د قرآن کریم د معناګانو ژباړه - الترجمة الأمهرية - زين * - د ژباړو فهرست (لړلیک)


د معناګانو ژباړه سورت: الشعراء   آیت:

ሱረቱ አሽ ሹዐራእ

طسٓمٓ
1. ጣ፤ሲን፤ሚይም::
عربي تفسیرونه:
تِلۡكَ ءَايَٰتُ ٱلۡكِتَٰبِ ٱلۡمُبِينِ
2. እነዚህ ግልጽ የሆነው መጽሀፍ አናቅጽ ናቸው::
عربي تفسیرونه:
لَعَلَّكَ بَٰخِعٞ نَّفۡسَكَ أَلَّا يَكُونُواْ مُؤۡمِنِينَ
3.(መልዕክተኛችን ሙሐመድ ሆይ!) ከሓዲያን አማኞች ባለ መሆናቸው በቁጭት ነፍስህን እንዳታጠፋ ይፈራልሃል (ያሰጋል)::
عربي تفسیرونه:
إِن نَّشَأۡ نُنَزِّلۡ عَلَيۡهِم مِّنَ ٱلسَّمَآءِ ءَايَةٗ فَظَلَّتۡ أَعۡنَٰقُهُمۡ لَهَا خَٰضِعِينَ
4. ብንሻ ኖሮ በእነርሱ ላይ ከሰማይ ተዓምርን እናወርድና አንገቶቻቸው (መሪዎቻቸው) ለእርሷ ተዋራጆች እናደርጋለን::
عربي تفسیرونه:
وَمَا يَأۡتِيهِم مِّن ذِكۡرٖ مِّنَ ٱلرَّحۡمَٰنِ مُحۡدَثٍ إِلَّا كَانُواْ عَنۡهُ مُعۡرِضِينَ
5. ከአር-ረህማን ዘንድ አዲስ የተወረደ ተግሳፅ አይመጣላቸዉም:: ከእርሱ የሚሸሹ ቢሆኑ እንጂ::
عربي تفسیرونه:
فَقَدۡ كَذَّبُواْ فَسَيَأۡتِيهِمۡ أَنۢبَٰٓؤُاْ مَا كَانُواْ بِهِۦ يَسۡتَهۡزِءُونَ
6. በእርግጥም አስተባበሉ:: የዚያም በእርሱ ይሳለቁበት የነበሩት ወሬዎች ፍጻሜ ይመጣባቸዋል::
عربي تفسیرونه:
أَوَلَمۡ يَرَوۡاْ إِلَى ٱلۡأَرۡضِ كَمۡ أَنۢبَتۡنَا فِيهَا مِن كُلِّ زَوۡجٖ كَرِيمٍ
7.ወደ ምድርም በውስጧ ከመልካም በቃይ ጎሳ ብዙን እንዳበቀልን አላዩምን።
عربي تفسیرونه:
إِنَّ فِي ذَٰلِكَ لَأٓيَةٗۖ وَمَا كَانَ أَكۡثَرُهُم مُّؤۡمِنِينَ
8. በዚህ አስደናቂ ምልክት አለበት፤ አብዛኞቻቸዉም ትክክለኛ አማኞች አልነበሩም።
عربي تفسیرونه:
وَإِنَّ رَبَّكَ لَهُوَ ٱلۡعَزِيزُ ٱلرَّحِيمُ
9. (መልዕክተኛችን ሙሐመድ ሆይ!) ጌታህ በትክክል ሁሉን አሸናፊና አዛኝ ነው::
عربي تفسیرونه:
وَإِذۡ نَادَىٰ رَبُّكَ مُوسَىٰٓ أَنِ ٱئۡتِ ٱلۡقَوۡمَ ٱلظَّٰلِمِينَ
10. (መልዕክተኛችን ሙሐመድ ሆይ!) ጌታህም ሙሳን «ወደ እነዚያ በደለኛ ህዝቦች ሂድ።» በማለት በጠራው ጊዜ የሆነውን አስታውስ።
عربي تفسیرونه:
قَوۡمَ فِرۡعَوۡنَۚ أَلَا يَتَّقُونَ
11. «ወደ ፈርዖን ህዝቦች አላህን አይፈሩምን?»
عربي تفسیرونه:
قَالَ رَبِّ إِنِّيٓ أَخَافُ أَن يُكَذِّبُونِ
12. ሙሳም «ጌታዬ ሆይ! እኔ ያስተባብሉኛል ብዬ እፈራለሁ።
عربي تفسیرونه:
وَيَضِيقُ صَدۡرِي وَلَا يَنطَلِقُ لِسَانِي فَأَرۡسِلۡ إِلَىٰ هَٰرُونَ
13. «ልቤም ይጠባል፤ ምላሴም ይንተባተባል። ስለዚህ ወደ ሃሩንም ላክ።
عربي تفسیرونه:
وَلَهُمۡ عَلَيَّ ذَنۢبٞ فَأَخَافُ أَن يَقۡتُلُونِ
14. «በተጨማሪም ለእነርሱም በእኔ ላይ (የደም) ወንጀል አላቸው:: ስለዚህ እንዳይገድሉኝም እፈራለሁ።» አለ።
عربي تفسیرونه:
قَالَ كَلَّاۖ فَٱذۡهَبَا بِـَٔايَٰتِنَآۖ إِنَّا مَعَكُم مُّسۡتَمِعُونَ
15. አላህ አለ: «ተው! አይነኩህም ሁለታችሁም በተአምሮታችን ታጅባችሁ ሂዱ። እኛ ከናንተ ጋር ሁነን ሰሚዎች ነንና።
عربي تفسیرونه:
فَأۡتِيَا فِرۡعَوۡنَ فَقُولَآ إِنَّا رَسُولُ رَبِّ ٱلۡعَٰلَمِينَ
16. «ወደ ፈርዖንም ሂዱና። በሉትም: ‹እኛ የዓለማት ጌታ መልዕክተኞች ነን።
عربي تفسیرونه:
أَنۡ أَرۡسِلۡ مَعَنَا بَنِيٓ إِسۡرَٰٓءِيلَ
17. «‹የኢስራኢልን ልጆችም ከእኛ ጋር ልቀቅልን።›» (በሉት)
عربي تفسیرونه:
قَالَ أَلَمۡ نُرَبِّكَ فِينَا وَلِيدٗا وَلَبِثۡتَ فِينَا مِنۡ عُمُرِكَ سِنِينَ
18. ፈርዖንም አለ፡ «ልጅ ሆንህ በእኛ ውስጥ አላሳደግንህምን? በእኛ ውስጥም ከዕድሜህ ብዙ ዓመታትን አልተቀመጥክምን?
