Check out the new design

Tradução dos significados do Nobre Qur’an. - Tradução do amárico - Academia África * - Índice de tradução


Tradução dos significados Surah: Al-Baqarah   Versículo:
وَٱلَّذِينَ يُتَوَفَّوۡنَ مِنكُمۡ وَيَذَرُونَ أَزۡوَٰجٗا يَتَرَبَّصۡنَ بِأَنفُسِهِنَّ أَرۡبَعَةَ أَشۡهُرٖ وَعَشۡرٗاۖ فَإِذَا بَلَغۡنَ أَجَلَهُنَّ فَلَا جُنَاحَ عَلَيۡكُمۡ فِيمَا فَعَلۡنَ فِيٓ أَنفُسِهِنَّ بِٱلۡمَعۡرُوفِۗ وَٱللَّهُ بِمَا تَعۡمَلُونَ خَبِيرٞ
234. (ወንዶች ሆይ!) እነዚያ ከናንተ ውስጥ የሚሞቱና ሚስቶችን የሚተው ሚስቶቻቸው በራሳቸው አራት ወር ከአስር ቀናትን ከጋብቻ ይታገሱ:: ጊዜያቸውንም በጨረሱ ጊዜ በራሳቸው ተነሳሽነት በሚፈጽሙት ሕጋዊ ተግባር በእናንተ ላይ ምንም ኃጢአት የለባችሁም:: አላህ የምትሰሩትን ነገር ሁሉ ውስጠ አዋቂ ነው::
Os Tafssir em língua árabe:
وَلَا جُنَاحَ عَلَيۡكُمۡ فِيمَا عَرَّضۡتُم بِهِۦ مِنۡ خِطۡبَةِ ٱلنِّسَآءِ أَوۡ أَكۡنَنتُمۡ فِيٓ أَنفُسِكُمۡۚ عَلِمَ ٱللَّهُ أَنَّكُمۡ سَتَذۡكُرُونَهُنَّ وَلَٰكِن لَّا تُوَاعِدُوهُنَّ سِرًّا إِلَّآ أَن تَقُولُواْ قَوۡلٗا مَّعۡرُوفٗاۚ وَلَا تَعۡزِمُواْ عُقۡدَةَ ٱلنِّكَاحِ حَتَّىٰ يَبۡلُغَ ٱلۡكِتَٰبُ أَجَلَهُۥۚ وَٱعۡلَمُوٓاْ أَنَّ ٱللَّهَ يَعۡلَمُ مَا فِيٓ أَنفُسِكُمۡ فَٱحۡذَرُوهُۚ وَٱعۡلَمُوٓاْ أَنَّ ٱللَّهَ غَفُورٌ حَلِيمٞ
235. (ወንዶች ሆይ!) ባሎቻቸው የሞቱባቸውን ሴቶች የጋብቻ (አሽሙር) ፍንጭ በመስጠታችሁ ወይም እንዲህ ዓይነቱን ሀሳብ በውስጣችሁ በማሰባችሁ ምክንያት በእናንተ ላይ ምንም ኃጢአት የለባችሁም:: አላህ እናንተ በእርግጥ እንዲህ ዓይነቱን ሀሳብ እንደምታስተናግዱ ቀድሞውኑ ያውቃል:: ስለዚህ (አሽሙር) ፍንጭ መስጠትንና ማሰብን ፈቀደላችሁ:: ግና በሕግ የታወቀን ጨዋ ንግግር የምትነጋገሩ ካልሆናችሁ በስተቀር የተፃፈው የኢዳ ጊዜው እስከሚደርስ ድረስ ለትዳር እንደምትፈልጓቸው በሚስጥር ቃል አትግቡላቸው:: ጋብቻን ለመዋዋልም ቁርጥ ሀሳብ አታድርጉ:: አላህ በነፍሶቻችሁ ውስጥ ያለውን ሁሉን ጠንቅቆ የሚያውቅ መሆኑን እወቁ:: ተጠንቀቁም፤ አላህ መሀሪና ታጋሽ መሆኑንም እወቁ::
Os Tafssir em língua árabe:
لَّا جُنَاحَ عَلَيۡكُمۡ إِن طَلَّقۡتُمُ ٱلنِّسَآءَ مَا لَمۡ تَمَسُّوهُنَّ أَوۡ تَفۡرِضُواْ لَهُنَّ فَرِيضَةٗۚ وَمَتِّعُوهُنَّ عَلَى ٱلۡمُوسِعِ قَدَرُهُۥ وَعَلَى ٱلۡمُقۡتِرِ قَدَرُهُۥ مَتَٰعَۢا بِٱلۡمَعۡرُوفِۖ حَقًّا عَلَى ٱلۡمُحۡسِنِينَ
236. (ባሎች ሆይ!) ሴቶችን ግንኙነት ከማድረግ በፊት ወይም ለእነርሱ መህርን ሳትወስኑላቸው ብትፈቷቸው በእናንተ ላይ ኃጢአት የለባችሁም:: ነገር ግን ሀብታምም ደሃም እንደየአቅማቸው ይካሷቸው:: ይህ አቅምን መሰረት ያደረገ ካሳ በቅን ሰዎች ላይ የተደነገገ ህግ ነው::
Os Tafssir em língua árabe:
وَإِن طَلَّقۡتُمُوهُنَّ مِن قَبۡلِ أَن تَمَسُّوهُنَّ وَقَدۡ فَرَضۡتُمۡ لَهُنَّ فَرِيضَةٗ فَنِصۡفُ مَا فَرَضۡتُمۡ إِلَّآ أَن يَعۡفُونَ أَوۡ يَعۡفُوَاْ ٱلَّذِي بِيَدِهِۦ عُقۡدَةُ ٱلنِّكَاحِۚ وَأَن تَعۡفُوٓاْ أَقۡرَبُ لِلتَّقۡوَىٰۚ وَلَا تَنسَوُاْ ٱلۡفَضۡلَ بَيۡنَكُمۡۚ إِنَّ ٱللَّهَ بِمَا تَعۡمَلُونَ بَصِيرٌ
237. (ባሎች ሆይ!) ለሚስቶቻችሁ መህርን የወሰናችሁላቸው ስትሆኑ ሳትገናኟቸው በፊት ብትፈቷቸው ራሳቸው ይቅር ካላሉ ወይም ያ የጋብቻ ውል በእጁ የሆነ ባል ካላግራራ በስተቀር ከወሰናችሁት ግማሹን መስጠት ግድ ሆኖባችኋል:: ሁላችሁም ይቅር መባባላችሁ ወደ አላህ ፍራቻ በጣም የቀረበ ነው:: አንዱ ለሌላው በጎ መዋልን አይዘንጋ:: አላህም የምትሰሩትን ሁሉ ተመልካች ነውና::
Os Tafssir em língua árabe:
 
Tradução dos significados Surah: Al-Baqarah
Índice de capítulos Número de página
 
Tradução dos significados do Nobre Qur’an. - Tradução do amárico - Academia África - Índice de tradução

Tradução - Muhammad Zain Zaher Al-Din. Publicado pela Academia da África.

Fechar