Ibisobanuro bya qoran ntagatifu - الترجمة الأمهرية - زين * - Ishakiro ry'ibisobanuro


Ibisobanuro by'amagambo Isura: Al Hijri   Umurongo:

ሱረቱ አል ሒጅር

الٓرۚ تِلۡكَ ءَايَٰتُ ٱلۡكِتَٰبِ وَقُرۡءَانٖ مُّبِينٖ
1. አሊፍ፤ ላም፤ ራ፤ እነዚህ አናቅጽ ከመጽሐፍ አናቅጽና ገላጭ ከሆነው ቁርኣን ናቸው።
Ibisobanuro by'icyarabu:
رُّبَمَا يَوَدُّ ٱلَّذِينَ كَفَرُواْ لَوۡ كَانُواْ مُسۡلِمِينَ
2.እነዚያ በአላህ የካዱት ሰዎች በትንሳኤ ቀን ሙስሊሞች በሆኑ ኖሮ ብለው በብዛት ይመኛሉ::
Ibisobanuro by'icyarabu:
ذَرۡهُمۡ يَأۡكُلُواْ وَيَتَمَتَّعُواْ وَيُلۡهِهِمُ ٱلۡأَمَلُۖ فَسَوۡفَ يَعۡلَمُونَ
3. (መልዕክተኛችን ሙሐመድ ሆይ!) እነርሱን ተዋቸው:: ይብሉ ይጠቀሙም:: ተስፋም ያዘናጋቸው:: በእርግጥም መጥፎ ፍጻሜያቸውን ያውቃሉ::
Ibisobanuro by'icyarabu:
وَمَآ أَهۡلَكۡنَا مِن قَرۡيَةٍ إِلَّا وَلَهَا كِتَابٞ مَّعۡلُومٞ
4. (መልዕክተኛችን ሙሐመድ ሆይ!) ማንኛይቱንም ከተማ ለእርሷ የተወሰነ መጽሐፍ ጊዜያት ያላት ሆና እንጂ አላጠፋንም::
Ibisobanuro by'icyarabu:
مَّا تَسۡبِقُ مِنۡ أُمَّةٍ أَجَلَهَا وَمَا يَسۡتَـٔۡخِرُونَ
5. ማንኛይቱም ሕዝብ የመጥፊያ ጊዜዋን በምንም ዘዴ አትቀድምም:: ከእርሱም በማንም ሀይል አትዘገይምም::
Ibisobanuro by'icyarabu:
وَقَالُواْ يَٰٓأَيُّهَا ٱلَّذِي نُزِّلَ عَلَيۡهِ ٱلذِّكۡرُ إِنَّكَ لَمَجۡنُونٞ
6. እነዚያ የመካ ከሓዲያን አሉ: «አንተ ያ በእርሱ ላይ ቁርኣን የተወረደለት ሆይ! አንተ በእርግጥ እብድ ነህ።
Ibisobanuro by'icyarabu:
لَّوۡمَا تَأۡتِينَا بِٱلۡمَلَٰٓئِكَةِ إِن كُنتَ مِنَ ٱلصَّٰدِقِينَ
7. «ከእውነተኞቹ እንደ ሆንክ መስካሪ መላዕክት ለምን አታመጣልንም?» አሉ።
Ibisobanuro by'icyarabu:
مَا نُنَزِّلُ ٱلۡمَلَٰٓئِكَةَ إِلَّا بِٱلۡحَقِّ وَمَا كَانُوٓاْ إِذٗا مُّنظَرِينَ
8. መላእክትን ደግሞ በእውነት በቅጣት እንጂ አናወርድም:: ያን ጊዜም የሚቆዩ ጊዜ የሚሰጣቸው አይደሉም::
Ibisobanuro by'icyarabu:
إِنَّا نَحۡنُ نَزَّلۡنَا ٱلذِّكۡرَ وَإِنَّا لَهُۥ لَحَٰفِظُونَ
9. እኛ ቁርኣንን እኛው አወረድነው:: እኛም ጠባቂዎቹ ነን::
Ibisobanuro by'icyarabu:
وَلَقَدۡ أَرۡسَلۡنَا مِن قَبۡلِكَ فِي شِيَعِ ٱلۡأَوَّلِينَ
10. (መልዕክተኛችን ሙሐመድ ሆይ!) ካንተም በፊት በነበሩት በመጀመሪያዎቹ ሕዝቦች ውስጥ መልክተኞችን በእርግጥ ልከናል:
Ibisobanuro by'icyarabu:
وَمَا يَأۡتِيهِم مِّن رَّسُولٍ إِلَّا كَانُواْ بِهِۦ يَسۡتَهۡزِءُونَ
