د قرآن کریم د معناګانو ژباړه - الترجمة الأمهرية - زين * - د ژباړو فهرست (لړلیک)


د معناګانو ژباړه سورت: الجاثية   آیت:

ሱረቱ አል ጃሲያህ

حمٓ
1. ሓ፤ሚይም፤
عربي تفسیرونه:
تَنزِيلُ ٱلۡكِتَٰبِ مِنَ ٱللَّهِ ٱلۡعَزِيزِ ٱلۡحَكِيمِ
2. የመጽሐፉ መወረድ ሁሉን አሸናፊና ጥበበኛ ከሆነው ከአላህ ነው::
عربي تفسیرونه:
إِنَّ فِي ٱلسَّمَٰوَٰتِ وَٱلۡأَرۡضِ لَأٓيَٰتٖ لِّلۡمُؤۡمِنِينَ
3. በሰማያትና በምድር ውስጥ ለአማኞች ሁሉ እርግጠኛ ምልክቶች አሉ::
عربي تفسیرونه:
وَفِي خَلۡقِكُمۡ وَمَا يَبُثُّ مِن دَآبَّةٍ ءَايَٰتٞ لِّقَوۡمٖ يُوقِنُونَ
4. (ሰዎች ሆይ!) እናንተን በመፍጠር እና ከተንቀሳቃሽ ነገሮች በምድር ላይ የሚበተነውን ሁሉ በመፍጠሩ ለሚያረጋግጡ ህዝቦች ሁሉ አያሌ ተአምራት አሉ::
عربي تفسیرونه:
وَٱخۡتِلَٰفِ ٱلَّيۡلِ وَٱلنَّهَارِ وَمَآ أَنزَلَ ٱللَّهُ مِنَ ٱلسَّمَآءِ مِن رِّزۡقٖ فَأَحۡيَا بِهِ ٱلۡأَرۡضَ بَعۡدَ مَوۡتِهَا وَتَصۡرِيفِ ٱلرِّيَٰحِ ءَايَٰتٞ لِّقَوۡمٖ يَعۡقِلُونَ
5. በሌሊትና በቀን መተካካትም፤ አላህ ከሰማይ ባወረደው ሲሳይ (ዝናብ) በእርሱም ምድርን ከሞተች በኋላ ህያው በማድረጉ፤ ንፋሶችንም (በየ አቅጣጫው) በማዘዋወሩ ለሚያውቁ ህዝቦች ሁሉ በቂ ማስረጃዎች አሉ።
عربي تفسیرونه:
تِلۡكَ ءَايَٰتُ ٱللَّهِ نَتۡلُوهَا عَلَيۡكَ بِٱلۡحَقِّۖ فَبِأَيِّ حَدِيثِۭ بَعۡدَ ٱللَّهِ وَءَايَٰتِهِۦ يُؤۡمِنُونَ
6. እነዚህ ባንተ ላይ በእውነት የምናነባቸው የሆኑ የአላህ ማስረጃዎች ናቸው:: ከአላህና ከማስረጃዎቹ በኋላ በየትኛው ንግግር ያምናሉ?