عربي تفسیرونه:
وَفَعَلۡتَ فَعۡلَتَكَ ٱلَّتِي فَعَلۡتَ وَأَنتَ مِنَ ٱلۡكَٰفِرِينَ
19. «ያችን የሰራሃትን ስራስ አልሰራህምን? አንተ ከውለታ ቢሶች ነህ።» (አለ)።
عربي تفسیرونه:
قَالَ فَعَلۡتُهَآ إِذٗا وَأَنَا۠ مِنَ ٱلضَّآلِّينَ
20. ሙሳም አለ፡ «ያን ጊዜ እኔም ከተሳሳቱት ሆኜ ሰራኋት።
عربي تفسیرونه:
فَفَرَرۡتُ مِنكُمۡ لَمَّا خِفۡتُكُمۡ فَوَهَبَ لِي رَبِّي حُكۡمٗا وَجَعَلَنِي مِنَ ٱلۡمُرۡسَلِينَ
21. «በፈራኋችሁም ጊዜ ከናንተ ሸሸሁ። ጌታዬም ለእኔ ጥበብን ሰጠኝ:: ከመልዕክተኞችም አደረገኝ:።
عربي تفسیرونه:
وَتِلۡكَ نِعۡمَةٞ تَمُنُّهَا عَلَيَّ أَنۡ عَبَّدتَّ بَنِيٓ إِسۡرَٰٓءِيلَ
22. «ይህችም የኢስራኢልን ልጆች ባሪያ በማድረግህ በእኔ ላይ የምትመጻድቅባት ጸጋ ናት።»
عربي تفسیرونه:
قَالَ فِرۡعَوۡنُ وَمَا رَبُّ ٱلۡعَٰلَمِينَ
23. ፈርዖን: «ሙሳ ሆይ! ላከኝ የምትለው የዓለማት ጌታ ምንድን ነው?» አለ።
عربي تفسیرونه:
قَالَ رَبُّ ٱلسَّمَٰوَٰتِ وَٱلۡأَرۡضِ وَمَا بَيۡنَهُمَآۖ إِن كُنتُم مُّوقِنِينَ
24. ሙሳ፡- «የሰማያት የምድርና በመካከላቸዉም ያለው ፍጡር ሁሉ ጌታ ነው። የምታረጋግጡ ብትሆኑ ነገሩ ይህ ነው።» አለው።
عربي تفسیرونه:
قَالَ لِمَنۡ حَوۡلَهُۥٓ أَلَا تَسۡتَمِعُونَ
25. ፈርዖንም ዙሪያውን ላሉት ሰዎች: «አትሰሙምን?» አለ።
عربي تفسیرونه:
قَالَ رَبُّكُمۡ وَرَبُّ ءَابَآئِكُمُ ٱلۡأَوَّلِينَ
26. ሙሳ፡- «ጌታችሁና የመጀመሪያዎቹ አባቶቻችሁም ጌታ ነው።» አለ።
عربي تفسیرونه:
قَالَ إِنَّ رَسُولَكُمُ ٱلَّذِيٓ أُرۡسِلَ إِلَيۡكُمۡ لَمَجۡنُونٞ
27. ፈርዖን፡- «ያ ወደ እናንተ የተላከው መልዕክተኛችሁ በእርግጥ ዕብድ ነው።» አለ።
عربي تفسیرونه:
قَالَ رَبُّ ٱلۡمَشۡرِقِ وَٱلۡمَغۡرِبِ وَمَا بَيۡنَهُمَآۖ إِن كُنتُمۡ تَعۡقِلُونَ
28. ሙሳ፡- «(አላህ) የምስራቅና የምዕራብ በመካከላቸዉም ያለው ነገር ሁሉ ጌታ ነው:: ታውቁ እንደሆናችሁ (እመኑበት)።» አለ።
عربي تفسیرونه:
قَالَ لَئِنِ ٱتَّخَذۡتَ إِلَٰهًا غَيۡرِي لَأَجۡعَلَنَّكَ مِنَ ٱلۡمَسۡجُونِينَ
29. ፈርዖን: «ከእኔ ሌላ አምላክን ብትይዝ በእውነቱ ከእስረኞቹ አደርግሃለሁ።» አለ።
عربي تفسیرونه:
قَالَ أَوَلَوۡ جِئۡتُكَ بِشَيۡءٖ مُّبِينٖ
30. ሙሳ፡- «ግልጽ የሆነ አስረጅ ባመጣም እንኳን?» አለው።
عربي تفسیرونه:
قَالَ فَأۡتِ بِهِۦٓ إِن كُنتَ مِنَ ٱلصَّٰدِقِينَ
31. ፊርዓውን «እንግዲያውስ ከእውነተኞች እንደሆንክ አስረጁን አምጣው።» አለ።
عربي تفسیرونه:
فَأَلۡقَىٰ عَصَاهُ فَإِذَا هِيَ ثُعۡبَانٞ مُّبِينٞ
32. በትሩንም ጣለ:: እርሷም ወዲያውኑ ግልጽ እባብ ሆነች::
عربي تفسیرونه:
وَنَزَعَ يَدَهُۥ فَإِذَا هِيَ بَيۡضَآءُ لِلنَّٰظِرِينَ
33 እጁንም አወጣ እርሷም ወዲያውኑ ለተመልካቾች ነጭ (የምታበራ) ሆነች::
عربي تفسیرونه:
قَالَ لِلۡمَلَإِ حَوۡلَهُۥٓ إِنَّ هَٰذَا لَسَٰحِرٌ عَلِيمٞ
34. ፈርዖንም በዙሪያው ላሉት መማክርት አለ: «ይህ በእርግጥ አዋቂ ድግምተኛ ነው።
عربي تفسیرونه:
يُرِيدُ أَن يُخۡرِجَكُم مِّنۡ أَرۡضِكُم بِسِحۡرِهِۦ فَمَاذَا تَأۡمُرُونَ
35. «ከምድራችሁ በድግምት ሊያወጣችሁ ይፈልጋልና ምንን ታዛላችሁ?» አላቸው።
عربي تفسیرونه:
قَالُوٓاْ أَرۡجِهۡ وَأَخَاهُ وَٱبۡعَثۡ فِي ٱلۡمَدَآئِنِ حَٰشِرِينَ
36. እነርሱም አሉ: «እርሱንና ወንድሙን አቆያቸው:: ወደየከተሞቹ ሁሉ ሰብሳቢዎችን ላክ።
عربي تفسیرونه:
يَأۡتُوكَ بِكُلِّ سَحَّارٍ عَلِيمٖ
37. «በጣም አዋቂ ድግምተኞችን ሁሉ ያመጡልሃልና።» አሉ።
عربي تفسیرونه:
فَجُمِعَ ٱلسَّحَرَةُ لِمِيقَٰتِ يَوۡمٖ مَّعۡلُومٖ
38. ድግምተኞችም በታወቀ ቀን ቀጠሮ ተሰበሰቡ::
عربي تفسیرونه:
وَقِيلَ لِلنَّاسِ هَلۡ أَنتُم مُّجۡتَمِعُونَ
39. ለሰዎቹም ተባለ: «እናንተ ተሰብስባችኋልን?
عربي تفسیرونه:
لَعَلَّنَا نَتَّبِعُ ٱلسَّحَرَةَ إِن كَانُواْ هُمُ ٱلۡغَٰلِبِينَ
40. «ድግምተኞቹን እነርሱ አሸናፊዎች ቢሆኑ እንከተል ዘንድ» ተባለ።
عربي تفسیرونه:
فَلَمَّا جَآءَ ٱلسَّحَرَةُ قَالُواْ لِفِرۡعَوۡنَ أَئِنَّ لَنَا لَأَجۡرًا إِن كُنَّا نَحۡنُ ٱلۡغَٰلِبِينَ
41. ድግምተኞቹም በመጡ ጊዜ ለፈርዖን: «እኛ አሸናፊዎች ብንሆን ለእኛ ዋጋ አለን?» አሉት።
عربي تفسیرونه:
قَالَ نَعَمۡ وَإِنَّكُمۡ إِذٗا لَّمِنَ ٱلۡمُقَرَّبِينَ
42. እርሱም( ፈርዖን) «አዎን። እናንተ ያን ጊዜ እኔ ዘንድ ከባለሟሎቹ ትሆናላችሁ።» አላቸው።
عربي تفسیرونه:
قَالَ لَهُم مُّوسَىٰٓ أَلۡقُواْ مَآ أَنتُم مُّلۡقُونَ
43. ሙሳ ለእነርሱ: «የምትጥሉትን ጣሉ።» አላቸው።
عربي تفسیرونه:
فَأَلۡقَوۡاْ حِبَالَهُمۡ وَعِصِيَّهُمۡ وَقَالُواْ بِعِزَّةِ فِرۡعَوۡنَ إِنَّا لَنَحۡنُ ٱلۡغَٰلِبُونَ
44. ገመዶቻቸውንና በትሮቻቸውንም ጣሉ:: «በፈርዖንም ክብር ይሁንብን። እኛ በእርግጥ አሸናፊዎች ነን።» አሉ።
عربي تفسیرونه:
فَأَلۡقَىٰ مُوسَىٰ عَصَاهُ فَإِذَا هِيَ تَلۡقَفُ مَا يَأۡفِكُونَ
45. ሙሳም ብትሩን ጣለ:: ወዲያዉም እርሷ የሚያስመስሉትን ሁሉ ትውጣለች::