11. ማንኛዉም መልዕክተኛ በእርሱ የሚያላግጡበት ሆነው እንጂ አይመጣላቸዉም ነበር::
Ibisobanuro by'icyarabu:
كَذَٰلِكَ نَسۡلُكُهُۥ فِي قُلُوبِ ٱلۡمُجۡرِمِينَ
12. ልክ እንደዚሁ ማስተባበልን በአመጸኞች ልቦች ውስጥ እናስገባዋለን::
Ibisobanuro by'icyarabu:
لَا يُؤۡمِنُونَ بِهِۦ وَقَدۡ خَلَتۡ سُنَّةُ ٱلۡأَوَّلِينَ
13. በእርሱ አያምኑበትም፤ የቀድሞዎቹም ድርጊት በእርግጥ አልፋለች (እንደጠፉ ይጠፋሉ)::
Ibisobanuro by'icyarabu:
وَلَوۡ فَتَحۡنَا عَلَيۡهِم بَابٗا مِّنَ ٱلسَّمَآءِ فَظَلُّواْ فِيهِ يَعۡرُجُونَ
14. በእነርሱም ላይ ከሰማይ ደጃፍን በከፈትንላቸውና በእርሱ ሲወጡ ቢውሉም
Ibisobanuro by'icyarabu:
لَقَالُوٓاْ إِنَّمَا سُكِّرَتۡ أَبۡصَٰرُنَا بَلۡ نَحۡنُ قَوۡمٞ مَّسۡحُورُونَ
15. «የተዘጉ ዓይኖቻችን ተጭበርብረው ነው:: እንዲያዉም እኛ የተደገመብን ሰዎች ነን።» ባሉ ነበር።
Ibisobanuro by'icyarabu:
وَلَقَدۡ جَعَلۡنَا فِي ٱلسَّمَآءِ بُرُوجٗا وَزَيَّنَّٰهَا لِلنَّٰظِرِينَ
16. በሰማይም ላይ ከዋክብቶችን በእርግጥ አድርገናል (ፈጥረናል):: ለተመልካቾችም በከዋክብት አጊጠናታል::
Ibisobanuro by'icyarabu:
وَحَفِظۡنَٰهَا مِن كُلِّ شَيۡطَٰنٖ رَّجِيمٍ
17. ከተባረረ ሰይጣንም ሁሉ ጠብቀናታል::
Ibisobanuro by'icyarabu:
إِلَّا مَنِ ٱسۡتَرَقَ ٱلسَّمۡعَ فَأَتۡبَعَهُۥ شِهَابٞ مُّبِينٞ
18. ግን ወሬ መስማትን የሚሰርቅ ወዲያውኑ አብሪ ችቦ ይከተለዋል:: (ያቃጥለዋል)::
Ibisobanuro by'icyarabu:
وَٱلۡأَرۡضَ مَدَدۡنَٰهَا وَأَلۡقَيۡنَا فِيهَا رَوَٰسِيَ وَأَنۢبَتۡنَا فِيهَا مِن كُلِّ شَيۡءٖ مَّوۡزُونٖ
19. ምድርንም ዘረጋናት:: በውስጧም ኮረብታዎችን ጣልንባት:: በውስጧም የተለካን በቃይ ሁሉ አበቀልንባት::
Ibisobanuro by'icyarabu:
وَجَعَلۡنَا لَكُمۡ فِيهَا مَعَٰيِشَ وَمَن لَّسۡتُمۡ لَهُۥ بِرَٰزِقِينَ
20.(ሰዎች ሆይ!) በእርሷ ውስጥ ለእናንተ ልዩ ልዩ መኖሪያዎችንና ለእርሱ መጋቢዎቹ ያልሆናችሁትንም እንስሳትን አደረግንላችሁ::
Ibisobanuro by'icyarabu:
وَإِن مِّن شَيۡءٍ إِلَّا عِندَنَا خَزَآئِنُهُۥ وَمَا نُنَزِّلُهُۥٓ إِلَّا بِقَدَرٖ مَّعۡلُومٖ
21. መጋዘኖቹም መክፈቻቸው እኛው ዘንድ ያልሆነ ምንም ነገር የለም:: በተወሰነም ልክ እንጂ አናወርደዉም::
Ibisobanuro by'icyarabu:
وَأَرۡسَلۡنَا ٱلرِّيَٰحَ لَوَٰقِحَ فَأَنزَلۡنَا مِنَ ٱلسَّمَآءِ مَآءٗ فَأَسۡقَيۡنَٰكُمُوهُ وَمَآ أَنتُمۡ لَهُۥ بِخَٰزِنِينَ
