيزٞ ذُو ٱنتِقَامٖ
47. (መልዕክተኛችን ሙሐመድ ሆይ!) አላህንም ለመልዕክተኞቹ የገባላቸውን ቃል ኪዳኑን አፍራሽ አድርገህ አታስብ:: አላህ ሁሉን አሸናፊና የመበቀል ባለቤት ነው::
ߊߙߊߓߎߞߊ߲ߡߊ ߞߘߐߦߌߘߊ ߟߎ߬:
يَوۡمَ تُبَدَّلُ ٱلۡأَرۡضُ غَيۡرَ ٱلۡأَرۡضِ وَٱلسَّمَٰوَٰتُۖ وَبَرَزُواْ لِلَّهِ ٱلۡوَٰحِدِ ٱلۡقَهَّارِ
48. ምድር በሌላ ምድር የምትለወጥበትን ሰማያትም እንደዚሁ በሌላ ሰማያት የሚለወጥበትን እና አንድ ብቸኛና አሸናፊ ለሆነው አላህ ፍጡራን ሁሉ የሚገለጹበትን ቀን የሚሆነውን አስታውስ::
ߊߙߊߓߎߞߊ߲ߡߊ ߞߘߐߦߌߘߊ ߟߎ߬:
وَتَرَى ٱلۡمُجۡرِمِينَ يَوۡمَئِذٖ مُّقَرَّنِينَ فِي ٱلۡأَصۡفَادِ
49. (መልዕክተኛችን ሙሐመድ ሆይ!) አመጸኞችንም በዚያ ቀን በሰንሰለቶች ተቆራኝተው ታያቸዋለህ::
ߊߙߊߓߎߞߊ߲ߡߊ ߞߘߐߦߌߘߊ ߟߎ߬:
سَرَابِيلُهُم مِّن قَطِرَانٖ وَتَغۡشَىٰ وُجُوهَهُمُ ٱلنَّارُ
50. ቀሚሶቻቸው ከካትራሜ የተሰሩ ናቸው:: ፊቶቻቸውንም እሳት ትሸፍናቸዋለች::
ߊߙߊߓߎߞߊ߲ߡߊ ߞߘߐߦߌߘߊ ߟߎ߬:
لِيَجۡزِيَ ٱللَّهُ كُلَّ نَفۡسٖ مَّا كَسَبَتۡۚ إِنَّ ٱللَّهَ سَرِيعُ ٱلۡحِسَابِ
51. አላህ ይህንን ያደረገው ነፍስ ሁሉ የሠራችውን ትመነዳ ዘንድ ነው:: አላህ ምርመራው ፈጣን ነው::
ߊߙߊߓߎߞߊ߲ߡߊ ߞߘߐߦߌߘߊ ߟߎ߬:
هَٰذَا بَلَٰغٞ لِّلنَّاسِ وَلِيُنذَرُواْ بِهِۦ وَلِيَعۡلَمُوٓاْ أَنَّمَا هُوَ إِلَٰهٞ وَٰحِدٞ وَلِيَذَّكَّرَ أُوْلُواْ ٱلۡأَلۡبَٰبِ
52. (መልዕክተኛችን ሙሐመድ ሆይ!) ይህ ቁርኣን ለሰዎች ገሳጭና መድረስ ያለበት ነው:: ሊመከሩበት በእርሱም ሊስፈራሩበት፤ እርሱም አንድ አምላክ ብቻ መሆኑን ሊያውቁበት፤ የአእምሮ ባለቤቶችም ሊገሰጹበት የተወረደ ነው::
ߊߙߊߓߎߞߊ߲ߡߊ ߞߘߐߦߌߘߊ ߟߎ߬:
 
ߞߘߐ ߟߎ߬ ߘߟߊߡߌ߬ߘߊ߬ߟߌ ߝߐߘߊ ߘߏ߫: ߌߓߎ߬ߙߊ߬ߤߌߡߊ߫
ߝߐߘߊ ߟߎ߫ ߦߌ߬ߘߊ߬ߥߟߊ ߞߐߜߍ ߝߙߍߕߍ
 
ߞߎ߬ߙߣߊ߬ ߞߟߊߒߞߋ ߞߘߐ ߟߎ߬ ߘߟߊߡߌߘߊ - ߊߡߎߤߊߙߌߞߊ߲ ߘߟߊߡߌߘߊ - ߊߞߊ߬ߘߌߡߌߘߌ ߊߝߙߌߞߌߟߊ - ߘߟߊߡߌߘߊ ߟߎ߫ ߦߌ߬ߘߊ߬ߥߟߊ

ߡߎ߬ߤ߭ߊߡߡߊߘߎ߫ ߛߌ߲ߣߌ߲ ߛߌߙߘߌ߲ߘߌ߲߫ ߓߟߏ߫. ߛߊ߬ߘߊ߬ߙߌ߫ ߊ߲ߞߊ߬ߘߌ߬ߡߌ߫ ߊߝߙߌߞߌ߫.

ߘߊߕߎ߲߯ߠߌ߲