عربي تفسیرونه:
فَأُلۡقِيَ ٱلسَّحَرَةُ سَٰجِدِينَ
46. ከዚያም ድግምተኞቹ ሰጋጆች ሆነው ሱጁድ አደረጉ(ወረዱ)።
عربي تفسیرونه:
قَالُوٓاْ ءَامَنَّا بِرَبِّ ٱلۡعَٰلَمِينَ
47. እነርሱም አሉ፡- «በዓለማት ጌታ አመንን።
عربي تفسیرونه:
رَبِّ مُوسَىٰ وَهَٰرُونَ
48. «በሙሳና በሃሩን ጌታ (አመንን)።» (አሉ)
عربي تفسیرونه:
قَالَ ءَامَنتُمۡ لَهُۥ قَبۡلَ أَنۡ ءَاذَنَ لَكُمۡۖ إِنَّهُۥ لَكَبِيرُكُمُ ٱلَّذِي عَلَّمَكُمُ ٱلسِّحۡرَ فَلَسَوۡفَ تَعۡلَمُونَۚ لَأُقَطِّعَنَّ أَيۡدِيَكُمۡ وَأَرۡجُلَكُم مِّنۡ خِلَٰفٖ وَلَأُصَلِّبَنَّكُمۡ أَجۡمَعِينَ
49. ፈርዖንም «ለእናንተ ሳልፈቅድላችሁ በፊት ለእርሱ አመናችሁን? እርሱ ያ ድግምትን ያስተማራችሁ ታላቃችሁ ነው። ወደፊትም በእርግጥ የሚያገኛችሁን ታውቃላችሁ:: እጆቻችሁንና እግሮቻችሁን ቀኝና ግራን (በማናጋት) በማፈራረቅ እቆራርጣችኋለሁ:: ሁላችሁንም እሰቅላችኃለሁ።» አለ።
عربي تفسیرونه:
قَالُواْ لَا ضَيۡرَۖ إِنَّآ إِلَىٰ رَبِّنَا مُنقَلِبُونَ
50. እነርሱም አሉ፡- «ጉዳት የለብንም እኛ ወደ ጌታችን ተመላሾች ነን።
عربي تفسیرونه:
إِنَّا نَطۡمَعُ أَن يَغۡفِرَ لَنَا رَبُّنَا خَطَٰيَٰنَآ أَن كُنَّآ أَوَّلَ ٱلۡمُؤۡمِنِينَ
51. «እኛ የምዕምናን መጀመሪያ በመሆናችን ጌታችን ኃጢአቶቻችንን ለኛ ሊምር እንከጅላለን።»
عربي تفسیرونه:
۞ وَأَوۡحَيۡنَآ إِلَىٰ مُوسَىٰٓ أَنۡ أَسۡرِ بِعِبَادِيٓ إِنَّكُم مُّتَّبَعُونَ
52. ወደ ሙሳም «ባሮቼን ይዘህ ሌሊት ሂድ እናንተ የሚከተሏችሁ ናችሁና።» ስንል ላክን።
عربي تفسیرونه:
فَأَرۡسَلَ فِرۡعَوۡنُ فِي ٱلۡمَدَآئِنِ حَٰشِرِينَ
53. ፈርዖንም በየከተሞቹ ሰብሳቢዎችን (እንዲህ ሲል) ላከ::
عربي تفسیرونه:
إِنَّ هَٰٓؤُلَآءِ لَشِرۡذِمَةٞ قَلِيلُونَ
54. «እነዚህ ጥቂቶቹ ቡድኖች ናቸው።
عربي تفسیرونه:
وَإِنَّهُمۡ لَنَا لَغَآئِظُونَ
55. «እነርሱም ለእኛ አስቆጪዎች ናቸው።
عربي تفسیرونه:
وَإِنَّا لَجَمِيعٌ حَٰذِرُونَ
56. «እኛም ብዙዎች ጥንቁቆች ነን።» አለ።
عربي تفسیرونه:
فَأَخۡرَجۡنَٰهُم مِّن جَنَّٰتٖ وَعُيُونٖ
57. አወጣናቸዉም፤ ከአትክልቶችና ከምንጮች::
عربي تفسیرونه:
وَكُنُوزٖ وَمَقَامٖ كَرِيمٖ
58. ከድልቦችም ከመልካም መቀመጫዎችም፤
عربي تفسیرونه:
كَذَٰلِكَۖ وَأَوۡرَثۡنَٰهَا بَنِيٓ إِسۡرَٰٓءِيلَ
59. ልክ እንደዚሁ ለኢስራኢል ልጆች አወረስናትም::
عربي تفسیرونه:
فَأَتۡبَعُوهُم مُّشۡرِقِينَ
60. ጸሐይዋ ስትወጣም ተከተሏቸው::
عربي تفسیرونه:
فَلَمَّا تَرَٰٓءَا ٱلۡجَمۡعَانِ قَالَ أَصۡحَٰبُ مُوسَىٰٓ إِنَّا لَمُدۡرَكُونَ
61. ሁለቱ ቡድኖችም በተያዩ ጊዜ የሙሳ ጓዶች «እኛ (የፈርዖን ሰዎች) የሚደርሱብን ነን።» አሉ።
عربي تفسیرونه:
قَالَ كَلَّآۖ إِنَّ مَعِيَ رَبِّي سَيَهۡدِينِ
62. ሙሳ «በፍፁም! ጌታዬ ከእኔ ጋር ነው። በእርግጥ ይመራኛል።» አለ።
عربي تفسیرونه:
فَأَوۡحَيۡنَآ إِلَىٰ مُوسَىٰٓ أَنِ ٱضۡرِب بِّعَصَاكَ ٱلۡبَحۡرَۖ فَٱنفَلَقَ فَكَانَ كُلُّ فِرۡقٖ كَٱلطَّوۡدِ ٱلۡعَظِيمِ
63. ወደ ሙሳም «ባህሩን በበትርህ ምታው።» ስንል ላክንበት:: ከዚያ መታውና ተከፈለ፤ ክፍሉም ሁሉ እንደ ታላቅ ጋራ ሆነ::
عربي تفسیرونه:
وَأَزۡلَفۡنَا ثَمَّ ٱلۡأٓخَرِينَ
64. እዚያም ዘንድ ሌሎችን አቀረብን::
عربي تفسیرونه:
وَأَنجَيۡنَا مُوسَىٰ وَمَن مَّعَهُۥٓ أَجۡمَعِينَ
65. ሙሳንና ከእርሱ ጋር ያሉትንም ሰዎች ሁሉንም አዳን::
عربي تفسیرونه:
ثُمَّ أَغۡرَقۡنَا ٱلۡأٓخَرِينَ
66. ከዚያም ሌሎቹን አሰመጥን::
عربي تفسیرونه:
إِنَّ فِي ذَٰلِكَ لَأٓيَةٗۖ وَمَا كَانَ أَكۡثَرُهُم مُّؤۡمِنِينَ
67. በዚህ ውስጥ ታላቅ ተዐምር አለበት፤ አብዛሀኞቻቸዉም ትክክለኛ አማኞች አልነበሩም።
عربي تفسیرونه:
وَإِنَّ رَبَّكَ لَهُوَ ٱلۡعَزِيزُ ٱلرَّحِيمُ
68. (መልዕክተኛችን ሙሐመድ ሆይ!) ጌታህ አላህ እርሱ አሸናፊና አዛኝ ነው::
عربي تفسیرونه:
وَٱتۡلُ عَلَيۡهِمۡ نَبَأَ إِبۡرَٰهِيمَ
69. (መልዕክተኛችን ሙሐመድ ሆይ!) በእነርሱም (በህዝቦችህ) ላይ የኢብራሂምን ወሬ አንብብላቸው::
عربي تفسیرونه:
إِذۡ قَالَ لِأَبِيهِ وَقَوۡمِهِۦ مَا تَعۡبُدُونَ
70. ለአባቱና ለህዝቦቹ «ምንን ትገዛላችሁ?» ባለ ጊዜ።
عربي تفسیرونه:
قَالُواْ نَعۡبُدُ أَصۡنَامٗا فَنَظَلُّ لَهَا عَٰكِفِينَ
71. «ጣኦታትን እንገዛለን:: እርሷንም በመገዛት ላይ እንቆያለን።» አሉ።
عربي تفسیرونه:
قَالَ هَلۡ يَسۡمَعُونَكُمۡ إِذۡ تَدۡعُونَ
72. ኢብራሂም አለ፡- «በጠራችኋቸው ጊዜ ይሰሟችኋልን?
عربي تفسیرونه:
أَوۡ يَنفَعُونَكُمۡ أَوۡ يَضُرُّونَ
73. «ወይስ ይጠቅሟችኋልን? ወይስ ይጎዷችኋልን?»
عربي تفسیرونه:
قَالُواْ بَلۡ وَجَدۡنَآ ءَابَآءَنَا كَذَٰلِكَ يَفۡعَلُونَ
74. «የለም! ነገር ግን አባቶቻችን ልክ እንደዚሁ ሲሰሩ አገኘን(ና እኛም እነርሱን እንከተላለን።») አሉት።
عربي تفسیرونه:
قَالَ أَفَرَءَيۡتُم مَّا كُنتُمۡ تَعۡبُدُونَ
75. እርሱም አለ: «ትገዙት የነበራችሁትን አስተዋላችሁን?