22. ንፋስን ደመናን ተሸካሚዎች አድርገን ላክን:: ከሰማይም ከደመና ዝናብን አወረድን:: እርሱንም አጠጣናችሁ:: እናንተ ለእርሱ አድላቢዎች (አከማቾች) አይደላችሁም::
Ibisobanuro by'icyarabu:
وَإِنَّا لَنَحۡنُ نُحۡيِۦ وَنُمِيتُ وَنَحۡنُ ٱلۡوَٰرِثُونَ
23. እኛ ሕያው የምናደርግና የምንገድል እኛው ብቻ ነን:: እኛው ፍጡርን ሁሉ የምንወርስ ቀሪ ነን::
Ibisobanuro by'icyarabu:
وَلَقَدۡ عَلِمۡنَا ٱلۡمُسۡتَقۡدِمِينَ مِنكُمۡ وَلَقَدۡ عَلِمۡنَا ٱلۡمُسۡتَـٔۡخِرِينَ
24. ከናንተም ተቀዳሚዎቹን በእርግጥ አውቀናል:: ወደ ኋላ ቀሪዎቹንም በእርግጥ አውቀናል::
Ibisobanuro by'icyarabu:
وَإِنَّ رَبَّكَ هُوَ يَحۡشُرُهُمۡۚ إِنَّهُۥ حَكِيمٌ عَلِيمٞ
25. (መልዕክተኛችን ሙሐመድ ሆይ!)ጌታህ ይሰበስባቸዋል:: እርሱ ጥበበኛና ሁሉን አዋቂ ነውና::
Ibisobanuro by'icyarabu:
وَلَقَدۡ خَلَقۡنَا ٱلۡإِنسَٰنَ مِن صَلۡصَٰلٖ مِّنۡ حَمَإٖ مَّسۡنُونٖ
26. ሰውንም ከሚቅጨለጨል ሸክላ ከሚገማ ጥቁር ጭቃ በእርግጥ ፈጠርነው::
Ibisobanuro by'icyarabu:
وَٱلۡجَآنَّ خَلَقۡنَٰهُ مِن قَبۡلُ مِن نَّارِ ٱلسَّمُومِ
27. ጃንን ከሰው በፊት ከእሳት ነበልባል ፈጠርነው::
Ibisobanuro by'icyarabu:
وَإِذۡ قَالَ رَبُّكَ لِلۡمَلَٰٓئِكَةِ إِنِّي خَٰلِقُۢ بَشَرٗا مِّن صَلۡصَٰلٖ مِّنۡ حَمَإٖ مَّسۡنُونٖ
28. (መልዕክተኛችን ሙሐመድ ሆይ!) ጌታህም ለመላዕክት ባለ ጊዜ (የሆነውን አስታውስ): «እኔ ሰውን ከሚቅጨለጨል ሸክላ ከሚገማ ጭቃ እፈጥራለሁ።
Ibisobanuro by'icyarabu:
فَإِذَا سَوَّيۡتُهُۥ وَنَفَخۡتُ فِيهِ مِن رُّوحِي فَقَعُواْ لَهُۥ سَٰجِدِينَ
29. «ፍጥረቱን ባስተካከልኩትና በውስጡ ከመንፈሴ በነፋሁበትም ጊዜ ለእርሱ ሰጋጆች ሆናችሁ ውደቁ።»
Ibisobanuro by'icyarabu:
فَسَجَدَ ٱلۡمَلَٰٓئِكَةُ كُلُّهُمۡ أَجۡمَعُونَ
30. መላዓክትም ሁሉም ተሰብስበው ሰገዱ::
Ibisobanuro by'icyarabu:
إِلَّآ إِبۡلِيسَ أَبَىٰٓ أَن يَكُونَ مَعَ ٱلسَّٰجِدِينَ
31. ዲያብሎስ ብቻ ሲቀር:: እርሱማ ከሰጋጆቹ ጋር ከመሆን እንቢ አለ።
Ibisobanuro by'icyarabu:
قَالَ يَٰٓإِبۡلِيسُ مَا لَكَ أَلَّا تَكُونَ مَعَ ٱلسَّٰجِدِينَ
32. አላህም፡ «ዲያብሎስ ሆይ! ከሰጋጆቹ ጋር የማትሆን ላንተ ምን ምክንያት አለህ?» አለው።
Ibisobanuro by'icyarabu:
قَالَ لَمۡ أَكُن لِّأَسۡجُدَ لِبَشَرٍ خَلَقۡتَهُۥ مِن صَلۡصَٰلٖ مِّنۡ حَمَإٖ مَّسۡنُونٖ
33. «ከሚቅጨለጨል ሸክላ ከግም ጭቃ ለፈጠርከው ሰው ልሰግድ አይገባኝም።» አለ።
Ibisobanuro by'icyarabu:
قَالَ فَٱخۡرُجۡ مِنۡهَا فَإِنَّكَ رَجِيمٞ