عربي تفسیرونه:
وَيۡلٞ لِّكُلِّ أَفَّاكٍ أَثِيمٖ
7. (መልዕክተኛችን ሙሐመድ ሆይ!) ውሸታም፤ ኃጢአተኛ ለሆነ ሁሉ ወዮለት (ጥፋት ተገባው)።
عربي تفسیرونه:
يَسۡمَعُ ءَايَٰتِ ٱللَّهِ تُتۡلَىٰ عَلَيۡهِ ثُمَّ يُصِرُّ مُسۡتَكۡبِرٗا كَأَن لَّمۡ يَسۡمَعۡهَاۖ فَبَشِّرۡهُ بِعَذَابٍ أَلِيمٖ
8. የአላህን አናቅጽ በእርሱ ላይ የሚነበቡለት ሲሆኑ ይሰማል:: ከዚያም የኮራ ሲሆን እንዳልሰማ ሆኖ በክህደቱ ላይ ይዘወትራል:: እናም እርሱን በአሳማሚ ቅጣት አብስረው::
عربي تفسیرونه:
وَإِذَا عَلِمَ مِنۡ ءَايَٰتِنَا شَيۡـًٔا ٱتَّخَذَهَا هُزُوًاۚ أُوْلَٰٓئِكَ لَهُمۡ عَذَابٞ مُّهِينٞ
9. ከአናቅጻችንም አንዲትን ነገር ባወቀ ጊዜ መሳለቂያ ያደርጋታል:: እነዚያ ለእነርሱ አዋራጅ ቅጣት አለባቸው::
عربي تفسیرونه:
مِّن وَرَآئِهِمۡ جَهَنَّمُۖ وَلَا يُغۡنِي عَنۡهُم مَّا كَسَبُواْ شَيۡـٔٗا وَلَا مَا ٱتَّخَذُواْ مِن دُونِ ٱللَّهِ أَوۡلِيَآءَۖ وَلَهُمۡ عَذَابٌ عَظِيمٌ
10. ከፊታቸዉም ገሀነም አለች:: የሰበሰቡት ሀብትም ከእነርሱ ላይ ምንንም አይመልስላቸዉም:: ከአላህ ሌላም ረዳቶች ያደረጓቸው ሁሉ ምንንም አይጠቅሟቸዉም:: ለእነርሱም ታላቅ ቅጣት አለባቸው::
عربي تفسیرونه:
هَٰذَا هُدٗىۖ وَٱلَّذِينَ كَفَرُواْ بِـَٔايَٰتِ رَبِّهِمۡ لَهُمۡ عَذَابٞ مِّن رِّجۡزٍ أَلِيمٌ
11. ይህ ቁርኣን መሪ ነው:: እነዚያም በጌታቸው አናቅጽ የካዱት ሁሉ ለእነርሱ ከብርቱ ቅጣት ድርሻቸው አለባቸው።
عربي تفسیرونه:
۞ ٱللَّهُ ٱلَّذِي سَخَّرَ لَكُمُ ٱلۡبَحۡرَ لِتَجۡرِيَ ٱلۡفُلۡكُ فِيهِ بِأَمۡرِهِۦ وَلِتَبۡتَغُواْ مِن فَضۡلِهِۦ وَلَعَلَّكُمۡ تَشۡكُرُونَ
12. አላህ ያ ባህርን በውስጡ ታንኳዎች በፈቃዱ እንዲንሻለሉበት ከችሮታዉም እንድትፈልጉበት እንድታመሰግኑትም ለእናንተ የገራላችሁ ነው።
عربي تفسیرونه:
وَسَخَّرَ لَكُم مَّا فِي ٱلسَّمَٰوَٰتِ وَمَا فِي ٱلۡأَرۡضِ جَمِيعٗا مِّنۡهُۚ إِنَّ فِي ذَٰلِكَ لَأٓيَٰتٖ لِّقَوۡمٖ يَتَفَكَّرُونَ
13. ለእናንተ በሰማያትና በምድር ያለው ሁሉ በመላ ከእርሱ ሲሆን ያገራላችሁ ነው። በዚህ ለሚያስተነትኑ ህዝቦች ሁሉ አያሌ ተዐምራት አሉበት።
عربي تفسیرونه:
قُل لِّلَّذِينَ ءَامَنُواْ يَغۡفِرُواْ لِلَّذِينَ لَا يَرۡجُونَ أَيَّامَ ٱللَّهِ لِيَجۡزِيَ قَوۡمَۢا بِمَا كَانُواْ يَكۡسِبُونَ
14. (መልዕክተኛችን ሙሐመድ ሆይ!) ለእነዚያ በአላህ ላመኑት «ለእነዚያ የአላህን ቀናት ለማይፈሩት ሰዎች ምህረት (ይቅርታ) አድርጉ» በላቸው:: (አላህ) ህዝቦችን ይሰሩት በነበሩት ነገር ይመነዳልና።
عربي تفسیرونه:
مَنۡ عَمِلَ صَٰلِحٗا فَلِنَفۡسِهِۦۖ وَمَنۡ أَسَآءَ فَعَلَيۡهَاۖ ثُمَّ إِلَىٰ رَبِّكُمۡ تُرۡجَعُونَ
15. መልካምን የሰራ ሁሉ ጥቅሙ ለነፍሱ ነው:: ክፉንም ተግባር የሰራ ሁሉ ክፋቱ በእርሱው ላይ ነው:: ከዚያም ሁላችሁም ወደ ጌታችሁ ትመለሳላችሁ::
عربي تفسیرونه:
وَلَقَدۡ ءَاتَيۡنَا بَنِيٓ إِسۡرَٰٓءِيلَ ٱلۡكِتَٰبَ وَٱلۡحُكۡمَ وَٱلنُّبُوَّةَ وَرَزَقۡنَٰهُم مِّنَ ٱلطَّيِّبَٰتِ وَفَضَّلۡنَٰهُمۡ عَلَى ٱلۡعَٰلَمِينَ
16. ለኢስራኢል ልጆችም መጽሐፍን፤ ሕግን እና ነብይነትን በእርግጥ ሰጠናቸው:: ከመልካም ሲሳዮችም ለገስንላቸው:: (በዘመናቸው ከነበሩት) የዓለማት ህዝብ ላይም አበለጥናቸው::
عربي تفسیرونه:
وَءَاتَيۡنَٰهُم بَيِّنَٰتٖ مِّنَ ٱلۡأَمۡرِۖ فَمَا ٱخۡتَلَفُوٓاْ إِلَّا مِنۢ بَعۡدِ مَا جَآءَهُمُ ٱلۡعِلۡمُ بَغۡيَۢا بَيۡنَهُمۡۚ إِنَّ رَبَّكَ يَقۡضِي بَيۡنَهُمۡ يَوۡمَ ٱلۡقِيَٰمَةِ فِيمَا كَانُواْ فِيهِ يَخۡتَلِفُونَ
17. ከትዕዛዝም ግልጽ ነገሮችን ሰጠናቸው:: እውቀቱም ከመጣላቸው በኋላ በመካከላቸው ለምቀኝነት እንጅ ለሌላ አልተለያዩም:: (መልዕክተኛችን ሙሐመድ ሆይ!) ጌታህ በትንሳኤ ቀን በዚያ በእርሱ ይለያዩበት በነበሩት ነገር ሁሉ በመካከላቸው በትክክል ይፈርዳል::
عربي تفسیرونه:
ثُمَّ جَعَلۡنَٰكَ عَلَىٰ شَرِيعَةٖ مِّنَ ٱلۡأَمۡرِ فَٱتَّبِعۡهَا وَلَا تَتَّبِعۡ أَهۡوَآءَ ٱلَّذِينَ لَا يَعۡلَمُونَ
18. (መልዕክተኛችን ሙሐመድ ሆይ!) ከዚያም ከሃይማኖት በትክክለኛው ሕግ ላይ አደረግንህ:: ስለዚህ ተከተለው:: የነዚያን የማያውቁትን ህዝቦች ዝንባሌዎች አትከተል::
عربي تفسیرونه:
إِنَّهُمۡ لَن يُغۡنُواْ عَنكَ مِنَ ٱللَّهِ شَيۡـٔٗاۚ وَإِنَّ ٱلظَّٰلِمِينَ بَعۡضُهُمۡ أَوۡلِيَآءُ بَعۡضٖۖ وَٱللَّهُ وَلِيُّ ٱلۡمُتَّقِينَ
19. እነርሱ ከአላህ ቅጣት ምንንም ካንተ አይገፈትሩልህምና። በደለኞችም ከፊላቸው ለከፊሉ ረዳቶች ናቸው:: አላህ የጥንቁቆቹ ወዳጅ ነውና::