عربي تفسیرونه:
أَنتُمۡ وَءَابَآؤُكُمُ ٱلۡأَقۡدَمُونَ
76. «እናንተም የቀድሞዎቹ አባቶቻችሁም እየተገዛችሁት ያለውን።
عربي تفسیرونه:
فَإِنَّهُمۡ عَدُوّٞ لِّيٓ إِلَّا رَبَّ ٱلۡعَٰلَمِينَ
77. «እነርሱም ጣኦቶቹ ለእኔ ጠላቶች ናቸው:: የዓለማት ጌታ ብቻ ሲቀር:: እርሱማ ወዳጄ ነው።
عربي تفسیرونه:
ٱلَّذِي خَلَقَنِي فَهُوَ يَهۡدِينِ
78. «እርሱ ያ የፈጠረኝ ነው:: እርሱም ይመራኛል።
عربي تفسیرونه:
وَٱلَّذِي هُوَ يُطۡعِمُنِي وَيَسۡقِينِ
79. «ያም እርሱ የሚያበላኝና የሚያጠጣኝም ነው።
عربي تفسیرونه:
وَإِذَا مَرِضۡتُ فَهُوَ يَشۡفِينِ
80. «በታመምኩም ጊዜ እርሱ ያሽረኛል።
عربي تفسیرونه:
وَٱلَّذِي يُمِيتُنِي ثُمَّ يُحۡيِينِ
81. «ያም የሚገድለኝ ከዚያም ህያው የሚያደርገኝ ነው።
عربي تفسیرونه:
وَٱلَّذِيٓ أَطۡمَعُ أَن يَغۡفِرَ لِي خَطِيٓـَٔتِي يَوۡمَ ٱلدِّينِ
82. «ያም በፍርዱ ቀን ኃጢአቴን ሊምርልኝ የምከጅለው ነው።» (አለ)
عربي تفسیرونه:
رَبِّ هَبۡ لِي حُكۡمٗا وَأَلۡحِقۡنِي بِٱلصَّٰلِحِينَ
83. (ኢብራሂምም) «ጌታዬ ሆይ! እውቀትን ስጠኝ በደጋጎቹም ሰዎች አስጠጋኝ።
عربي تفسیرونه:
وَٱجۡعَل لِّي لِسَانَ صِدۡقٖ فِي ٱلۡأٓخِرِينَ
84. «በኋለኞቹም ህዝቦች ውስጥ ለእኔ መልካም ዝናን አድርግልኝ።
عربي تفسیرونه:
وَٱجۡعَلۡنِي مِن وَرَثَةِ جَنَّةِ ٱلنَّعِيمِ
85. «የጸጋይቱን ገነት ከሚወርሱትም ሰዎች አድርገኝ።
عربي تفسیرونه:
وَٱغۡفِرۡ لِأَبِيٓ إِنَّهُۥ كَانَ مِنَ ٱلضَّآلِّينَ
86. «ለአባቴም ኃጢያቱን ማር። እርሱ ከተሳሳቱት ነበርና።
عربي تفسیرونه:
وَلَا تُخۡزِنِي يَوۡمَ يُبۡعَثُونَ
87. «በሚቀሰቀሱበት ቀንም አታዋርደኝ።
عربي تفسیرونه:
يَوۡمَ لَا يَنفَعُ مَالٞ وَلَا بَنُونَ
88. «ገንዘብም ሆነ ልጆች በማይጠቅሙበት ቀን፤
عربي تفسیرونه:
إِلَّا مَنۡ أَتَى ٱللَّهَ بِقَلۡبٖ سَلِيمٖ
89. «ወደ አላህ በንጹህ ልብ የመጣ ቢሆን አንጂ።»
عربي تفسیرونه:
وَأُزۡلِفَتِ ٱلۡجَنَّةُ لِلۡمُتَّقِينَ
90. ገነትም ለጥንቁቆቹ በምትቀረብበት ቀን፤
عربي تفسیرونه:
وَبُرِّزَتِ ٱلۡجَحِيمُ لِلۡغَاوِينَ
91. ገሀነምም ለጠማሞቹ በምትገለጽበት ቀን::
عربي تفسیرونه:
وَقِيلَ لَهُمۡ أَيۡنَ مَا كُنتُمۡ تَعۡبُدُونَ
92. ለእነርሱም «እነዚያ ትገዟቸው የነበራችሁት የት ናቸው?
عربي تفسیرونه:
مِن دُونِ ٱللَّهِ هَلۡ يَنصُرُونَكُمۡ أَوۡ يَنتَصِرُونَ
93. « ከአላህ ሌላ ሲሆኑ (ትገዟቸው የነበራችሁ) ይረዱዋችኋልን? ወይስ ለራሳቸው ይረዳሉን?» በሚባል ቀን።
عربي تفسیرونه:
فَكُبۡكِبُواْ فِيهَا هُمۡ وَٱلۡغَاوُۥنَ
94. በውስጧም እነርሱና ጠማሞች በፊቶቻቸው ተጥለው ይንከባለላሉ::
عربي تفسیرونه:
وَجُنُودُ إِبۡلِيسَ أَجۡمَعُونَ
95 የሰይጣንም ሰራዊቶች መላዉም ይጣላሉ::
عربي تفسیرونه:
قَالُواْ وَهُمۡ فِيهَا يَخۡتَصِمُونَ
96. እነርሱም በርሷ ውስጥ የሚከራከሩ ሆነው ይላሉ:
عربي تفسیرونه:
تَٱللَّهِ إِن كُنَّا لَفِي ضَلَٰلٖ مُّبِينٍ
97. «በአላህ እንምላለን፤ እኛ በግልጽ መሳሳት ውስጥ ነብርን።
عربي تفسیرونه:
إِذۡ نُسَوِّيكُم بِرَبِّ ٱلۡعَٰلَمِينَ
98. «በዓለማት ጌታ ባስተካከልናችሁ ጊዜ።
عربي تفسیرونه:
وَمَآ أَضَلَّنَآ إِلَّا ٱلۡمُجۡرِمُونَ
99. «አመጸኞቹም እንጅ ሌላ አላሳሳተንም።
عربي تفسیرونه:
فَمَا لَنَا مِن شَٰفِعِينَ
100. «ከአማላጆችም ለኛ ምንም የለንም።
عربي تفسیرونه:
وَلَا صَدِيقٍ حَمِيمٖ
101. «አዛኝ ወዳጅም የለንም።
عربي تفسیرونه:
فَلَوۡ أَنَّ لَنَا كَرَّةٗ فَنَكُونَ مِنَ ٱلۡمُؤۡمِنِينَ
102 «ለእኛም አንዲት ጊዜ እንኳን የመመለስ እድል በኖረንና ከትክክለኛ አማኞች በሆን እንመኛለን።» ይላሉ።
عربي تفسیرونه:
إِنَّ فِي ذَٰلِكَ لَأٓيَةٗۖ وَمَا كَانَ أَكۡثَرُهُم مُّؤۡمِنِينَ
103. በዚህ ውስጥ አስደናቂ ግሣጼ አለበት:: አብዛሀኞቻቸዉም ትክክለኛ አማኞች አልነበሩም::
عربي تفسیرونه:
وَإِنَّ رَبَّكَ لَهُوَ ٱلۡعَزِيزُ ٱلرَّحِيمُ
104. (መልዕክተኛችን ሙሐመድ ሆይ!) ጌታህም እርሱ በእርግጥ ሁሉን አሸናፊዉና አዛኙ ነው::
عربي تفسیرونه:
كَذَّبَتۡ قَوۡمُ نُوحٍ ٱلۡمُرۡسَلِينَ
105. የኑህ ህዝቦች መልዕክተኞችን አስተባበሉ::
عربي تفسیرونه:
إِذۡ قَالَ لَهُمۡ أَخُوهُمۡ نُوحٌ أَلَا تَتَّقُونَ
106. ወንድማቸው ኑህ ለእነርሱ ባላቸው ጊዜ፡ «አትጠነቀቁምን?
عربي تفسیرونه:
إِنِّي لَكُمۡ رَسُولٌ أَمِينٞ
107. «እኔ ለእናንተ ታማኝ መልዕክተኛ ነኝ።
عربي تفسیرونه:
فَٱتَّقُواْ ٱللَّهَ وَأَطِيعُونِ
108. «አላህንም ፍሩ ታዘዙኝም።
عربي تفسیرونه:
وَمَآ أَسۡـَٔلُكُمۡ عَلَيۡهِ مِنۡ أَجۡرٍۖ إِنۡ أَجۡرِيَ إِلَّا عَلَىٰ رَبِّ ٱلۡعَٰلَمِينَ
109. «በእርሱም ላይ ምንም ዋጋ አልጠይቃችሁም:: ዋጋዬ ከዓለማት ጌታ ብቻ እንጂ በሌላ ላይ አይደለም።
عربي تفسیرونه:
فَٱتَّقُواْ ٱللَّهَ وَأَطِيعُونِ
110. «አላህንም ፍሩ። ታዘዙኝም።»
عربي تفسیرونه:
۞ قَالُوٓاْ أَنُؤۡمِنُ لَكَ وَٱتَّبَعَكَ ٱلۡأَرۡذَلُونَ
111. እነርሱም «ወራዶቹ ብቻ የተከተሉህ ሆነህ ላንተ እናምናለን?» አሉት።
عربي تفسیرونه:
قَالَ وَمَا عِلۡمِي بِمَا كَانُواْ يَعۡمَلُونَ
112. እርሱም አላቸው፡- «ይሰሩት በነበሩት ነገር ምን ዕውቀት አለኝና?