34. አላህም አለው: «ከእርሷም ውጣ አንተ የተባረርክ እርጉም ነህና።
Ibisobanuro by'icyarabu:
وَإِنَّ عَلَيۡكَ ٱللَّعۡنَةَ إِلَىٰ يَوۡمِ ٱلدِّينِ
35. «ባንተ ላይም እስከ ፍርዱ ቀን ድረስ እርግማን አለብህ።» አለው።
Ibisobanuro by'icyarabu:
قَالَ رَبِّ فَأَنظِرۡنِيٓ إِلَىٰ يَوۡمِ يُبۡعَثُونَ
36. «ጌታዬ ሆይ! እንግዲያውስ እስከሚቀሰቀሱበት ቀን ድረስ አቆየኝ።» አለ።
Ibisobanuro by'icyarabu:
قَالَ فَإِنَّكَ مِنَ ٱلۡمُنظَرِينَ
37. አላህም አለ፡- «አንተ ከሚቆዩት ነህ።
Ibisobanuro by'icyarabu:
إِلَىٰ يَوۡمِ ٱلۡوَقۡتِ ٱلۡمَعۡلُومِ
38. «እስከታወቀው ቀን ድረስ።»
Ibisobanuro by'icyarabu:
قَالَ رَبِّ بِمَآ أَغۡوَيۡتَنِي لَأُزَيِّنَنَّ لَهُمۡ فِي ٱلۡأَرۡضِ وَلَأُغۡوِيَنَّهُمۡ أَجۡمَعِينَ
39. ዲያብሎስም አለ፡- «ጌታዬ ሆይ! እኔን በማጥመምህ ይሁንብኝ ለእነርሱ በምድር ላይ ኃጢአትን እሸልምላቸዋለሁ። ሁላቸውንም አጠማቸዋለሁ።
Ibisobanuro by'icyarabu:
إِلَّا عِبَادَكَ مِنۡهُمُ ٱلۡمُخۡلَصِينَ
40. «ከእነርሱ ፍጹሞቹ ባሮችህ ብቻ ሲቀሩ።»
Ibisobanuro by'icyarabu:
قَالَ هَٰذَا صِرَٰطٌ عَلَيَّ مُسۡتَقِيمٌ
41. አላህም አለ፡- «ይህ በእኔ ላይ መጠበቁ የተገባ ቀጥተኛ መንገድ ነው።
Ibisobanuro by'icyarabu:
إِنَّ عِبَادِي لَيۡسَ لَكَ عَلَيۡهِمۡ سُلۡطَٰنٌ إِلَّا مَنِ ٱتَّبَعَكَ مِنَ ٱلۡغَاوِينَ
42. «እነሆ ባሮቼ! በእነርሱ ላይ አንተ ስልጣን የለህም። ከጠማሞች የተከተለህ ሰው ብቻ ሲቀር።
Ibisobanuro by'icyarabu:
وَإِنَّ جَهَنَّمَ لَمَوۡعِدُهُمۡ أَجۡمَعِينَ
43. «ገሀነምም ለእርሱና ለተከተሉት ለሁሉም በእርግጥ ቀጠሯቸው ናት።
Ibisobanuro by'icyarabu:
لَهَا سَبۡعَةُ أَبۡوَٰبٖ لِّكُلِّ بَابٖ مِّنۡهُمۡ جُزۡءٞ مَّقۡسُومٌ
44. «ለእርሷ ሰባት በሮች (ደጃፎች ) አሏት። ለየበሮቹም ሁሉ ከሰይጣናት ቡድኖች የተከፋፈለ ድርሻ አለ።»
Ibisobanuro by'icyarabu:
إِنَّ ٱلۡمُتَّقِينَ فِي جَنَّٰتٖ وَعُيُونٍ
45. እነዚያ ከኃጢአት የተጠነቀቁት በአትክልቶችና በምንጮች ውስጥ ናቸው::
Ibisobanuro by'icyarabu:
ٱدۡخُلُوهَا بِسَلَٰمٍ ءَامِنِينَ
46. «ጸጥተኞች ሆናችሁ በሰላም ግቧት።» ይባላሉ።
Ibisobanuro by'icyarabu:
وَنَزَعۡنَا مَا فِي صُدُورِهِم مِّنۡ غِلٍّ إِخۡوَٰنًا عَلَىٰ سُرُرٖ مُّتَقَٰبِلِينَ
47. በአልጋዎችም ላይ ፊት ለፊት የሚተያዩ ወንድማማቾች ሆነው በልቦቻቸው ውስጥ ያለውን ቂም ሁሉ እናስወግዳለን::
Ibisobanuro by'icyarabu:
لَا يَمَسُّهُمۡ فِيهَا نَصَبٞ وَمَا هُم مِّنۡهَا بِمُخۡرَجِينَ
48. በእርሷም ውስጥ ምንም ድካም አይነካቸዉም፤ እነርሱም ከእርሷ ለምንጊዜም የሚወጡ አይደሉም::
Ibisobanuro by'icyarabu:
۞ نَبِّئۡ عِبَادِيٓ أَنِّيٓ أَنَا ٱلۡغَفُورُ ٱلرَّحِيمُ
49. (መልዕክተኛችን ሙሐመድ ሆይ!) መሃሪና አዛኝ እኔው ብቻ መሆኔን ለባሮቼ ንገር::
Ibisobanuro by'icyarabu:
وَأَنَّ عَذَابِي هُوَ ٱلۡعَذَابُ ٱلۡأَلِيمُ
50. ቅጣቴም እርሱ አሳማሚ ቅጣት መሆኑንም ንገራቸው።
Ibisobanuro by'icyarabu:
وَنَبِّئۡهُمۡ عَن ضَيۡفِ إِبۡرَٰهِيمَ
51. (መልዕክተኛችን ሙሐመድ ሆይ!) ከኢብራሂም እንግዶችም ወሬ ንገራቸው::
Ibisobanuro by'icyarabu:
إِذۡ دَخَلُواْ عَلَيۡهِ فَقَالُواْ سَلَٰمٗا قَالَ إِنَّا مِنكُمۡ وَجِلُونَ
52. በእርሱ ላይ በገቡና ሰላም ባሉት ጊዜ (የሆነውን አስታውስ):: እርሱም፡- «እኛ ከናንተ ፈሪዎች ነን።» አላቸው።
Ibisobanuro by'icyarabu:
قَالُواْ لَا تَوۡجَلۡ إِنَّا نُبَشِّرُكَ بِغُلَٰمٍ عَلِيمٖ
53. «አትፍራ እኛ አዋቂ በሆነ ወንድ ልጅ እናበስርሃለን።» አሉት።
Ibisobanuro by'icyarabu:
قَالَ أَبَشَّرۡتُمُونِي عَلَىٰٓ أَن مَّسَّنِيَ ٱلۡكِبَرُ فَبِمَ تُبَشِّرُونَ
54. «እርጅና የደረሰብኝ ከመሆኔ ጋር አበሰራችሁኝን? በምን ታበስሩኛላችሁ?» አለ።
Ibisobanuro by'icyarabu:
قَالُواْ بَشَّرۡنَٰكَ بِٱلۡحَقِّ فَلَا تَكُن مِّنَ ٱلۡقَٰنِطِينَ
55. «በእውነት አበሰርንህ ከተስፋ ቆራጮችም አትሁን።» አሉ።
Ibisobanuro by'icyarabu:
قَالَ وَمَن يَقۡنَطُ مِن رَّحۡمَةِ رَبِّهِۦٓ إِلَّا ٱلضَّآلُّونَ
56. «ከጠማማዎችም በስተቀር ከጌታው እዝነት ተስፋን የሚቆርጥ ማነው?» አለ።
Ibisobanuro by'icyarabu:
قَالَ فَمَا خَطۡبُكُمۡ أَيُّهَا ٱلۡمُرۡسَلُونَ
57. «እናንተ መልዕክተኞች ሆይ! ኧረ ለመሆኑ ነገራችሁ ምንድን ነው?» አለ።
Ibisobanuro by'icyarabu:
قَالُوٓاْ إِنَّآ أُرۡسِلۡنَآ إِلَىٰ قَوۡمٖ مُّجۡرِمِينَ
58. አሉም: «እኛ አመፀኞች ወደ ሆኑ ሕዝቦች ተልከናል።
Ibisobanuro by'icyarabu:
إِلَّآ ءَالَ لُوطٍ إِنَّا لَمُنَجُّوهُمۡ أَجۡمَعِينَ
59. «የሉጥ ቤተሰቦች ብቻ ሲቀሩ እነርሱን እኛ ሁላቸውንም በእርግጥ የምናድናቸው ነን።
Ibisobanuro by'icyarabu:
إِلَّا ٱمۡرَأَتَهُۥ قَدَّرۡنَآ إِنَّهَا لَمِنَ ٱلۡغَٰبِرِينَ
60. «ሚስቱ ብቻ ስትቀር።» (አሉ) እርሷንማ በቅጣቱ ውስጥ ከሚቀሩት ሰዎች መሆኗን ወስነናል።
Ibisobanuro by'icyarabu:
فَلَمَّا جَآءَ ءَالَ لُوطٍ ٱلۡمُرۡسَلُونَ
61. መልዕክተኞቹም የሉጥን ቤተሰቦች በመጡባቸው ጊዜ።
