Check out the new design

د قرآن کریم د معناګانو ژباړه - امهري ژباړه - د افریقا اکاډمي * - د ژباړو فهرست (لړلیک)

PDF XML CSV Excel API
Please review the Terms and Policies

د معناګانو ژباړه سورت: یوسف   آیت:
فَلَمَّآ أَن جَآءَ ٱلۡبَشِيرُ أَلۡقَىٰهُ عَلَىٰ وَجۡهِهِۦ فَٱرۡتَدَّ بَصِيرٗاۖ قَالَ أَلَمۡ أَقُل لَّكُمۡ إِنِّيٓ أَعۡلَمُ مِنَ ٱللَّهِ مَا لَا تَعۡلَمُونَ
96. አብሳሪዉም በመጣ ጊዜ ቀሚሱን በፊቱ ላይ ጣለው፤ ወዲያዉም የሚያይ ሆነ:: «እኔ ለእናንተ ከአላህ በኩል የማታውቁትን አውቃለሁ አላልኳችሁም ነበርን?» አላቸው።
عربي تفسیرونه:
قَالُواْ يَٰٓأَبَانَا ٱسۡتَغۡفِرۡ لَنَا ذُنُوبَنَآ إِنَّا كُنَّا خَٰطِـِٔينَ
97. «አባታችን ሆይ! ለኃጢያቶቻችን ምሕረትን ለምንልን:: እኛ ጥፋተኞች ነበርንና።» አሉ::
عربي تفسیرونه:
قَالَ سَوۡفَ أَسۡتَغۡفِرُ لَكُمۡ رَبِّيٓۖ إِنَّهُۥ هُوَ ٱلۡغَفُورُ ٱلرَّحِيمُ
98. «ወደ ፊት ለእናንተ ጌታዬን ምሕረትን እለምንላችኋለሁ:: እነሆ እርሱ መሓሪ አዛኝ ነውና።» አላቸው።
عربي تفسیرونه:
فَلَمَّا دَخَلُواْ عَلَىٰ يُوسُفَ ءَاوَىٰٓ إِلَيۡهِ أَبَوَيۡهِ وَقَالَ ٱدۡخُلُواْ مِصۡرَ إِن شَآءَ ٱللَّهُ ءَامِنِينَ
99. በዩሱፍ ላይም በገቡ ጊዜ ወላጆቹን ወደ እርሱ አስጠጋቸው፤ «በአላህም ፈቃድ ጥብቆች ስትሆኑ ሚስርን (ግብጽ) ግቡ።» አላቸው::
عربي تفسیرونه:
وَرَفَعَ أَبَوَيۡهِ عَلَى ٱلۡعَرۡشِ وَخَرُّواْ لَهُۥ سُجَّدٗاۖ وَقَالَ يَٰٓأَبَتِ هَٰذَا تَأۡوِيلُ رُءۡيَٰيَ مِن قَبۡلُ قَدۡ جَعَلَهَا رَبِّي حَقّٗاۖ وَقَدۡ أَحۡسَنَ بِيٓ إِذۡ أَخۡرَجَنِي مِنَ ٱلسِّجۡنِ وَجَآءَ بِكُم مِّنَ ٱلۡبَدۡوِ مِنۢ بَعۡدِ أَن نَّزَغَ ٱلشَّيۡطَٰنُ بَيۡنِي وَبَيۡنَ إِخۡوَتِيٓۚ إِنَّ رَبِّي لَطِيفٞ لِّمَا يَشَآءُۚ إِنَّهُۥ هُوَ ٱلۡعَلِيمُ ٱلۡحَكِيمُ
100. ወላጆቹንም በዙፋኑ ላይ አወጣቸው ለርሱም ሰጋጆች ሆነው ወረዱለት። «አባቴም ሆይ! ይህ ፊት ያየኋት ሕልሜ ፍች ነው፡፡ ጌታዬ በእርግጥ እውነት አደረጋት፡፡ ከወህኒ ቤትም ባወጣኝና ሰይጣንም በእኔና በወንድሞቼ መካከል ካበላሸ በኋላ እናንተን ከገጠር ባመጣችሁ ጊዜ በእርግጥ ለእኔ መልካም ዋለልኝ:: ጌታዬ ለሚሻው ነገር እዝነቱ ረቂቅ ነው:: እነሆ እርሱ አዋቂውና ጥበበኛው ነው።» አለ።
عربي تفسیرونه:
۞ رَبِّ قَدۡ ءَاتَيۡتَنِي مِنَ ٱلۡمُلۡكِ وَعَلَّمۡتَنِي مِن تَأۡوِيلِ ٱلۡأَحَادِيثِۚ فَاطِرَ ٱلسَّمَٰوَٰتِ وَٱلۡأَرۡضِ أَنتَ وَلِيِّۦ فِي ٱلدُّنۡيَا وَٱلۡأٓخِرَةِۖ تَوَفَّنِي مُسۡلِمٗا وَأَلۡحِقۡنِي بِٱلصَّٰلِحِينَ
101. «ጌታዬ ሆይ! ከንግስና በእርግጥ ሰጠኸኝ:: ከህልሞችም ፍች አስተማርከኝ:: የሰማያትና የምድር ፈጣሪ ሆይ! አንተ በቅርቢቱና በመጨረሻይቱ ዓለም ረዳቴ ነህ:: ሙስሊም ሆኜ ግደለኝ:: ወደ መልካም ሰሪዎችም አስጠጋኝ።» አለ።
عربي تفسیرونه:
ذَٰلِكَ مِنۡ أَنۢبَآءِ ٱلۡغَيۡبِ نُوحِيهِ إِلَيۡكَۖ وَمَا كُنتَ لَدَيۡهِمۡ إِذۡ أَجۡمَعُوٓاْ أَمۡرَهُمۡ وَهُمۡ يَمۡكُرُونَ
102. (መልዕክተኛችን ሙሐመድ ሆይ!) ይህ ወደ አንተ የምናወርደው ሲሆን ከሩቅ ወሬዎች ነው:: አንተም እነርሱ በዩሱፍ ላይ የሚያሴሩ ሆነው ነገራቸውን በቆረጡ ጊዜ እነርሱ ዘንድ አብረህ አልነበርክም::
عربي تفسیرونه:
وَمَآ أَكۡثَرُ ٱلنَّاسِ وَلَوۡ حَرَصۡتَ بِمُؤۡمِنِينَ
103. አብዛኛዎቹ ሰዎች ለማመናቸው ብትጓጓም የሚያምኑ አይደሉም::
عربي تفسیرونه:
 
د معناګانو ژباړه سورت: یوسف
د سورتونو فهرست (لړلیک) د مخ نمبر
 
د قرآن کریم د معناګانو ژباړه - امهري ژباړه - د افریقا اکاډمي - د ژباړو فهرست (لړلیک)

محمد زین زهرالدین ژباړلی دی . د افریقا اکاډمۍ لخوا خپره شوې.

بندول