عربي تفسیرونه:
إِنۡ حِسَابُهُمۡ إِلَّا عَلَىٰ رَبِّيۖ لَوۡ تَشۡعُرُونَ
113. «ምርመራቸው በጌታዬ ላይ እንጅ በሌላ ላይ አይደለም:: ብታውቁ ኖሮ ይህንን ትረዱት ነበር።
عربي تفسیرونه:
وَمَآ أَنَا۠ بِطَارِدِ ٱلۡمُؤۡمِنِينَ
114. «እኔ አማኞችን አባራሪ አይደለሁም።
عربي تفسیرونه:
إِنۡ أَنَا۠ إِلَّا نَذِيرٞ مُّبِينٞ
115. «እኔም እኮ ግልጽ አስፈራሪ እንጂ ሌላ አይደለሁም።» (አለ)
عربي تفسیرونه:
قَالُواْ لَئِن لَّمۡ تَنتَهِ يَٰنُوحُ لَتَكُونَنَّ مِنَ ٱلۡمَرۡجُومِينَ
116. «ኑህ ሆይ! ከምትለው ባትከለከል በእርግጥ ከሚወገሩት ትሆናለህ።» አሉት።
عربي تفسیرونه:
قَالَ رَبِّ إِنَّ قَوۡمِي كَذَّبُونِ
117. እርሱም አለ፡- «ጌታየ ሆይ! ህዝቦቼ አስተባበሉኝ።
عربي تفسیرونه:
فَٱفۡتَحۡ بَيۡنِي وَبَيۡنَهُمۡ فَتۡحٗا وَنَجِّنِي وَمَن مَّعِيَ مِنَ ٱلۡمُؤۡمِنِينَ
118. «በእኔና በእነርሱም መካከል ተገቢ ፍርድን ፍረድ:: ከእነርሱ አድነኝም:: ከእኔ ጋር ያሉትን አማኞችም አድን።»
عربي تفسیرونه:
فَأَنجَيۡنَٰهُ وَمَن مَّعَهُۥ فِي ٱلۡفُلۡكِ ٱلۡمَشۡحُونِ
119. እርሱንም ሆነ ከእርሱ ጋር ያሉትን ሁሉ በተሞላው መርከብ ውስጥ አዳንን::
عربي تفسیرونه:
ثُمَّ أَغۡرَقۡنَا بَعۡدُ ٱلۡبَاقِينَ
120. ከዚያም በኋላ ቀሪዎቹን አሰመጥን።
عربي تفسیرونه:
إِنَّ فِي ذَٰلِكَ لَأٓيَةٗۖ وَمَا كَانَ أَكۡثَرُهُم مُّؤۡمِنِينَ
121. በዚህ ውስጥ ታላቅ ግሣጼ አለበት፤ አብዛሀኞቻቸዉም ትክክለኛ አማኞች አልነበሩም::
عربي تفسیرونه:
وَإِنَّ رَبَّكَ لَهُوَ ٱلۡعَزِيزُ ٱلرَّحِيمُ
122. ጌታህም እርሱ በእርግጥ ሁሉን አሸናፊዉና አዛኙ ነው::
عربي تفسیرونه:
كَذَّبَتۡ عَادٌ ٱلۡمُرۡسَلِينَ
123. ዓድ መልዕክተኞችን አስተባበለች፤
عربي تفسیرونه:
إِذۡ قَالَ لَهُمۡ أَخُوهُمۡ هُودٌ أَلَا تَتَّقُونَ
124. ወንድማቸው ሁድ ለእነርሱ ባላቸው ጊዜ: «አትጠነቀቁምን?
عربي تفسیرونه:
إِنِّي لَكُمۡ رَسُولٌ أَمِينٞ
125. «እኔ ለእናንተ ታማኝ መልዕክተኛ ነኝ።
عربي تفسیرونه:
فَٱتَّقُواْ ٱللَّهَ وَأَطِيعُونِ
126. «አላህን ብቻ ፍሩ ታዘዙኝም።
عربي تفسیرونه:
وَمَآ أَسۡـَٔلُكُمۡ عَلَيۡهِ مِنۡ أَجۡرٍۖ إِنۡ أَجۡرِيَ إِلَّا عَلَىٰ رَبِّ ٱلۡعَٰلَمِينَ
127. «በእርሱም ላይ ምንም ዋጋ አለምናችሁም:: ዋጋዬ በዓለማት ጌታ ላይ ብቻ እንጅ በሌላ ላይ አይደለም።
عربي تفسیرونه:
أَتَبۡنُونَ بِكُلِّ رِيعٍ ءَايَةٗ تَعۡبَثُونَ
128. «የምትጫወቱ ሆናችሁ በከፍተኛ ስፍራ ሁሉ ላይ ምልክት ትገነባላችሁን?
عربي تفسیرونه:
وَتَتَّخِذُونَ مَصَانِعَ لَعَلَّكُمۡ تَخۡلُدُونَ
129. «የውሃ ማጠራቀሚያዎችንና ህንፃዎችንም ለዘላለም መኖርን የምትከጅሉ ሆናችሁ ትሰራላችሁን?
عربي تفسیرونه:
وَإِذَا بَطَشۡتُم بَطَشۡتُمۡ جَبَّارِينَ
130. «በቀጣችሁም ጊዜ ጨካኞች ሆናችሁ ትቀጣላችሁን?
عربي تفسیرونه:
فَٱتَّقُواْ ٱللَّهَ وَأَطِيعُونِ
131. «አላህንም ፍሩ። ታዘዙኝም።
عربي تفسیرونه:
وَٱتَّقُواْ ٱلَّذِيٓ أَمَدَّكُم بِمَا تَعۡلَمُونَ
132. «ያንንም በምታውቁት ጸጋ ያጣቀማችሁን ጌታን (አላህን) ፍሩ።
عربي تفسیرونه:
أَمَدَّكُم بِأَنۡعَٰمٖ وَبَنِينَ
133. «በእንስሳዎችና በልጆችም ያጣቀማችሁ።
عربي تفسیرونه:
وَجَنَّٰتٖ وَعُيُونٍ
134. «በአትክልቶችና በምንጮችም ያጣቀማችሁን ጌታን (አላህን) ፍሩ።
عربي تفسیرونه:
إِنِّيٓ أَخَافُ عَلَيۡكُمۡ عَذَابَ يَوۡمٍ عَظِيمٖ
135. «እኔ በእናንተ ላይ የታላቅን ቀን ቅጣት እፈራለሁና።»
عربي تفسیرونه:
قَالُواْ سَوَآءٌ عَلَيۡنَآ أَوَعَظۡتَ أَمۡ لَمۡ تَكُن مِّنَ ٱلۡوَٰعِظِينَ
136. እነርሱም አሉ: «ብትገስጽም ወይም ከገሳጮች ባትሆንም በእኛ ላይ እኩል ነው።
عربي تفسیرونه:
إِنۡ هَٰذَآ إِلَّا خُلُقُ ٱلۡأَوَّلِينَ
137. «(ያለንበትን አንለቅም)። ይህ የፊተኞቹ ሰዎች መንገድ እንጂ ሌላ አይደለም።
عربي تفسیرونه:
وَمَا نَحۡنُ بِمُعَذَّبِينَ
138. «እኛም የምንቀጣ አይደለንም።» አሉ።
عربي تفسیرونه:
فَكَذَّبُوهُ فَأَهۡلَكۡنَٰهُمۡۚ إِنَّ فِي ذَٰلِكَ لَأٓيَةٗۖ وَمَا كَانَ أَكۡثَرُهُم مُّؤۡمِنِينَ
139. አስተባበሉትም፤ አጠፋናቸዉም፤ በዚህም ውስጥ እርግጠኛ ግሣጼም አለበት:: አብዛኞቻቸዉም ምዕምናን አልነበሩም::
عربي تفسیرونه:
وَإِنَّ رَبَّكَ لَهُوَ ٱلۡعَزِيزُ ٱلرَّحِيمُ
140. (መልዕክተኛችን ሙሐመድ ሆይ!) ጌታህም እርሱ በእርግጥ አሸናፊውና አዛኙ ነው::
عربي تفسیرونه:
كَذَّبَتۡ ثَمُودُ ٱلۡمُرۡسَلِينَ
141. የሰሙድ ህዝቦች መልዕክተኞችን አስተባበሉ::
عربي تفسیرونه:
إِذۡ قَالَ لَهُمۡ أَخُوهُمۡ صَٰلِحٌ أَلَا تَتَّقُونَ
142. ወንድማቸው ሷሊህ ለእነርሱ ባላቸው ጊዜ: «አትጠነቀቁምን?
