Check out the new design

د قرآن کریم د معناګانو ژباړه - امهري ژباړه - محمد صادق * - د ژباړو فهرست (لړلیک)

XML CSV Excel API
Please review the Terms and Policies

د معناګانو ژباړه سورت: مائده   آیت:
وَلَوۡ أَنَّ أَهۡلَ ٱلۡكِتَٰبِ ءَامَنُواْ وَٱتَّقَوۡاْ لَكَفَّرۡنَا عَنۡهُمۡ سَيِّـَٔاتِهِمۡ وَلَأَدۡخَلۡنَٰهُمۡ جَنَّٰتِ ٱلنَّعِيمِ
የመጽሐፉም ባለቤቶች ባመኑና (ከክህደትም) በተጠነቀቁ ኖሮ ከእነሱ ኃጢኣቶቻቸውን በእርግጥ ባበስንና የመጠቀሚያ ገነቶችንም በእርግጥ ባገባናቸው ነበር፡፡
عربي تفسیرونه:
وَلَوۡ أَنَّهُمۡ أَقَامُواْ ٱلتَّوۡرَىٰةَ وَٱلۡإِنجِيلَ وَمَآ أُنزِلَ إِلَيۡهِم مِّن رَّبِّهِمۡ لَأَكَلُواْ مِن فَوۡقِهِمۡ وَمِن تَحۡتِ أَرۡجُلِهِمۚ مِّنۡهُمۡ أُمَّةٞ مُّقۡتَصِدَةٞۖ وَكَثِيرٞ مِّنۡهُمۡ سَآءَ مَا يَعۡمَلُونَ
እነርሱም ተውራትንና ኢንጂልን ከጌታቸውም ወደ እነሱ የተወረደውን መጽሐፍ ባቋቋሙ (በሠሩበት) ኖሮ ከበላያቸውና ከእግሮቻቸው ሥር በተመገቡ ነበር፡፡ ከእነሱ ውስጥ ትክክለኞች ሕዝቦች አልሉ፡፡ ከእነሱም ብዙዎቹ የሚሠሩት ነገር ከፋ!
عربي تفسیرونه:
۞ يَٰٓأَيُّهَا ٱلرَّسُولُ بَلِّغۡ مَآ أُنزِلَ إِلَيۡكَ مِن رَّبِّكَۖ وَإِن لَّمۡ تَفۡعَلۡ فَمَا بَلَّغۡتَ رِسَالَتَهُۥۚ وَٱللَّهُ يَعۡصِمُكَ مِنَ ٱلنَّاسِۗ إِنَّ ٱللَّهَ لَا يَهۡدِي ٱلۡقَوۡمَ ٱلۡكَٰفِرِينَ
አንተ መልክተኛ ሆይ! ከጌታህ ወዳንተ የተወረደውን አድርስ፡፡ ባትሠራም መልክቱን አላደረስክም፡፡ አላህም ከሰዎች ይጠብቅሃል፡፡ አላህ ከሓዲዎችን ሕዝቦች አያቀናምና፡፡
عربي تفسیرونه:
قُلۡ يَٰٓأَهۡلَ ٱلۡكِتَٰبِ لَسۡتُمۡ عَلَىٰ شَيۡءٍ حَتَّىٰ تُقِيمُواْ ٱلتَّوۡرَىٰةَ وَٱلۡإِنجِيلَ وَمَآ أُنزِلَ إِلَيۡكُم مِّن رَّبِّكُمۡۗ وَلَيَزِيدَنَّ كَثِيرٗا مِّنۡهُم مَّآ أُنزِلَ إِلَيۡكَ مِن رَّبِّكَ طُغۡيَٰنٗا وَكُفۡرٗاۖ فَلَا تَأۡسَ عَلَى ٱلۡقَوۡمِ ٱلۡكَٰفِرِينَ
«እናንተ የመጽሐፉ ባለቤቶች ሆይ! ተውራትንና ኢንጂልን ከጌታችሁም ወደእናንተ የተወረደውን እስከምታቆሙ (እስከምትሠሩባቸው) ድረስ በምንም ላይ አይደላችሁም» በላቸው፡፡ ከጌታህም ወደ አንተ የተወረደው ቁርኣን ከእነሱ ብዙዎቹን ትዕቢትንና ክህደትን በእርግጥ ይጨምርባቸዋል፡፡ በከሓዲያን ሕዝቦችም ላይ አትዘን፡፡
عربي تفسیرونه:
إِنَّ ٱلَّذِينَ ءَامَنُواْ وَٱلَّذِينَ هَادُواْ وَٱلصَّٰبِـُٔونَ وَٱلنَّصَٰرَىٰ مَنۡ ءَامَنَ بِٱللَّهِ وَٱلۡيَوۡمِ ٱلۡأٓخِرِ وَعَمِلَ صَٰلِحٗا فَلَا خَوۡفٌ عَلَيۡهِمۡ وَلَا هُمۡ يَحۡزَنُونَ
እነዚያ ያመኑና እነዚያም አይሁዳውያን የኾኑ፣ ሳቢኣኖችም {1}፣ ክርስቲያኖችም (ከነርሱ) በአላህና በመጨረሻው ቀን ያመነና መልካምን ሥራ የሠራ ሰው በነርሱ ላይ ፍርሃት የለባቸውም፡፡ እነርሱም አያዝኑም፡፡
{1} ሳቢኣህ ማለት እነሱ በተፈጥሯቸው የቀሩ እና የሚከተሉ ሃይማኖት የሌላቸው ሰዎች ናቸው።
عربي تفسیرونه:
لَقَدۡ أَخَذۡنَا مِيثَٰقَ بَنِيٓ إِسۡرَٰٓءِيلَ وَأَرۡسَلۡنَآ إِلَيۡهِمۡ رُسُلٗاۖ كُلَّمَا جَآءَهُمۡ رَسُولُۢ بِمَا لَا تَهۡوَىٰٓ أَنفُسُهُمۡ فَرِيقٗا كَذَّبُواْ وَفَرِيقٗا يَقۡتُلُونَ
የእስራኤልን ልጆች የጠበቀ ቃል ኪዳን በእርግጥ ያዝንባቸው፡፡ ወደ እነሱም መልክተኞችን ላክን፡፡ ነፍሶቻቸው በማትወደው ነገር መልእክተኛ በመጣላቸው ቁጥር ከፊሉን አስተባበሉ፤ ከፊሉንም ይገድላሉ፡፡
عربي تفسیرونه:
 
د معناګانو ژباړه سورت: مائده
د سورتونو فهرست (لړلیک) د مخ نمبر
 
د قرآن کریم د معناګانو ژباړه - امهري ژباړه - محمد صادق - د ژباړو فهرست (لړلیک)

د شیخ محمد صادق او محمد الثاني حبيب لخوا ژباړل شوې ده. دې ته د رواد الترجمة مرکز تر څارنې لاندې انکشاف ورکړل شوی، او اصلي ژباړې ته د نظرونو څرګندولو، ارزونې، او دوامداره پرمختګ او بیاکتنې لپاره فرصت شتون لري.

بندول