Check out the new design

د قرآن کریم د معناګانو ژباړه - امهري ژباړه - محمد صادق * - د ژباړو فهرست (لړلیک)

XML CSV Excel API
Please review the Terms and Policies

د معناګانو ژباړه سورت: حج   آیت:
أَلَمۡ تَرَ أَنَّ ٱللَّهَ سَخَّرَ لَكُم مَّا فِي ٱلۡأَرۡضِ وَٱلۡفُلۡكَ تَجۡرِي فِي ٱلۡبَحۡرِ بِأَمۡرِهِۦ وَيُمۡسِكُ ٱلسَّمَآءَ أَن تَقَعَ عَلَى ٱلۡأَرۡضِ إِلَّا بِإِذۡنِهِۦٓۚ إِنَّ ٱللَّهَ بِٱلنَّاسِ لَرَءُوفٞ رَّحِيمٞ
አላህ በምድር ውስጥ ያለን ሁሉ ለእናንተ የገራላችሁ፣ መርከቦችንም በባሕር ውስጥ በፈቃዱ የሚንሻለሉ ሲኾኑ (የገራላችሁ) መኾኑን፣ ሰማይንም በፈቃዱ ካልኾነ በምድር ላይ እንዳትወድቅ የሚይዛት መኾኑን አላየህምን? አላህ ለሰዎች በእርግጥ ሩኅሩኅ አዛኝ ነው፡፡
عربي تفسیرونه:
وَهُوَ ٱلَّذِيٓ أَحۡيَاكُمۡ ثُمَّ يُمِيتُكُمۡ ثُمَّ يُحۡيِيكُمۡۗ إِنَّ ٱلۡإِنسَٰنَ لَكَفُورٞ
እርሱም ያ ሕያው ያደረጋችሁ ነው፡፡ ከዚያም ይገድላችኋል፡፡ ከዚያም ሕያው ያደርጋችኋል፡፡ ሰው በእርግጥ በጣም ከሓዲ ነው፡፡
عربي تفسیرونه:
لِّكُلِّ أُمَّةٖ جَعَلۡنَا مَنسَكًا هُمۡ نَاسِكُوهُۖ فَلَا يُنَٰزِعُنَّكَ فِي ٱلۡأَمۡرِۚ وَٱدۡعُ إِلَىٰ رَبِّكَۖ إِنَّكَ لَعَلَىٰ هُدٗى مُّسۡتَقِيمٖ
ለየሕዝቡ ሁሉ እነሱ የሚሠሩበት የኾነን ሥርዓተ ሃይማኖት አድርገናል፡፡ ስለዚህ በነገሩ አይከራከሩህ፡፡ ወደ ጌታህ መንገድም ጥራ፡፡ አንተ በእርግጥ በቅኑ መንገድ ላይ ነህና፡፡
عربي تفسیرونه:
وَإِن جَٰدَلُوكَ فَقُلِ ٱللَّهُ أَعۡلَمُ بِمَا تَعۡمَلُونَ
ቢከራከሩህም «አላህ የምትሰሩትን ሁሉ ዐዋቂ ነው» በላቸው፡፡
عربي تفسیرونه:
ٱللَّهُ يَحۡكُمُ بَيۡنَكُمۡ يَوۡمَ ٱلۡقِيَٰمَةِ فِيمَا كُنتُمۡ فِيهِ تَخۡتَلِفُونَ
አላህ በትንሣኤ ቀን በዚያ በእርሱ ትለያዩበት በነበራችሁት ሁሉ በመካከላችሁ ይፈርዳል፡፡
عربي تفسیرونه:
أَلَمۡ تَعۡلَمۡ أَنَّ ٱللَّهَ يَعۡلَمُ مَا فِي ٱلسَّمَآءِ وَٱلۡأَرۡضِۚ إِنَّ ذَٰلِكَ فِي كِتَٰبٍۚ إِنَّ ذَٰلِكَ عَلَى ٱللَّهِ يَسِيرٞ
አላህ በሰማይና በምድር ውስጥ ያለን ሁሉ በእርግጥ የሚያውቅ መኾኑን አታውቅምን? ይህ በመጽሐፍ ውስጥ (የተመዘገበ) ነው፡፡ ይህ በአላህ ላይ ገር ነው፡፡
عربي تفسیرونه:
وَيَعۡبُدُونَ مِن دُونِ ٱللَّهِ مَا لَمۡ يُنَزِّلۡ بِهِۦ سُلۡطَٰنٗا وَمَا لَيۡسَ لَهُم بِهِۦ عِلۡمٞۗ وَمَا لِلظَّٰلِمِينَ مِن نَّصِيرٖ
ከአላህ ሌላም በእርሱ ማስረጃን ያላወረደበትን ለእነርሱም በእርሱ ዕውቀት የሌላቸውን ነገር ይግገዛሉ፡፡ ለባዳዮችም ምንም ረዳት የላቸውም፡፡
عربي تفسیرونه:
وَإِذَا تُتۡلَىٰ عَلَيۡهِمۡ ءَايَٰتُنَا بَيِّنَٰتٖ تَعۡرِفُ فِي وُجُوهِ ٱلَّذِينَ كَفَرُواْ ٱلۡمُنكَرَۖ يَكَادُونَ يَسۡطُونَ بِٱلَّذِينَ يَتۡلُونَ عَلَيۡهِمۡ ءَايَٰتِنَاۗ قُلۡ أَفَأُنَبِّئُكُم بِشَرّٖ مِّن ذَٰلِكُمُۚ ٱلنَّارُ وَعَدَهَا ٱللَّهُ ٱلَّذِينَ كَفَرُواْۖ وَبِئۡسَ ٱلۡمَصِيرُ
አንቀጾቻችንም የተብራሩ ኾነው በእነሱ ላይ በሚነበቡ ጊዜ በእነዚያ በካዱት ሰዎች ፊቶች ላይ ጥላቻን ታውቃለህ፡፡ በእነዚያ በእነሱ ላይ አንቀጾቻችንን በሚያነቡት ላይ በኃይል ሊዘልሉባቸው ይቃረባሉ፡፡ «ከዚህ ይልቅ የከፋን ነገር ልንገራችሁን?» በላቸው፡፡ «(እርሱም) እሳት ናት፡፡ አላህ ለእነዚያ ለካዱት ሰዎች ቀጥሯታል፡፡ ምን ትከፋም መመለሻ!»
عربي تفسیرونه:
 
د معناګانو ژباړه سورت: حج
د سورتونو فهرست (لړلیک) د مخ نمبر
 
د قرآن کریم د معناګانو ژباړه - امهري ژباړه - محمد صادق - د ژباړو فهرست (لړلیک)

د شیخ محمد صادق او محمد الثاني حبيب لخوا ژباړل شوې ده. دې ته د رواد الترجمة مرکز تر څارنې لاندې انکشاف ورکړل شوی، او اصلي ژباړې ته د نظرونو څرګندولو، ارزونې، او دوامداره پرمختګ او بیاکتنې لپاره فرصت شتون لري.

بندول