عربي تفسیرونه:
إِنِّي لَكُمۡ رَسُولٌ أَمِينٞ
143. «እኔ ለእናንተ ታማኝ መልዕክተኛ ነኝ።
عربي تفسیرونه:
فَٱتَّقُواْ ٱللَّهَ وَأَطِيعُونِ
144. «አላህን ፍሩ ታዘዙኝም።
عربي تفسیرونه:
وَمَآ أَسۡـَٔلُكُمۡ عَلَيۡهِ مِنۡ أَجۡرٍۖ إِنۡ أَجۡرِيَ إِلَّا عَلَىٰ رَبِّ ٱلۡعَٰلَمِينَ
145. «በእርሱም ላይ ምንም ዋጋ አልለምናችሁም:: ዋጋዬ በዓለማት ጌታ ላይ ብቻ እንጂ በሌላ ላይ አይደለም።
عربي تفسیرونه:
أَتُتۡرَكُونَ فِي مَا هَٰهُنَآ ءَامِنِينَ
146. «በዚያ እዚህ ባለው ጸጋ ውስጥ የረካችሁ ሆናችሁ ትቀራላችሁን?
عربي تفسیرونه:
فِي جَنَّٰتٖ وَعُيُونٖ
147. «በአትክልቶችና በምንጮች ውስጥ
عربي تفسیرونه:
وَزُرُوعٖ وَنَخۡلٖ طَلۡعُهَا هَضِيمٞ
148. «በአዝመራዎችም ፍሬዋ የበሰለ በሆነች ዘንባባም ውስጥ ትቀራላችሁን?
عربي تفسیرونه:
وَتَنۡحِتُونَ مِنَ ٱلۡجِبَالِ بُيُوتٗا فَٰرِهِينَ
149. «ብልሆች ሆናችሁ ከጋራዎች ቤቶችንም ትጠርባላችሁ።
عربي تفسیرونه:
فَٱتَّقُواْ ٱللَّهَ وَأَطِيعُونِ
150. «አላህንም ፍሩ፤ ታዘዙኝም።
عربي تفسیرونه:
وَلَا تُطِيعُوٓاْ أَمۡرَ ٱلۡمُسۡرِفِينَ
151. «የወሰን አላፊዎችንም ትዕዛዝ አትከተሉ።
عربي تفسیرونه:
ٱلَّذِينَ يُفۡسِدُونَ فِي ٱلۡأَرۡضِ وَلَا يُصۡلِحُونَ
152. «የእነዚያን በምድር ላይ የሚያጠፉትንና የማያበጁትን (ትዕዛዝ አትከተሉ)።» (አለ)
عربي تفسیرونه:
قَالُوٓاْ إِنَّمَآ أَنتَ مِنَ ٱلۡمُسَحَّرِينَ
153. እነርሱም አሉ: «አንተ በብዙ ከተደገመባቸው ሰዎች ብቻ ነህ።
عربي تفسیرونه:
مَآ أَنتَ إِلَّا بَشَرٞ مِّثۡلُنَا فَأۡتِ بِـَٔايَةٍ إِن كُنتَ مِنَ ٱلصَّٰدِقِينَ
154. «አንተ ብጤያችን ሰው እንጂ ሌላ አይደለህም። ከእውነተኞችም ከሆንክ ተዐምርን አምጣ።» (አሉ)
عربي تفسیرونه:
قَالَ هَٰذِهِۦ نَاقَةٞ لَّهَا شِرۡبٞ وَلَكُمۡ شِرۡبُ يَوۡمٖ مَّعۡلُومٖ
155. እርሱም አለ: «ይህች ግመል ናት:: ለእርሷ የመጠጥ ፋንታ አላት:: ለእናንተም የታወቀ ቀን ፋንታ አላችሁ፤
عربي تفسیرونه:
وَلَا تَمَسُّوهَا بِسُوٓءٖ فَيَأۡخُذَكُمۡ عَذَابُ يَوۡمٍ عَظِيمٖ
156. «በክፉም አትንኳት የታላቅ ቀን ቅጣት ይይዛችኋልና።»
عربي تفسیرونه:
فَعَقَرُوهَا فَأَصۡبَحُواْ نَٰدِمِينَ
157. ወጓትም:: ወዲያው ተጸፃቾች ሆነው አነጉ::
عربي تفسیرونه:
فَأَخَذَهُمُ ٱلۡعَذَابُۚ إِنَّ فِي ذَٰلِكَ لَأٓيَةٗۖ وَمَا كَانَ أَكۡثَرُهُم مُّؤۡمِنِينَ
158. ቅጣትም ያዛቸው በዚህም ውስጥ አያሌ ግሣጼ አለበት:: አብዛኞቻቸዉም አማኞች አልነበሩም::
عربي تفسیرونه:
وَإِنَّ رَبَّكَ لَهُوَ ٱلۡعَزِيزُ ٱلرَّحِيمُ
159. ጌታህም እርሱ በእርግጥ ሁሉን አሸናፊውና አዛኙ ነው።
عربي تفسیرونه:
كَذَّبَتۡ قَوۡمُ لُوطٍ ٱلۡمُرۡسَلِينَ
160. የሉጥ ህዝቦች መልዕክተኞችን አስተባበሉ::
عربي تفسیرونه:
إِذۡ قَالَ لَهُمۡ أَخُوهُمۡ لُوطٌ أَلَا تَتَّقُونَ
161. ወንድማቸው ሉጥ ለእነርሱ ባለ ጊዜ: «አትጠነቀቁምን?
عربي تفسیرونه:
إِنِّي لَكُمۡ رَسُولٌ أَمِينٞ
162. «እኔ ለእናንተ ታማኝ መልዕክተኛ ነኝ።
عربي تفسیرونه:
فَٱتَّقُواْ ٱللَّهَ وَأَطِيعُونِ
163. «አላህንም ፍሩ ታዘዙኝም።
عربي تفسیرونه:
وَمَآ أَسۡـَٔلُكُمۡ عَلَيۡهِ مِنۡ أَجۡرٍۖ إِنۡ أَجۡرِيَ إِلَّا عَلَىٰ رَبِّ ٱلۡعَٰلَمِينَ
164. «በእርሱም ላይ ምንም ዋጋ አለምናችሁም:: ዋጋዬ በዓለማት ጌታ ላይ እንጅ በሌላ ላይ አይደለም::
عربي تفسیرونه:
أَتَأۡتُونَ ٱلذُّكۡرَانَ مِنَ ٱلۡعَٰلَمِينَ
165. «ከዓለማት ሰዎች መካከል የተለየ ወንዶችን ትገናኛላችሁን?
عربي تفسیرونه:
وَتَذَرُونَ مَا خَلَقَ لَكُمۡ رَبُّكُم مِّنۡ أَزۡوَٰجِكُمۚ بَلۡ أَنتُمۡ قَوۡمٌ عَادُونَ
166. «ከሚስቶቻችሁም ጌታችሁ ለእናንተ የፈጠረላችሁን ትተዋላችሁን? በእውነት እናንተ ወሰን አላፊዎች ህዝቦች ናችሁ።» (አለ)
عربي تفسیرونه:
قَالُواْ لَئِن لَّمۡ تَنتَهِ يَٰلُوطُ لَتَكُونَنَّ مِنَ ٱلۡمُخۡرَجِينَ
167. እነርሱም አሉ: «ሉጥ ሆይ! ከዚህ ነገርህ ባትከለከል በእርግጥ በሀይል ከአገር ከሚወጡት ትሆናለህ።»
عربي تفسیرونه:
قَالَ إِنِّي لِعَمَلِكُم مِّنَ ٱلۡقَالِينَ
168. እርሱም አለ: «እኔ ስራችሁን ከሚጠሉት ሰዎች አንዱ ነኝ።
عربي تفسیرونه:
رَبِّ نَجِّنِي وَأَهۡلِي مِمَّا يَعۡمَلُونَ
169. «ጌታዬ ሆይ! እኔንም ሆነ ቤተሰቦቼን እኒህ ህዝቦች ከሚሰሩት ስራ ቅጣት አድነን።»
عربي تفسیرونه:
فَنَجَّيۡنَٰهُ وَأَهۡلَهُۥٓ أَجۡمَعِينَ
170. እርሱንም ሆነ ቤተሰቦቹንም በጠቅላላ አዳንናቸው።
عربي تفسیرونه:
إِلَّا عَجُوزٗا فِي ٱلۡغَٰبِرِينَ
171. በቀሪዎቹ ውስጥ የሆነች አሮጊት ስተቀር (እርሷ ግን ጠፋች)::
عربي تفسیرونه:
ثُمَّ دَمَّرۡنَا ٱلۡأٓخَرِينَ
172. ከዚያም ሌሎቹን አጠፋን።
عربي تفسیرونه:
وَأَمۡطَرۡنَا عَلَيۡهِم مَّطَرٗاۖ فَسَآءَ مَطَرُ ٱلۡمُنذَرِينَ
173. በእነርሱም ላይ የድንጋይን ዝናብን አዘነብንባቸው:: የተስፋራሪዎችም ዝናብ ከፋ::
عربي تفسیرونه:
إِنَّ فِي ذَٰلِكَ لَأٓيَةٗۖ وَمَا كَانَ أَكۡثَرُهُم مُّؤۡمِنِينَ
174. በዚህ ውስጥ አስደናቂ ተዐምር አለበት:: አብዛኞቻቸዉም ምዕምናን አልነበሩም::
عربي تفسیرونه:
وَإِنَّ رَبَّكَ لَهُوَ ٱلۡعَزِيزُ ٱلرَّحِيمُ
175. ጌታህ እርሱ አሸናፊውና አዛኙ ነው።
عربي تفسیرونه:
كَذَّبَ أَصۡحَٰبُ لۡـَٔيۡكَةِ ٱلۡمُرۡسَلِينَ
176. የአይካ ሰዎች መልዕክተኞችን አስተባበሉ::
عربي تفسیرونه:
إِذۡ قَالَ لَهُمۡ شُعَيۡبٌ أَلَا تَتَّقُونَ
177. ወንድማቸው ሹዐይብ ለእነርሱ ባላቸው ጊዜ: «አትጠነቀቁምን?