عربي تفسیرونه:
هَٰذَا بَصَٰٓئِرُ لِلنَّاسِ وَهُدٗى وَرَحۡمَةٞ لِّقَوۡمٖ يُوقِنُونَ
20. ይህ (ቁርኣን) ለሰዎች የልብ ብርሃኖች ነው:: ለሚያረጋግጡትም ህዝቦች ሁሉ መሪና እዝነት ነው::
عربي تفسیرونه:
أَمۡ حَسِبَ ٱلَّذِينَ ٱجۡتَرَحُواْ ٱلسَّيِّـَٔاتِ أَن نَّجۡعَلَهُمۡ كَٱلَّذِينَ ءَامَنُواْ وَعَمِلُواْ ٱلصَّٰلِحَٰتِ سَوَآءٗ مَّحۡيَاهُمۡ وَمَمَاتُهُمۡۚ سَآءَ مَا يَحۡكُمُونَ
21. እነዚያ ኃጢአቶችን የሰሩ ሕይወታቸዉንም ሞታቸዉንም ልክ እንደነዚያ እንዳመኑት መልካሞችንም እንደሰሩት ልናደርጋቸው ያስባሉን? (አይስቡ):: ይህ ከሆነ ፍርዱ ምንኛ ከፋ፤
عربي تفسیرونه:
وَخَلَقَ ٱللَّهُ ٱلسَّمَٰوَٰتِ وَٱلۡأَرۡضَ بِٱلۡحَقِّ وَلِتُجۡزَىٰ كُلُّ نَفۡسِۭ بِمَا كَسَبَتۡ وَهُمۡ لَا يُظۡلَمُونَ
22. አላህም ሰማያትንና ምድርን በትክክል ፈጠረ:: እነርሱ የማይበደሉ ሲሆኑ ነፍስ ሁሉ በሰራችው ስራ ትመነዳ ዘንድ።
عربي تفسیرونه:
أَفَرَءَيۡتَ مَنِ ٱتَّخَذَ إِلَٰهَهُۥ هَوَىٰهُ وَأَضَلَّهُ ٱللَّهُ عَلَىٰ عِلۡمٖ وَخَتَمَ عَلَىٰ سَمۡعِهِۦ وَقَلۡبِهِۦ وَجَعَلَ عَلَىٰ بَصَرِهِۦ غِشَٰوَةٗ فَمَن يَهۡدِيهِ مِنۢ بَعۡدِ ٱللَّهِۚ أَفَلَا تَذَكَّرُونَ
23. (መልዕክተኛችን ሙሐመድ ሆይ!) ዝንባሌውን አምላኩ ያደረገውን አላህም ከእውቀት ጋር ያጠመመውን በጆሮውና በልቡም ላይ ያተመበትን በዓይኑም ላይ ሺፋን ያደረገበትን ሰው አየህን? ታዲያ ከአላህ በኋላ የሚያቀናው ማነው? አትገሰጹምን?
عربي تفسیرونه:
وَقَالُواْ مَا هِيَ إِلَّا حَيَاتُنَا ٱلدُّنۡيَا نَمُوتُ وَنَحۡيَا وَمَا يُهۡلِكُنَآ إِلَّا ٱلدَّهۡرُۚ وَمَا لَهُم بِذَٰلِكَ مِنۡ عِلۡمٍۖ إِنۡ هُمۡ إِلَّا يَظُنُّونَ
24. (ከሓዲያን) «እርሷም(ሕይወት) የቅርቢቱ ሕይወታችን ብቻ እንጂ ሌላ አይደለችም:: እንሞታለን:: ህያዉም እንሆናለን:: ከጊዜም (ማለፍ) በሰተቀር ሌላ አያጠፋንም» አሉ:: ለእነርሱም በዚህ በሚሉት ምንም እውቀት የላቸዉም:: እነርሱ የሚጠራጠሩ እንጂ ሌላ አይደሉም::
عربي تفسیرونه:
وَإِذَا تُتۡلَىٰ عَلَيۡهِمۡ ءَايَٰتُنَا بَيِّنَٰتٖ مَّا كَانَ حُجَّتَهُمۡ إِلَّآ أَن قَالُواْ ٱئۡتُواْ بِـَٔابَآئِنَآ إِن كُنتُمۡ صَٰدِقِينَ
