Check out the new design

د قرآن کریم د معناګانو ژباړه - امهري ژباړه - د افریقا اکاډمي * - د ژباړو فهرست (لړلیک)


د معناګانو ژباړه سورت: نمل   آیت:
وَإِنَّهُۥ لَهُدٗى وَرَحۡمَةٞ لِّلۡمُؤۡمِنِينَ
77. እርሱም ለአማኞች ብቸኛ መምሪያና እዝነት ነው::
عربي تفسیرونه:
إِنَّ رَبَّكَ يَقۡضِي بَيۡنَهُم بِحُكۡمِهِۦۚ وَهُوَ ٱلۡعَزِيزُ ٱلۡعَلِيمُ
78. (መልዕክተኛችን ሙሐመድ ሆይ!) ጌታህ በመካከላቸው በትክክል ፍርዱ ይፈርዳል፤ እርሱም ሁሉን አሸናፊዉና አዋቂው ነው።
عربي تفسیرونه:
فَتَوَكَّلۡ عَلَى ٱللَّهِۖ إِنَّكَ عَلَى ٱلۡحَقِّ ٱلۡمُبِينِ
79. (መልዕክተኛችን ሙሐመድ ሆይ!) በአላህም ላይ ተጠጋ:: አንተ ግልጽ በሆነው እውነት ላይ ነህና።
عربي تفسیرونه:
إِنَّكَ لَا تُسۡمِعُ ٱلۡمَوۡتَىٰ وَلَا تُسۡمِعُ ٱلصُّمَّ ٱلدُّعَآءَ إِذَا وَلَّوۡاْ مُدۡبِرِينَ
80. (መልዕክተኛችን ሙሐመድ ሆይ!) አንተ ሙታንን አታሰማም። ደንቆሮዎችንም የሚተው ሆነው በዞሩ ጊዜ ጥሪን አታሰማም።
عربي تفسیرونه:
وَمَآ أَنتَ بِهَٰدِي ٱلۡعُمۡيِ عَن ضَلَٰلَتِهِمۡۖ إِن تُسۡمِعُ إِلَّا مَن يُؤۡمِنُ بِـَٔايَٰتِنَا فَهُم مُّسۡلِمُونَ
81.(መልዕክተኛችን ሙሐመድ ሆይ!) አንተም ልበ ዕውሮችን ከጥመታቸው አቅኚ አይደለህም:: እነዚያን በአናቅጻችን በትክክል የሚያምኑትን እንጂ አታሰማም:: እነርሱ ፍጹም ታዛዦች (ሙስሊሞች) ናቸውና።
عربي تفسیرونه:
۞ وَإِذَا وَقَعَ ٱلۡقَوۡلُ عَلَيۡهِمۡ أَخۡرَجۡنَا لَهُمۡ دَآبَّةٗ مِّنَ ٱلۡأَرۡضِ تُكَلِّمُهُمۡ أَنَّ ٱلنَّاسَ كَانُواْ بِـَٔايَٰتِنَا لَا يُوقِنُونَ
82. በእነርሱም ላይ የቅጣት ቃሉ በተረጋገጠ ጊዜ ሰዎቹ በአናቅጻችን የማያረጋግጡ እንደነበሩ የምትነግራቸውን እንስሳ ለእነርሱ ከምድር እናወጣላቸዋለን::
عربي تفسیرونه:
وَيَوۡمَ نَحۡشُرُ مِن كُلِّ أُمَّةٖ فَوۡجٗا مِّمَّن يُكَذِّبُ بِـَٔايَٰتِنَا فَهُمۡ يُوزَعُونَ
83. (መልዕክተኛችን ሙሐመድ ሆይ!) ከሕዝቦቹም ሁሉ በአናቅጽ የሚያስተባብሉትን ቡድኖች የምንሰበስብበትን ቀን አስታውስ:: እነርሱም ይከመከማሉ::
عربي تفسیرونه:
حَتَّىٰٓ إِذَا جَآءُو قَالَ أَكَذَّبۡتُم بِـَٔايَٰتِي وَلَمۡ تُحِيطُواْ بِهَا عِلۡمًا أَمَّاذَا كُنتُمۡ تَعۡمَلُونَ
84. በመጡም ጊዜ (አላህ) ይላቸዋል፡ «በአንቀጾቼ እርሷን በማወቅ ያላዳረሳችሁ ስትሆኑ አስተባበላችሁን? ወይስ ምንን ትሰሩ ነበራችሁ?»
عربي تفسیرونه:
وَوَقَعَ ٱلۡقَوۡلُ عَلَيۡهِم بِمَا ظَلَمُواْ فَهُمۡ لَا يَنطِقُونَ
85. በመበደላቸዉም ምክኒያት በእነርሱ ላይ ቃሉ ይፈጸምባቸዋል:: እነርሱም አይናገሩም::
عربي تفسیرونه:
أَلَمۡ يَرَوۡاْ أَنَّا جَعَلۡنَا ٱلَّيۡلَ لِيَسۡكُنُواْ فِيهِ وَٱلنَّهَارَ مُبۡصِرًاۚ إِنَّ فِي ذَٰلِكَ لَأٓيَٰتٖ لِّقَوۡمٖ يُؤۡمِنُونَ
86. እኛ ሌሊትን በእርሱ ውስጥ እንደሚያርፉበት ቀንንም የሚያሳይ እንዳደረግን አያዩምን? ለሚያምኑ ሕዝቦች በዚህ ውስጥ አያሌ ተዓምራት አሉበት::
عربي تفسیرونه:
وَيَوۡمَ يُنفَخُ فِي ٱلصُّورِ فَفَزِعَ مَن فِي ٱلسَّمَٰوَٰتِ وَمَن فِي ٱلۡأَرۡضِ إِلَّا مَن شَآءَ ٱللَّهُۚ وَكُلٌّ أَتَوۡهُ دَٰخِرِينَ
87. (መልዕክተኛችን ሙሐመድ ሆይ!) በቀንዱም በሚነፋ ቀን በሰማያት ውስጥ ያሉትና በምድርም ውስጥ ያሉት ሁሉ አላህ የሻው ነገር ብቻ ሲቀር በሚደነግጡ ጊዜ የሚሆነውን አስታውስ። ሁሉም የተናነሱ ሆነዉም ወደ እርሱ ይመጣሉ::
عربي تفسیرونه:
وَتَرَى ٱلۡجِبَالَ تَحۡسَبُهَا جَامِدَةٗ وَهِيَ تَمُرُّ مَرَّ ٱلسَّحَابِۚ صُنۡعَ ٱللَّهِ ٱلَّذِيٓ أَتۡقَنَ كُلَّ شَيۡءٍۚ إِنَّهُۥ خَبِيرُۢ بِمَا تَفۡعَلُونَ
88. ጋራዎችንም እርሷ እንደ ደመና አስተላለፍ የምታልፍ ስትሆን የቆመች ናት ብለህ የምታስባት ሆና ታያለህ፤ የዚያን ነገሩን ሁሉ ያጠነከረውን የአላህን ጥበብ ተመልከት:: እርሱ በምትሠሩት ሁሉ ውስጥ አዋቂ ነው::
عربي تفسیرونه:
 
د معناګانو ژباړه سورت: نمل
د سورتونو فهرست (لړلیک) د مخ نمبر
 
د قرآن کریم د معناګانو ژباړه - امهري ژباړه - د افریقا اکاډمي - د ژباړو فهرست (لړلیک)

محمد زین زهرالدین ژباړلی دی . د افریقا اکاډمۍ لخوا خپره شوې.

بندول