عربي تفسیرونه:
إِنِّي لَكُمۡ رَسُولٌ أَمِينٞ
178. «እኔ ለእናንተ ታማኝ መልዕክተኛ ነኝ።
عربي تفسیرونه:
فَٱتَّقُواْ ٱللَّهَ وَأَطِيعُونِ
179. «አላህን ፍሩ፤ ታዘዙኝም።
عربي تفسیرونه:
وَمَآ أَسۡـَٔلُكُمۡ عَلَيۡهِ مِنۡ أَجۡرٍۖ إِنۡ أَجۡرِيَ إِلَّا عَلَىٰ رَبِّ ٱلۡعَٰلَمِينَ
180. «በእርሱም ላይ ምንም ዋጋ አልጠይቃችሁም፤ ዋጋዬ በዓለማት ጌታ ላይ እንጂ በሌላ ላይ አይደለም።
عربي تفسیرونه:
۞ أَوۡفُواْ ٱلۡكَيۡلَ وَلَا تَكُونُواْ مِنَ ٱلۡمُخۡسِرِينَ
181. «ስፍርንም ሙሉ:: ከአጎዳዮችም አትሁኑ።
عربي تفسیرونه:
وَزِنُواْ بِٱلۡقِسۡطَاسِ ٱلۡمُسۡتَقِيمِ
182. «በትክክለኛ ሚዛንም መዝኑ።
عربي تفسیرونه:
وَلَا تَبۡخَسُواْ ٱلنَّاسَ أَشۡيَآءَهُمۡ وَلَا تَعۡثَوۡاْ فِي ٱلۡأَرۡضِ مُفۡسِدِينَ
183. «ሰዎችንም ነገሮቻቸውን አታጉድሉባቸው:: በምድርም ላይ አጥፊዎች ሆናችሁ አታበላሹ።
عربي تفسیرونه:
وَٱتَّقُواْ ٱلَّذِي خَلَقَكُمۡ وَٱلۡجِبِلَّةَ ٱلۡأَوَّلِينَ
184. «ያንንም የፈጠራችሁን የቀድሞዎቹንም ፍጡሮች የፈጠረውን ፍሩ።» (ባለ ጊዜ የሆነውን አስታውስ)
عربي تفسیرونه:
قَالُوٓاْ إِنَّمَآ أَنتَ مِنَ ٱلۡمُسَحَّرِينَ
185. እነርሱም አሉ: «ሹዓይብ ሆይ! አንተ በብዛት ከተደገመባቸው ሰዎች አንዱ ነህ።
عربي تفسیرونه:
وَمَآ أَنتَ إِلَّا بَشَرٞ مِّثۡلُنَا وَإِن نَّظُنُّكَ لَمِنَ ٱلۡكَٰذِبِينَ
186. «አንተም ብጤያችን ሰው እንጂ ሌላ አይደለህም:: እነሆ ከውሸታሞች ነህ ብለን እንጠረጥርሃለን፤
عربي تفسیرونه:
فَأَسۡقِطۡ عَلَيۡنَا كِسَفٗا مِّنَ ٱلسَّمَآءِ إِن كُنتَ مِنَ ٱلصَّٰدِقِينَ
187. «ከእውነተኞችም እንደሆንክ በእኛ ላይ ከሰማይ ቁራጭን ጣልብን።» (አሉ)
عربي تفسیرونه:
قَالَ رَبِّيٓ أَعۡلَمُ بِمَا تَعۡمَلُونَ
188. «ጌታዬ የምትሰሩትን ሁሉ አዋቂ ነው።» አላቸው።
عربي تفسیرونه:
فَكَذَّبُوهُ فَأَخَذَهُمۡ عَذَابُ يَوۡمِ ٱلظُّلَّةِۚ إِنَّهُۥ كَانَ عَذَابَ يَوۡمٍ عَظِيمٍ
189. አስተባበሉትም የጥላይቱ ቀን ቅጣትም ያዛቸው፤ እርሱ የከባድ ቀን ቅጣት ነበርና::
عربي تفسیرونه:
إِنَّ فِي ذَٰلِكَ لَأٓيَةٗۖ وَمَا كَانَ أَكۡثَرُهُم مُّؤۡمِنِينَ
190. በዚህ ውስጥ አስደናቂ ተዐምር አለበት:: አብዛዛቻቸዉም አማኞች አልነበሩም::
عربي تفسیرونه:
وَإِنَّ رَبَّكَ لَهُوَ ٱلۡعَزِيزُ ٱلرَّحِيمُ
191. (መልዕክተኛችን ሙሐመድ ሆይ!) ጌታህም እርሱ በእርግጥ አሸናፊዉንና አዛኙ ነው::
عربي تفسیرونه:
وَإِنَّهُۥ لَتَنزِيلُ رَبِّ ٱلۡعَٰلَمِينَ
192. (መልዕክተኛችን ሙሐመድ ሆይ!) እርሱም (ቁርኣን) በእርግጥ ከዓለማት ጌታ የተወረደ ነው::
عربي تفسیرونه:
نَزَلَ بِهِ ٱلرُّوحُ ٱلۡأَمِينُ
193. እርሱን ታማኙ መንፈስ ጂብሪል አወረደው::
عربي تفسیرونه:
عَلَىٰ قَلۡبِكَ لِتَكُونَ مِنَ ٱلۡمُنذِرِينَ
194. ከአስፈራሪዎች ነብያት ትሆን ዘንድ በልብህ ላይ አወረደው፤
عربي تفسیرونه:
بِلِسَانٍ عَرَبِيّٖ مُّبِينٖ
195. ግልጽ በሆነ ዐረብኛ ቋንቋ፤ (አወረደው)
عربي تفسیرونه:
وَإِنَّهُۥ لَفِي زُبُرِ ٱلۡأَوَّلِينَ
196. እርሱም (ቁርኣን) በቀድሞዎቹ መጽሐፍት ውስጥ የተወሳ ነው::
عربي تفسیرونه:
أَوَلَمۡ يَكُن لَّهُمۡ ءَايَةً أَن يَعۡلَمَهُۥ عُلَمَٰٓؤُاْ بَنِيٓ إِسۡرَٰٓءِيلَ
197. የኢስራኢል ልጆች ሊቃውንት የሚያውቁት መሆኑ ለእነርሱ (ለመካ ከሓዲያን) ምልክት አይሆናቸዉም?