25. አናቅጻችንም ግልፆች ሆነው በእነርሱ ላይ በተነበቡላቸው ጊዜ የክርክራቸው ማስረጃ «እውነተኞች እንደሆናችሁ እስቲ የቀድሞ አባቶቻችንን አምጡ» ማለት እንጂ ሌላ አልነበረም።
عربي تفسیرونه:
قُلِ ٱللَّهُ يُحۡيِيكُمۡ ثُمَّ يُمِيتُكُمۡ ثُمَّ يَجۡمَعُكُمۡ إِلَىٰ يَوۡمِ ٱلۡقِيَٰمَةِ لَا رَيۡبَ فِيهِ وَلَٰكِنَّ أَكۡثَرَ ٱلنَّاسِ لَا يَعۡلَمُونَ
26. (መልዕክተኛችን ሙሐመድ ሆይ!) «አላህ ህያው ያደርጋችኋል ከዚያም ያሞታችኋልም:: ከዚያም በትንሳኤ ቀን ይሰበስባችኋል:: ይህም ጥርጥር የለበትም:: ግን አብዛኛዎቹ ሰዎች አያውቁም።» በላቸው::
عربي تفسیرونه:
وَلِلَّهِ مُلۡكُ ٱلسَّمَٰوَٰتِ وَٱلۡأَرۡضِۚ وَيَوۡمَ تَقُومُ ٱلسَّاعَةُ يَوۡمَئِذٖ يَخۡسَرُ ٱلۡمُبۡطِلُونَ
27. የሰማያትና የምድር ግዛት የአላህ ብቻ ነው:: ሰዓቲቱም በምትከሰትበት ቀን ያን ጊዜ አጥፊዎች ሁሉ ይከስራሉ::
عربي تفسیرونه:
وَتَرَىٰ كُلَّ أُمَّةٖ جَاثِيَةٗۚ كُلُّ أُمَّةٖ تُدۡعَىٰٓ إِلَىٰ كِتَٰبِهَا ٱلۡيَوۡمَ تُجۡزَوۡنَ مَا كُنتُمۡ تَعۡمَلُونَ
28. (መልዕክተኛችን ሙሐመድ ሆይ!) ህዝቦችን ሁሉ ተንበርካኪ ሆነው ታያቸዋለህ:: ህዝብም ሁሉ ወደ ግል መጽሐፋቸው ይጠራሉ:: ይባላሉም: «ዛሬ ቀደም ሲል ትሰሩት የነበራችሁትን ነገር ትመነዳላችሁ
عربي تفسیرونه:
هَٰذَا كِتَٰبُنَا يَنطِقُ عَلَيۡكُم بِٱلۡحَقِّۚ إِنَّا كُنَّا نَسۡتَنسِخُ مَا كُنتُمۡ تَعۡمَلُونَ
29. «ይህ መጽሐፋችን ነው:: በእናንተ ላይ በእውነት ይናገራል:: እኛ ያንን ትሰሩት የነበራችሁትን ሁሉ እናስገለብጥ ነበርንና» (ይባላሉ)::
عربي تفسیرونه:
فَأَمَّا ٱلَّذِينَ ءَامَنُواْ وَعَمِلُواْ ٱلصَّٰلِحَٰتِ فَيُدۡخِلُهُمۡ رَبُّهُمۡ فِي رَحۡمَتِهِۦۚ ذَٰلِكَ هُوَ ٱلۡفَوۡزُ ٱلۡمُبِينُ
30. እነዚያ ያመኑትና መልካሞችን የሰሩትማ ጌታቸው በእዝነቱ ውስጥ ያስገባቸዋል:: ይህ እርሱ ግልጽ የሆነ እድልን ማግኘት ነው::
عربي تفسیرونه:
وَأَمَّا ٱلَّذِينَ كَفَرُوٓاْ أَفَلَمۡ تَكُنۡ ءَايَٰتِي تُتۡلَىٰ عَلَيۡكُمۡ فَٱسۡتَكۡبَرۡتُمۡ وَكُنتُمۡ قَوۡمٗا مُّجۡرِمِينَ
31. እነዚያም የካዱትማ ለእነርሱ ይባላሉ: «አናቅጾቼ በእናንተ ላይ ይነበቡ አልነበሩምን? ኮራችሁም :: ከሓዲያን ህዝቦችም ነበራችሁ::
عربي تفسیرونه:
وَإِذَا قِيلَ إِنَّ وَعۡدَ ٱللَّهِ حَقّٞ وَٱلسَّاعَةُ لَا رَيۡبَ فِيهَا قُلۡتُم مَّا نَدۡرِي مَا ٱلسَّاعَةُ إِن نَّظُنُّ إِلَّا ظَنّٗا وَمَا نَحۡنُ بِمُسۡتَيۡقِنِينَ
32. «የአላህ ቀጠሮ እውነት ነው:: በእርሷ መምጣት (ጥርጥር) የለም:: በተባለ ጊዜም 'ሰዓቲቱ ምን እንደሆነች አናውቅም መጠራጠርን የምንጠራጠር እንጂ ሌላ አይደለንም:: እኛም አረጋጋጮች አይደለንም' አላችሁ::» (ይባላሉ)
عربي تفسیرونه:
وَبَدَا لَهُمۡ سَيِّـَٔاتُ مَا عَمِلُواْ وَحَاقَ بِهِم مَّا كَانُواْ بِهِۦ يَسۡتَهۡزِءُونَ
33. የሰሩዋቸው ኃጢአቶችም ለእነርሱ ይገለጹላቸዋል:: ያም በእርሱ ይሳለቁበት የነበሩት ቅጣት በእነርሱ ላይ ይወርድባቸዋል::
عربي تفسیرونه:
وَقِيلَ ٱلۡيَوۡمَ نَنسَىٰكُمۡ كَمَا نَسِيتُمۡ لِقَآءَ يَوۡمِكُمۡ هَٰذَا وَمَأۡوَىٰكُمُ ٱلنَّارُ وَمَا لَكُم مِّن نَّٰصِرِينَ
34. «በዱንያ የዚህንም ቀናችሁን መገናኘት እንደረሳችሁ ሁሉ ዛሬ እኛም እንተዋችኋለን:: መኖሪያችሁም እሳት ናት:: ለእናንተም ከረዳቶች ምንም የላችሁም» ይባላል።
عربي تفسیرونه:
ذَٰلِكُم بِأَنَّكُمُ ٱتَّخَذۡتُمۡ ءَايَٰتِ ٱللَّهِ هُزُوٗا وَغَرَّتۡكُمُ ٱلۡحَيَوٰةُ ٱلدُّنۡيَاۚ فَٱلۡيَوۡمَ لَا يُخۡرَجُونَ مِنۡهَا وَلَا هُمۡ يُسۡتَعۡتَبُونَ
35. «ይህ እናንተ የአላህን አናቅጽ መቀላጃ በማድረጋችሁና ቅርቢቱ ሕይወት ስለ አታለለቻችሁ ነው» ይባላሉ:: ዛሬ ከእርሷ አይወጡም:: እነርሱም በወቀሳ አይታለፉም::
عربي تفسیرونه:
فَلِلَّهِ ٱلۡحَمۡدُ رَبِّ ٱلسَّمَٰوَٰتِ وَرَبِّ ٱلۡأَرۡضِ رَبِّ ٱلۡعَٰلَمِينَ
36. ምስጋና ሁሉ ለሰማያት፤ ለምድርና ለዓለማት ጌታ ለሆነው ለአላህ ብቻ የተገባው ነው::
عربي تفسیرونه:
وَلَهُ ٱلۡكِبۡرِيَآءُ فِي ٱلسَّمَٰوَٰتِ وَٱلۡأَرۡضِۖ وَهُوَ ٱلۡعَزِيزُ ٱلۡحَكِيمُ
37. ኩራትም በሰማያትም ሆነ በምድር ለእርሱ ብቻ ነው:: እርሱ ሁሉን አሸናፊና ጥበበኛ ነውና::
عربي تفسیرونه:
 
د معناګانو ژباړه سورت: الجاثية
د سورتونو فهرست (لړلیک) د مخ نمبر
 
د قرآن کریم د معناګانو ژباړه - الترجمة الأمهرية - زين - د ژباړو فهرست (لړلیک)

ترجمة معاني القرآن الكريم إلى اللغة الأمهرية ترجمها محمد زين نهر الدين صادرة عن أكاديمية أفريقيا.

بندول