Ibisobanuro by'icyarabu:
قَالَ إِنَّكُمۡ قَوۡمٞ مُّنكَرُونَ
62. ሉጥ «እናንተ የተሳሳታችሁ ሕዝቦች ናችሁ።» አላቸው።
Ibisobanuro by'icyarabu:
قَالُواْ بَلۡ جِئۡنَٰكَ بِمَا كَانُواْ فِيهِ يَمۡتَرُونَ
63. አሉም: «አይደለም:: እኛ ህዝቦችህ በእሱ ይጠራጠሩበት በነበሩት ቅጣት መጣንልህ።
Ibisobanuro by'icyarabu:
وَأَتَيۡنَٰكَ بِٱلۡحَقِّ وَإِنَّا لَصَٰدِقُونَ
64. «እውነትንም ይዘን መጣንልህ:: እኛም በእርግጥ እውነተኞች ነን።
Ibisobanuro by'icyarabu:
فَأَسۡرِ بِأَهۡلِكَ بِقِطۡعٖ مِّنَ ٱلَّيۡلِ وَٱتَّبِعۡ أَدۡبَٰرَهُمۡ وَلَا يَلۡتَفِتۡ مِنكُمۡ أَحَدٞ وَٱمۡضُواْ حَيۡثُ تُؤۡمَرُونَ
65. «ከቤተሰብህ ጋር በሌሊቱ ከፊል (አጋማሽ) ላይ ሂድ:: በኋላቸዉም ተከተል:: ከናንተም አንድም ሰው ወደ ኋላው አይገላመጥ:: ወደ ታዘዛችሁበትም ስፍራ እለፉ።» አሉት::
Ibisobanuro by'icyarabu:
وَقَضَيۡنَآ إِلَيۡهِ ذَٰلِكَ ٱلۡأَمۡرَ أَنَّ دَابِرَ هَٰٓؤُلَآءِ مَقۡطُوعٞ مُّصۡبِحِينَ
66. ወደ እርሱም ያንን ትዕዛዝ አወረድን :: እርሱም የእነዚህ ሕዝቦች መጨረሻ ያነጉ ሲሆኑ ስራቸው መቆረጥ ነው::
Ibisobanuro by'icyarabu:
وَجَآءَ أَهۡلُ ٱلۡمَدِينَةِ يَسۡتَبۡشِرُونَ
67. የከተማይቱም ሰዎች የሚበሳሰሩ ሆነው መጡ::
Ibisobanuro by'icyarabu:
قَالَ إِنَّ هَٰٓؤُلَآءِ ضَيۡفِي فَلَا تَفۡضَحُونِ
68. ሉጥም አለ፡- «እነዚህ እንግዶቼ ናቸውና አታጋልጡኝ።
Ibisobanuro by'icyarabu:
وَٱتَّقُواْ ٱللَّهَ وَلَا تُخۡزُونِ
69. «አላህንም ፍሩ አታሳፍሩኝም።»
Ibisobanuro by'icyarabu:
قَالُوٓاْ أَوَلَمۡ نَنۡهَكَ عَنِ ٱلۡعَٰلَمِينَ
70. «ከዓለማት ማንንም እንዳታስተናግድ አልከለከልንህምን?» አሉት።
Ibisobanuro by'icyarabu:
قَالَ هَٰٓؤُلَآءِ بَنَاتِيٓ إِن كُنتُمۡ فَٰعِلِينَ
71. ሉጥም፡- «እነዚህ ሴቶች ልጆቼ ናቸው። የምትፈጽሙ ከሆናችሁ አግቧቸው።» አለ።
Ibisobanuro by'icyarabu:
لَعَمۡرُكَ إِنَّهُمۡ لَفِي سَكۡرَتِهِمۡ يَعۡمَهُونَ
72. (መልዕክተኛችን ሙሐመድ ሆይ!) በዕድሜህ እንምላለን እነርሱ በእርግጥ በስካራቸው ውስጥ ይዋልላሉ::
Ibisobanuro by'icyarabu:
فَأَخَذَتۡهُمُ ٱلصَّيۡحَةُ مُشۡرِقِينَ
73. ጩኸቲቱም ጸሐይ የወጣችባቸው ሲሆኑ ያዘቻቸው::
Ibisobanuro by'icyarabu:
فَجَعَلۡنَا عَٰلِيَهَا سَافِلَهَا وَأَمۡطَرۡنَا عَلَيۡهِمۡ حِجَارَةٗ مِّن سِجِّيلٍ
74. ላይዋንም ከታችዋ አደረግን:: በእነርሱም ላይ የሸክላ ድንጋዮችን አዘነብንባቸው::
Ibisobanuro by'icyarabu:
إِنَّ فِي ذَٰلِكَ لَأٓيَٰتٖ لِّلۡمُتَوَسِّمِينَ
75. በዚህ ውስጥ ለተመልካቾች በእርግጥ ብዙ መገሰጫዎች አሉበት::
Ibisobanuro by'icyarabu:
وَإِنَّهَا لَبِسَبِيلٖ مُّقِيمٍ
76. እርሷም ከተማይቱ በቀጥታ መንገድ ላይ ናት::
Ibisobanuro by'icyarabu:
إِنَّ فِي ذَٰلِكَ لَأٓيَةٗ لِّلۡمُؤۡمِنِينَ
77. በዚህ ውስጥ በእርግጥ ለአማኞች መገሰጫ አለ::
Ibisobanuro by'icyarabu:
وَإِن كَانَ أَصۡحَٰبُ ٱلۡأَيۡكَةِ لَظَٰلِمِينَ
78. እነሆ የአይካ ሰዎችም በእርግጥ በዳዮች ነበሩ::
Ibisobanuro by'icyarabu:
فَٱنتَقَمۡنَا مِنۡهُمۡ وَإِنَّهُمَا لَبِإِمَامٖ مُّبِينٖ
79. ከእነርሱም ተበቀልን ሁለቱም የሉጥና የአይከት ሕዝቦች ከተሞች በእርግጥ በግልጽ መንገድ ላይ ናቸው::
Ibisobanuro by'icyarabu:
وَلَقَدۡ كَذَّبَ أَصۡحَٰبُ ٱلۡحِجۡرِ ٱلۡمُرۡسَلِينَ
80. የሒጅር ሰዎች መልዕክተኞቹን በእርግጥ አስተባበሉ::
Ibisobanuro by'icyarabu:
وَءَاتَيۡنَٰهُمۡ ءَايَٰتِنَا فَكَانُواْ عَنۡهَا مُعۡرِضِينَ
81. ተዓምራታችንን ሰጠናቸው ከርሷም ዘንጊዎች ነበሩ::
Ibisobanuro by'icyarabu:
وَكَانُواْ يَنۡحِتُونَ مِنَ ٱلۡجِبَالِ بُيُوتًا ءَامِنِينَ
82. ከኮረብታዎችም ቤቶችን ጸጥተኞች ሆነው ይጠርቡ ነበር::
Ibisobanuro by'icyarabu:
فَأَخَذَتۡهُمُ ٱلصَّيۡحَةُ مُصۡبِحِينَ
83. ያነጉ ሲሆኑ ጩኸት ያዘቻቸው (ወደሙ)።
Ibisobanuro by'icyarabu:
فَمَآ أَغۡنَىٰ عَنۡهُم مَّا كَانُواْ يَكۡسِبُونَ
84. ይሠሩት የነበሩትም ምንም አልጠቀማቸዉም::
Ibisobanuro by'icyarabu:
وَمَا خَلَقۡنَا ٱلسَّمَٰوَٰتِ وَٱلۡأَرۡضَ وَمَا بَيۡنَهُمَآ إِلَّا بِٱلۡحَقِّۗ وَإِنَّ ٱلسَّاعَةَ لَأٓتِيَةٞۖ فَٱصۡفَحِ ٱلصَّفۡحَ ٱلۡجَمِيلَ
85. ሰማያትንና ምድርን በመካከላቸው ያለውንም ሁሉ በእውነት እንጂ በላግጣ አልፈጠርንም:: ሰዓቲቱም በእርግጥ መጪ ናት:: መልካምን ይቅርታ አድርግላቸው::
Ibisobanuro by'icyarabu:
إِنَّ رَبَّكَ هُوَ ٱلۡخَلَّٰقُ ٱلۡعَلِيمُ
86. (መልዕክተኛችን ሙሐመድ ሆይ!) ጌታህ እርሱ ያልነበረን ነገር ሁሉ ፈጣሪው፤ አዋቂው ነው።
Ibisobanuro by'icyarabu:
وَلَقَدۡ ءَاتَيۡنَٰكَ سَبۡعٗا مِّنَ ٱلۡمَثَانِي وَٱلۡقُرۡءَانَ ٱلۡعَظِيمَ
87. (መልዕክተኛችን ሙሐመድ ሆይ!) ከሚደጋገሙ የሆኑን ባለ ሰባት አንቀጽንና ታላቁንም ቁርኣን በሙሉ በእርግጥ ሰጠንህ::
Ibisobanuro by'icyarabu:
لَا تَمُدَّنَّ عَيۡنَيۡكَ إِلَىٰ مَا مَتَّعۡنَا بِهِۦٓ أَزۡوَٰجٗا مِّنۡهُمۡ وَلَا تَحۡزَنۡ عَلَيۡهِمۡ وَٱخۡفِضۡ جَنَاحَكَ لِلۡمُؤۡمِنِينَ