عربي تفسیرونه:
وَلَوۡ نَزَّلۡنَٰهُ عَلَىٰ بَعۡضِ ٱلۡأَعۡجَمِينَ
198. ከአዕጀሞች ባንዱ ላይ ባወረድነዉም ኖሮ
عربي تفسیرونه:
فَقَرَأَهُۥ عَلَيۡهِم مَّا كَانُواْ بِهِۦ مُؤۡمِنِينَ
199. በእነርሱ ላይ ቢያነበዉም በእርሱ አማኞች አይሆኑም ነበር::
عربي تفسیرونه:
كَذَٰلِكَ سَلَكۡنَٰهُ فِي قُلُوبِ ٱلۡمُجۡرِمِينَ
200. እንድዚሁ ማስተባበልን በተንኮለኞች ልቦች ውስጥ አስገባነው::
عربي تفسیرونه:
لَا يُؤۡمِنُونَ بِهِۦ حَتَّىٰ يَرَوُاْ ٱلۡعَذَابَ ٱلۡأَلِيمَ
201. አሳማሚ ቅጣትን እስከሚያዩ ድረስ በእርሱ አያምኑም::
عربي تفسیرونه:
فَيَأۡتِيَهُم بَغۡتَةٗ وَهُمۡ لَا يَشۡعُرُونَ
202. እነርሱ የማያውቁ ሲሆኑ ቅጣቱ ድንገት እስከሚመጣባቸዉም ድረስ (አያምኑም)::
عربي تفسیرونه:
فَيَقُولُواْ هَلۡ نَحۡنُ مُنظَرُونَ
203. በመጣባቸው ጊዜ: «እኛ የምንቆይ ነን?» እስከሚሉም (አያምኑም)።
عربي تفسیرونه:
أَفَبِعَذَابِنَا يَسۡتَعۡجِلُونَ
204. በቅጣታችን ያቻኩላሉን?
عربي تفسیرونه:
أَفَرَءَيۡتَ إِن مَّتَّعۡنَٰهُمۡ سِنِينَ
205. (መልዕክተኛችን ሙሐመድ ሆይ! ) አየህን? ብዙ ዓመታትን ብናጣቅማቸው::
عربي تفسیرونه:
ثُمَّ جَآءَهُم مَّا كَانُواْ يُوعَدُونَ
206. ከዚያም ያ ይስፈራሩበት የነበሩት ቢመጣባቸው
عربي تفسیرونه:
مَآ أَغۡنَىٰ عَنۡهُم مَّا كَانُواْ يُمَتَّعُونَ
207. ይጣቀሙበት የነበሩት ሁሉ ከእነርሱ ምንም አያብቃቃቸዉም::
عربي تفسیرونه:
وَمَآ أَهۡلَكۡنَا مِن قَرۡيَةٍ إِلَّا لَهَا مُنذِرُونَ
208. አንዲትንም ከተማ ለእርሷ አስፈራሪዎች ያሏት (እና ያስተባበለች) ሆና እንጂ አላጠፋንም::
عربي تفسیرونه:
ذِكۡرَىٰ وَمَا كُنَّا ظَٰلِمِينَ
209. ይህች ግሣጼ ናት:: በዳዮችም አልነበርንም::
عربي تفسیرونه:
وَمَا تَنَزَّلَتۡ بِهِ ٱلشَّيَٰطِينُ
210. ሰይጣናትም እርሱን ቁርኣንን አላወረዱትም::
عربي تفسیرونه:
وَمَا يَنۢبَغِي لَهُمۡ وَمَا يَسۡتَطِيعُونَ
211. ለእነርሱም አይገባቸዉም፤ አይችሉምም::
عربي تفسیرونه:
إِنَّهُمۡ عَنِ ٱلسَّمۡعِ لَمَعۡزُولُونَ
212. እነርሱ የመላዕክትን ንግግር ከመስማት የተከለከሉ ናቸው።
عربي تفسیرونه:
فَلَا تَدۡعُ مَعَ ٱللَّهِ إِلَٰهًا ءَاخَرَ فَتَكُونَ مِنَ ٱلۡمُعَذَّبِينَ
213. (መልዕክተኛችን ሙሐመድ ሆይ!) ከአላህም ጋር ሌላን አምላክ አትገዛ:: ከሚቀጡት ትሆናለህና::
عربي تفسیرونه:
وَأَنذِرۡ عَشِيرَتَكَ ٱلۡأَقۡرَبِينَ
214. (መልዕክተኛችን ሙሐመድ ሆይ!) ቅርቦች ዘመዶችህንም አስጠንቅቅ::
عربي تفسیرونه:
وَٱخۡفِضۡ جَنَاحَكَ لِمَنِ ٱتَّبَعَكَ مِنَ ٱلۡمُؤۡمِنِينَ
215. (ሙሐመድ ሆይ!) ከምዕምናንም ለተከተሉህ ሰዎች ክንፍህን ዝቅ አድርግ ልዝብ ሁን::
عربي تفسیرونه:
فَإِنۡ عَصَوۡكَ فَقُلۡ إِنِّي بَرِيٓءٞ مِّمَّا تَعۡمَلُونَ
216. (መልዕክተኛችን ሙሐመድ ሆይ!) እንቢ ካሉህ «እኔ ከምትሰሩት ወንጀል ሁሉ ንጹህ ነኝ።» በላቸው።
عربي تفسیرونه:
وَتَوَكَّلۡ عَلَى ٱلۡعَزِيزِ ٱلرَّحِيمِ
217. (ሙሐመድ ሆይ!) አሸናፊና አዛኝ በሆነው ጌታህ ላይም ተጠጋ::
عربي تفسیرونه:
ٱلَّذِي يَرَىٰكَ حِينَ تَقُومُ
218. በዚያ ለሶላት በምትቆም ጊዜ በሚያይህ::
عربي تفسیرونه:
وَتَقَلُّبَكَ فِي ٱلسَّٰجِدِينَ
219. በሰጋጆች ውስጥ መዘዋወርህንም (በሚያየው ጌታህ ላይ ተጠጋ::)
عربي تفسیرونه:
إِنَّهُۥ هُوَ ٱلسَّمِيعُ ٱلۡعَلِيمُ
220. እነሆ እርሱ (አላህ) ሁሉ ሰሚና ሁሉን አዋቂ ነውና።
عربي تفسیرونه:
هَلۡ أُنَبِّئُكُمۡ عَلَىٰ مَن تَنَزَّلُ ٱلشَّيَٰطِينُ
221. ሰይጣናት በማን ላይ እንደሚወርዱ ልንገራችሁን?
عربي تفسیرونه:
تَنَزَّلُ عَلَىٰ كُلِّ أَفَّاكٍ أَثِيمٖ
222. በውሸታም ኃጢአተኛ ሁሉ ላይ ይወርዳሉ::
عربي تفسیرونه:
يُلۡقُونَ ٱلسَّمۡعَ وَأَكۡثَرُهُمۡ كَٰذِبُونَ
223. የሰሙትን ወደ ጠንቋዮች ይጥላሉ:: አብዛኞቻቸዉም ውሸታሞች ናቸው::
عربي تفسیرونه:
وَٱلشُّعَرَآءُ يَتَّبِعُهُمُ ٱلۡغَاوُۥنَ
224. (መልዕክተኛችን ሙሐመድ ሆይ!) ባለ ቅኔዎችንም ጠማማዎች ይከተሏቸዋል::
عربي تفسیرونه:
أَلَمۡ تَرَ أَنَّهُمۡ فِي كُلِّ وَادٖ يَهِيمُونَ
225. እነርሱ (በንግግር) ሸለቆ ሁሉ የሚዋልሉ መሆናቸውን አታይምን?
عربي تفسیرونه:
وَأَنَّهُمۡ يَقُولُونَ مَا لَا يَفۡعَلُونَ
226. እነርሱም የማይሰሩትን ነገር የሚናገሩ መሆናቸውን አታይምን::
عربي تفسیرونه:
إِلَّا ٱلَّذِينَ ءَامَنُواْ وَعَمِلُواْ ٱلصَّٰلِحَٰتِ وَذَكَرُواْ ٱللَّهَ كَثِيرٗا وَٱنتَصَرُواْ مِنۢ بَعۡدِ مَا ظُلِمُواْۗ وَسَيَعۡلَمُ ٱلَّذِينَ ظَلَمُوٓاْ أَيَّ مُنقَلَبٖ يَنقَلِبُونَ
227. እነዚያ ያመኑና መልካም ስራዎችን የሰሩ አላህን በብዛት ያወሱ ከተበደሉም በኋላ (በቅኔ) የተከላከሉ ሲቀሩ፤ (እነርሱ አይወቀሱም)። እነዚያም የበደሉ ከሞቱ በኋላ እንዴት ያለን መመለስ እንደሚመለሱ በእርግጥ ያውቃሉ::
عربي تفسیرونه:
 
د معناګانو ژباړه سورت: الشعراء
د سورتونو فهرست (لړلیک) د مخ نمبر
 
د قرآن کریم د معناګانو ژباړه - الترجمة الأمهرية - زين - د ژباړو فهرست (لړلیک)

ترجمة معاني القرآن الكريم إلى اللغة الأمهرية ترجمها محمد زين نهر الدين صادرة عن أكاديمية أفريقيا.

بندول