88. ከእነርሱ ከከሓዲያን ብዙዎችን ወገኖች በእርሱ ወደ አጣቀምንበት ጸጋ ዓይኖችህን አትዘርጋ፤ በእነርሱም ላይ ባያምኑ አትዘን፤ ክንፍህንም ለአማኞች አለዝብ።
Ibisobanuro by'icyarabu:
وَقُلۡ إِنِّيٓ أَنَا ٱلنَّذِيرُ ٱلۡمُبِينُ
89. (መልዕክተኛችን ሙሐመድ ሆይ!) «ግልጽ አስፈራሪ እኔ ነኝ።» በል።
Ibisobanuro by'icyarabu:
كَمَآ أَنزَلۡنَا عَلَى ٱلۡمُقۡتَسِمِينَ
90. (ሰዎችን ለማገድ የመካን በሮች) በተከፋፈሉት ላይ እንደ አወረድነው (ቅጣት አስፈራሪያችሁ ነኝ በል)::
Ibisobanuro by'icyarabu:
ٱلَّذِينَ جَعَلُواْ ٱلۡقُرۡءَانَ عِضِينَ
91. እነርሱም እነዚያ ቁርኣንን ክፍልፍሎች ያደረጉ ናቸው::
Ibisobanuro by'icyarabu:
فَوَرَبِّكَ لَنَسۡـَٔلَنَّهُمۡ أَجۡمَعِينَ
92. (መልዕክተኛችን ሙሐመድ ሆይ!) በጌታህ እንምላለን ሁላቸውንም እንጠይቃቸዋለን::
Ibisobanuro by'icyarabu:
عَمَّا كَانُواْ يَعۡمَلُونَ
93. ይሠሩት ከነበሩት ነገር ሁሉ
Ibisobanuro by'icyarabu:
فَٱصۡدَعۡ بِمَا تُؤۡمَرُ وَأَعۡرِضۡ عَنِ ٱلۡمُشۡرِكِينَ
94. (መልዕክተኛችን ሙሐመድ ሆይ!) የታዘዝክበትንም ነገር በይፋ ግለጽ:: አጋሪዎችንም ተዋቸው::
Ibisobanuro by'icyarabu:
إِنَّا كَفَيۡنَٰكَ ٱلۡمُسۡتَهۡزِءِينَ
95. ተሳላቂዎችንም ሁሉ እኛ በቅተንሃል::
Ibisobanuro by'icyarabu:
ٱلَّذِينَ يَجۡعَلُونَ مَعَ ٱللَّهِ إِلَٰهًا ءَاخَرَۚ فَسَوۡفَ يَعۡلَمُونَ
96. እነርሱም እነዚያ ከአላህ ጋር ሌላ አምላክን ያደረጉ ናቸው:: በእርግጥም ፍጻሜያቸውን ወደፊት ያውቃሉ::
Ibisobanuro by'icyarabu:
وَلَقَدۡ نَعۡلَمُ أَنَّكَ يَضِيقُ صَدۡرُكَ بِمَا يَقُولُونَ
97. (መልዕክተኛችን ሙሐመድ ሆይ!) አንተም በሚሉት ነገር ልብህ የሚጠብ መሆኑን እናውቃለን::
Ibisobanuro by'icyarabu:
فَسَبِّحۡ بِحَمۡدِ رَبِّكَ وَكُن مِّنَ ٱلسَّٰجِدِينَ
98. ጌታህን ከማመስገን ጋር አጥራው:: ከሰጋጆቹም ሁን::
Ibisobanuro by'icyarabu:
وَٱعۡبُدۡ رَبَّكَ حَتَّىٰ يَأۡتِيَكَ ٱلۡيَقِينُ
99. (መልዕክተኛችን ሙሐመድ ሆይ!) እውነቱም ነገር (ሞት) እስኪመጣልህ ድረስ ጌታህን ተገዛ::
Ibisobanuro by'icyarabu:
 
Ibisobanuro by'amagambo Isura: Al Hijri
Urutonde rw'amasura numero y'urupapuro
 
Ibisobanuro bya qoran ntagatifu - الترجمة الأمهرية - زين - Ishakiro ry'ibisobanuro

ترجمة معاني القرآن الكريم إلى اللغة الأمهرية ترجمها محمد زين نهر الدين صادرة عن أكاديمية أفريقيا.

Gufunga